1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጉጂ ገዳ የስልጣን ርክክብ ከስምንት ዓመት በኋላ ሜኤ ቦኩ ላይ ይደረጋል

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 18 2016

የኦሮሞ የገዳ ስረዓት በጣም ረቂቅና ውስብስብ የአስተዳደር ስረዓት ሆኖ የኦሮሞ ሕዝብን ማኀበራዊና ፖለቲካዊ ሕይወት አንቀሳቃሽ ሞተር ሆኖ ዘመናትን የተሻገረ የዲሞክራሲ ስረዓት ስለመሆኑ ይነገርለታል። በጉጂ የኦሮሞ የገዳ ስረዓት በየስምንት ዓመቱ የሚከናወነው የበትረ ስልጣን ርክክብ ለ75ኛ ጊዜ ዘንድሮ ይከናወናል።

https://p.dw.com/p/4adGD
Äthiopien | Oromo | Abageda Jilo Man'o
ምስል Seyoum Getu/DW

የጉጂ ገዳ ስረዓት እና ተጠባቂው የስልጣን ርክክብ


የኦሮሞ የገዳ ስረዓት በጣም ረቂቅና ውስብስብ የአስተዳደር ስረዓት ሆኖ የኦሮሞ ሕዝብን ማኀበራዊና ፖለቲካዊ ሕይወት አንቀሳቃሽ ሞተር ሆኖ ዘመናትን የተሻገረ የዲሞክራሲ ስረዓት ስለመሆኑ ይነገርለታል። በጉጂ የኦሮሞ የገዳ ስረዓት በየስምንት ዓመቱ የሚከናወነው የበትረ ስልጣን ርክክብ ለ75ኛ ጊዜ ዘንድሮ ይከናወናል።  በፊታችን የካቲት ወር አጋማሽ የሚደረገው የጉጂ አባ ገዳ በትር ስልጣን ርክክብ የአንድ ሰው ስልጣን ማስረከብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን አዳዲስ አልያም የተሻሻሉ ህጎች የሚተዋወቁበት ፣ በተለያዩ የዕድሜ ክልል ውስጥ የተካተቱ ሰዎች ወደ ሌላኛው የዕድሜ ምዕራፍ ወይም ፓርቲ የሚሸጋገሩበት እንደመሆኑ ቀኑ በእርግጥ ለጉጂዎች በናፍቆት ይጠበቃል ። ጤና ይስጥልን አድማጮች የዛሬው የባህል መድረክ ዝግጅታችንበየስምንት ዓመቱ የሚከናወነውንና ዘንድሮ ለ75ኛው ጊዜ የሚካሄደውን የጉጂ አባ ገዳ በትረ ስልጣን ርክክብ እና የኦሮሞ የገዳ ስረዓትን ከብዙ በጥቂቱ ይዳስሳልየቀድሞ አባገዳ አጋ ጠንጠኖ ፋውንዴሽን ምስረታ

የጉጂ ገዳ ስረዓት ታሪካዊ ዳራ

ለዘመናዊው የዴሞክራሲ ስረዓት መሰረት ጥለዋል ተብለው ከሚጠቀሱ ጥንታዊ ህዝባዊ አስተዳደሮች  የገዳ ስረዓት አንዱና ተጠቃሽ እንደሆነ በመስኩ የተደረጉ ጥናቶች ያመለክታሉ ።

ከኦሮሞ ህዝብ በተጨማሪ ሌሎች እንደ ኮንሶ ያሉ መሰረታቸውን ኢትዮጵያውያ ውስጥ ያደረጉ ህዝቦችን ጨምሮ  በተቀረው የአፍሪቃ ክፍል እንደ የሞሮኮ እና ቱኒዚያ በርበሮች እና እንደ የናይጄሪያዎቹ ፉላኒዎች ያሉ የኩሽ ነገዶች የተመሳሳይ ስረዓት አራማጆች ስለመሆናቸው ይነገርላቸዋል።

