1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት ጥሪ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 4 2014

የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት ባሳለፈው ውሳኔ በተለይም በኦሮሚያ እና ከአገር ውጭ ያሉት እንዲሁም መንግስትን የሚፋለሙ ኃይላት ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ስርዓት እንዲመለሱ መንግስትም በሩን እንዲከፍት አሳስበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በግንባር በመምራት በአማጺያን ላይ ባገኙ የበላይነትም “አባ ቢያ” የሚል የጀግንነት ስም ሰጥተውአቸዋል፡፡

https://p.dw.com/p/44Chu
Äthiopien | Irreechaa Feierlichkeiten der Volkdgruppe der Oromo
ምስል Seyoum Getu/DW

የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት ጥሪ

በኢትዮጵያ በፖለቲካ ልዩነት የተነሳ የሚደርሱ የህዝብ ደህንነትና ፀጥታ ችግሮች እልባት እንዲያገኙ የኦሮሞ አባገዳዎች ጥሪ አቀረቡ። ተቃዋሚዎችም የአገር ጥቅም ከሚያስከብር ዓላማ ጎን እንዲቆሙ ጠየቁ። የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ ባሳለፉት ውሳኔ በተለይም በአገር ውስጥ በኦሮሚያ እና ከአገር ውጭ ያሉት እና መንግስትን የሚፋለሙ ኃይላት ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ስርዓት እንዲመለሱ፤ መንግስትም ለዚሁ በሩን እንዲከፍት አሳስበዋል። አባገዳዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ጥምር ጦራቸውን በግንባር በመምራት በአማጺያን ላይ ባሳዩት የበላይነትም “አባ ቢያ” የሚል የጀግንነት ስም ሰጥተውአቸዋል፡፡ ህዳር 22 ቀን 2014 ዓ.ም. ግድያ የተፈፀመባቸው የከረዩ አባገዳዎች ጉዳይም ተጣርቶ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው አባገዳዎቹ መንግስትን ጠይቀዋል። 


ስዩም ጌቱ


ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