በጉጂ የኦሮሞ የገዳ ስረዓት በየስምንት ዓመቱ የሚከናወነው የበትረ ስልጣን ርክክብ ለ75ኛ ጊዜ ዘንድሮ ይከናወናል። ሜኤ ቦኩ ላይ የሚደረገው የስልጣን ርክክብ ረዥም እና ውስብስብ ሂደቶችን አልፎ የሚደረግ እንደመሆኑ መጠን በጉጂ ብሎም በተቀረው የኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ተጠባቂ መሆኑ ነው የሚነገረው ።በኦሮሚያ ክልል መቋጫ ላጣው ግጭት የቀረበ የሰላም ጥሪ

ዶ/ር ተፈሪ ንጉሴ በዩናይትድ ስቴትስ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኖርዝዌስተርን እንና ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሚኒሶታ ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው ። የኦሮሞ የገዳ ስረአትን ማጥናት ብቻ ሳይሆን የተሻሻሉ ሕጎችን በማርቀቅ ጭምር ሚና እንደነበራቸው ይነገርላቸዋል። የጉጂ ገዳን ከአጠቃላዩ የኦሮሞ የገዳ ስረዓት ታሪካዊ አጀማመር ጋር እያጣቀሱ ይናገራሉ።

ዶ/ር ተፈሪ ንጉሴ በዩናይትድ ስቴትስ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኖርዝዌስተርን እንና ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሚኒሶታ ተባባሪ ፕሮፌሰር
በጉጂ የኦሮሞ የገዳ ስረዓት በየስምንት ዓመቱ የሚከናወነው የበትረ ስልጣን ርክክብ ለ75ኛ ጊዜ ዘንድሮ ይከናወናል። ሜኤ ቦኩ ላይ የሚደረገው የስልጣን ርክክብ ረዥም እና ውስብስብ ሂደቶችን አልፎ የሚደረግ እንደመሆኑ መጠን በጉጂ ብሎም በተቀረው የኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ተጠባቂ መሆኑ ነው የሚነገረው ።ምስል privat

«የጉጂ ገዳ ለሰባ አምስተኛ ጊዜ ሊተላለፍ ነው። አንዳንዶች የጉጂ ገዳን በ1420 ጀመረ የሚሉ አሉ አንዳንዶች ደግሞ በ1440 ነው የጀመረው ይላሉ ፤ ተቀራራቢ ነው የሚባለው ግን በ1440 እንደ ተጀመረ ነው። በግልጽ የሚታወቀው የፊታችን የካቲት 15 ቀን የሃርሞፋ ፓርቲ ለሮበሌ ፓርቲ ስልጣኑን ያስረክባል።»

የጉጂ አባ ገዳ የስልጣን ሽግግር ሂደት

የጉጂ አባ ገዳ የስልጣን ሽግግር ለማድረግ አምስት ተከታታይ ቀናት የሚወስድ ሂደት ውስጥ ያልፋል። በእያንዳንዱ ቀንም የኡራጋ ማቲ እና ሆኩ እንደ ገዳ ፣ ዶሪ እና ራባ ያሉ የተለያዩ የገዳ ፓርቲ አባላት መስመር ሰርተው ወደ መሰብሰቢያው ስፍራ ያቀናሉ ። እንዲያም ሆኖ ግን በተለየ ሁኔታ ካልሆነ በቀር አዲሱ ተመራጭ አባ ገዳ እስከ የምርጫው ቀን ድረስ አይታወቅም ።

«አባ ገዳ የሚሆነው ማነው ለሚለው አይታወቅም ። የመጨረሻ ምርጫ የሚደረገው የካቲት 15 ቀን ስለሆነ ነው። ከሶስቱ የኡራጋ ማቲ እና ሆኩ ከሚቀርቡ ሶስት ዕጩዎች ውስጥ አንዱ ተመርጦ አባ ገዳ ይሆናል።»

የስልጣን ርክክቡን ባህላዊ ሁነት በማይዳሰስ ቅርስነት ማስመዝገብ

በጉጂ ሜኤ ቦኩ የሚደረገው የአባ ገዳ የስልጣን ርክክብ የራሱን ባህላዊ እና መንፈሳዊ ትውፊት ተከትሎ እንደመደረጉ መጠን በስነስረዓቱ ላይ የሚካፈለው የህብረተሰብ ክፍል ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ይነገራል። አቶ ጂሎ ኬሜ የሜኤ ቦኩ የአባ ገዳ ስልጣን ርክክብ ስነስረዓትን ከሚያቀናጁ ሰዎች አንዱ ናቸው። ስነስረአቱ ከገዳ ስረዓት በተጨማሪ ራሱን ችሎ  በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በማይዳሰስ ቅርስነት እንዲመዘገብ ጥረት እንደሚያደርጉ ነው የሚናገሩት ።

«ዩኔስኮ ላይ ቢመዘገብ ምክንያቱም እዚያ ቦታ ላይ የሚገኘው የህዝብ ቁጥር እጅግ በጣም ከፍተኛ ስለሆነ ፤ ሁለተኛ እንደ ባህላዊ መልክዓ ምድር እንዲመዘገብ እንፈልጋለን ። የተለየ ምክንያቱ ስነስረዓቱ የሚከናወንበት ቦታ አይም ሜኤ ቦኩ እንደ ቅዱስ ስለሚታይ ነው። »የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት ሰብሳቢ ስለ ኦሮሚያው ግጭት

የጉጂ አባ ገዳ የስልጣን ወሰን

የጉጂ ገዳ እንደተቀሩት የኦሮሞ ገዳዎች ሁሉ የራሱ የስልጣን ወሰን እና ገደብ አለው ። ተፈጻሚነቱም እዚያው ጉጂ ውስጥ ነው ። ለዚህ ደግሞ በቅርቡ በተመሳሳይ ተከናውኖ የነበረው የቦረና አባ ገዳ የስልጣን ርክክብን በማሳያነት ማንሳት ይቻላል።ይህ ግን እንዴት እንዲህ ሆነ ኦሮሞ በአንድ ወቅት በአንድ ገዳ ስረዓት በአንድ አባ ገዳ ይመራ አልነበረ ወይ የሚል ጥያቄ ያስነሳል ። የባህል እና ቅርስ አጥኚው ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ተፈሪ ንጉሴ ታሪካዊ ዳራውን መለስ ብለው ያስታውሳሉ ።

ዶ/ር ተፈሪ ንጉሴ በዩናይትድ ስቴትስ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኖርዝዌስተርን እንና ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሚኒሶታ ተባባሪ ፕሮፌሰር
የጉጂ ገዳ እንደተቀሩት የኦሮሞ ገዳዎች ሁሉ የራሱ የስልጣን ወሰን እና ገደብ አለው ። ተፈጻሚነቱም እዚያው ጉጂ ውስጥ ነው ። ለዚህ ደግሞ በቅርቡ በተመሳሳይ ተከናውኖ የነበረው የቦረና አባ ገዳ የስልጣን ርክክብን በማሳያነት ማንሳት ይቻላል።ምስል privat

« በታሪክ እንደምናስታውሰው እስከ አስራሰባተኛው ክፍለዘመን ድረስ አንድ አባ ገዳ ነበረን ሁላችንም (ኦሮሞ) ነገር ግን የኦሮሞ መስፋፋት ገሚሱን ወደ ምዕራብ ፣ ገሚሱን ወደ ምስራቅ ፣ ገሚሱ ወደ ሰሜን በመሄዱ ግንኙነት እንዲቋረጥ ምክንያት ሆነ  ።  እንደዚያም ሆኖ ግን ባሌ ሙዳ ላይ በዓመት አንዴ ይገናኙ ነበር። ነገር ግን የየራሳቸውን አባ ገዳ ይዘው ነበር የሚመጡት  »

የኦሮሞ ገዳ ስረዓት አደረጃጀትና አሰራር ተወራራሽና ትስስር ካላቸው የገዳ እረከኖች ያሉት በትውልድ ቅደም ተከተል ላይ የተመሰረተ ማህበራዊ አደረጃጀት ነው። ለገዳ ሥረዓት አሰራር ወሳኝ ሚና ያለው የገዳ እርከን ነው። ሙሉ የገዳ ዑደት በአስር እርከኖች የተከፋፈለ ነው። እያንዳንዱ እርከን የስምንት ዓመት ዕድሜ አለው። ይህም ማለት ሙሉ የገዳ ዑደት 80 ዓመት ይፈጃል ማለት ነው። ይህም ማለት አንድ ሰው ተወልዶ እስኪሞት ድረስ በተለያዩ የዕድሜ ደረጃ በደረሰ ቁጥር በተለያዩ የገዳ እርከኖች ውስጥ ተሳታፊ እየሆነ መዝለቅ አለበት ማለት ነው ። የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት ጥሪ

« እጅግ በጣም ሰፊ ማህበረሰብ ነው በጉጉት እየጠበቀ ያለው ። አንደኛ የጉጂ ማህበረሰብ እንደ ማህበረሰብ ሁሉም ካለበት ደረጃ  አንድ ደረጃ ከፍ  የሚልበት እኔን ጨምሮ ሁሉም ከነበርንበት አባቶቻችን አንድ ደረጃ ወደ ላይ ሲጠጉ እኛም ያንኑ ተከትለን አንድ ደረጃ ወደ ላይ ከፍ የምንልበት ስለሆነ  እንደመሆኑ በጉጉት ነው የሚጠብቀው »

የጉጂ ገዳ ስረዓትን ለተቀረው ዓለም የማስተዋወቅ ጥረት

የጉጂ የገዳ ስረዓትም ይሁን አጠቃላይ የማህበረሰቡ ባህላዊ እና መንፈሳዊ ትውፊቶች ሰፊ እና ዕምቅ በአግባቡ ለተቀረው ዓለም ገና በአግባቡ ያልተዋወቀ እንደመሆኑ ድምጻዊ አቡሽ ዘለቀ በከፈተው መንገድ የወጡ እንደአደም መሐመድ እና ጫልቱ ቡቶ ያሉ ድምጻውያን ይህንኑ ቱባ ባህል ለማስተዋወቅ በውጣ ውረድ ውስጥ ደፋ ቀና እያሉ ስለመሆናቸው ይናገራሉ ።

ድምጻዊ አደም መሀመድ
የጉጂ የገዳ ስረዓትም ይሁን አጠቃላይ የማህበረሰቡ ባህላዊ እና መንፈሳዊ ትውፊቶች ሰፊ እና ዕምቅ በአግባቡ ለተቀረው ዓለም ገና በአግባቡ አልተዋወቀምምስል privat

በገዳ ስረዓት ውስጥ የዴሞክራሲ መገለጫ ተደርገው ከሚወሰዱት ውስጥ ከጥንት ከጥዋቱ ጀምሮ በተለያየ የዕድሜ ዕርከን ውስጥ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚኖራቸው ሚና አንዱ ሲሆን በዚህ ሂደት ሴቶች የነበራቸው ሚና ጎልቶ እንደሚጠቀስ ዶ/ር ንጉሴ ይናገራሉ።

« የገዳን ዑደት ስትመለከት ፤ በተለይ ከጉጂ አንጻር አፈ ታሪክ የሚነግረን የገዳ ስረዓት መጀመሪያ ላይ በሴቶች ሲተዳደር እንደነበር ነው»

የፊታችን የካቲት ሜኤ ቦኩ የምታስተናግደው የባሊ ወይም የስልጣን ርክክብ ከመከናወኑ አስቀድሞ ተጠባቂ ስነስረዓቶች አሉ ፤“ህዝብን የሚገድል ጠላት ነዉ”  የጉጂ አባገዳዎች ህብረት

የስልጣን ሽግግሩ ተግዳሮቶች እና ስኬት

ከ600 ዓመታት በላይ የዘለቀው የጉጂ ጋዳ የስልጣን ሽግግር በውጣ ውረድ ውስጥ ማለፉን በስረዓቱ ላይ ጥናት ያደረጉቱ ይገልጻሉ ። ዶ/ ር ተፈሪ እንደሚሉት የቅርብ ዓመታት የስልጣን ሽግግር ከጥቂት መሰናክሎች በቀር የተሳካ እንደነበር ያስታውሳሉ ።
የፊታችን የካቲት ሜኤ ቦኩ የምታስተናግደው የባሊ ወይም የስልጣን ርክክብ ከመከናወኑ አስቀድሞ ተጠባቂ ስነስረዓቶች አሉ ፤ ጂሎ ኬሜ 3

« ሜኤ ቦኩ ላይ ጉሚው ወይም ስብሰባዊ የሚቀመጠው ለ28 ቀናት ነው ። የስልጣን ርክክቡ የሚደረገው የካቲት አስራ አምስት ቀን ወይም በመጨረሻው ቀን ነው።  እስከዚያው ድረስ የተለያዩ ስነስረዓቶች ይከናወናሉ ። የተሻሻለ ሕግ ካለ ፤ አዲስ የወጣ ሕግም ካለ ለየፓርቲው እያስተዋወቀ ይቆያል»

ድምጻዊ አደም መሀመድ
ከ600 ዓመታት በላይ የዘለቀው የጉጂ ጋዳ የስልጣን ሽግግር በውጣ ውረድ ውስጥ ማለፉን በስረዓቱ ላይ ጥናት ያደረጉቱ ይገልጻሉ ።ምስል privat

በገዳ ስረዓት ውስጥ የመንግስት ጣልቃ ገብነት ያስከተለው መዘዝ

የጉጂም ይሁን አጠቃላይ የኦሮሞ የገዳ ስረዓት ከዘመናዊ የፖለቲካ ስርዓት በትይዩ ህዝቡን በባህላዊ መንገድ የማስተዳደር መብት ቢኖረውም በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ የፖለቲካ አስተዳደሩ ጫና ሲያሳድርበት እና የገዳ ስረዓቱ እና ስረዓቱን የሚመሩ አባገዳዎች ህይወታቸውን እስከማጣት የደረሱበትን የመንግስት ኃይሎች ጥቃት መለስ ብሎ ማስታወስ ይቻላል ይላሉ ችግሩን በጥልቀት ያጠኑቱ ። ዶ/ር ተፈሪ እንደሚሉት የፖለቲካዊው አስተዳደር የገዳን ብቻ ሳይሆን በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ሌሎች መንፈሳዊ አባቶችን ያላከበረ እና ለፖለቲካዊ ፍጆታ እየተጠቀመባቸው መምጣቱ ባህላዊ ስረዓቶቹ ለችግር ስለመጋለጣቸው በማሳያነት ያነሳሉ ። የገዳ ሥርዓት መመዝገብ

« ከፍተኛ ጫና ነው ያለው ምክንያቱም የየአካባቢውም ይሁን በኦሮሚያ ደረጃ ያሉ አስተዳዳሪዎች እየደወሉ እንዲህ አድርጉ እያሉ እያሉ አባቶችን ለችግር እያጋለጡ ነው»

የሆነ ሆኖ የጉጂ ገዳ ለመመረጥ ጥሩ የንግግር ችሎታ ፤ የማህበረሰቡን ጥንታዊ ታሪካዊና ወግ ጠንቅቆ የሚያውቅ  በመደቡ የስልጣን ዘመን ማህበረሰቡን ለመምራት የሚያስችል እምቅ ችሎታ አለው የሚለውን አባ ገዳ ከፊታችን የካቲት 15 ቀን ይመርጣል ። ተመራጩ በኦሮሚያ ክልል የአባ ገዳዎች ህብረት አባል ሲሆን ምናልባትም የኦሮሚያ አባ ገዳዎች ህብረት አባ ገዳ ሆኖ መመረጥ የሚችልበትን ዕድልም ሊያገኝ ይችላል ።

ታምራት ዲንሳ

ኂሩት መለሰ