1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የገዳ ሥርዓት መመዝገብ

ነጋሽ መሐመድ
ሐሙስ፣ ኅዳር 22 2009

ገዳ ዓለም አቀፍ ጥበቃ የሚደረግለት የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ ለኢትዮጵያ ድል፤ ለባሕሉ ባለቤቶች እርካታ ነዉ።ለአባገዳ ጃሎ ማዶ ደግሞ አስደሳች ነዉ።መረቁም አባገዳዉ

https://p.dw.com/p/2Tb2s
Symbolbild UNESCO
ምስል dapd

Äth. Gadaa-UNESCO - MP3-Stereo

የኦሮሞ ማሕበረሰብ የሚከተለዉ ባሕላዊ የአስተዳደር እና የሥልጣን ሽግግር ሥርዓት ገዳ በዓለም የማይዳደስስ ቅርስነት ተመዘገበ።አዲስ አበባ የተሰየመዉ የተባበሩት መንግሥታት የትምሕርት የሳይንስና የባሕል ድርጅት (UNESCO) አስራ-አንደኛዉ ስብሰባ ገዳ በዓለም ቅርስነት እንዲጠበቅ ትናንት በአብላጫ ድምፅ ወስኗል።ኢትዮጵያዉያን የገዳ ሥርዓት ተከታዮች እና የኢትዮጵያ መንግሥት ገዳ በዓለም አቀፍ የማይዳሰሱ ባሕላዊ ቅርስነት በመመዝገቡ የተሰማቸዉን ደስታ እየገለጡ ነዉ።ነጋሽ መሐመድ የምዝገባዉን ሒደትና ዉጤቱን የሚቃኝ ዘገባ አለዉ።

ነባሩ የኦሮሞ የአስተዳደር፤ የዕርቅ፤ የሽምግልና እና የሥልጣን ሽግግር ሥርዓት በዓለም አቀፍ ቅርስነት እንዲመዘገብ የኢትዮጵያ መንግሥት፤ በተለይ የባሕል ሚኒስቴር ማጥናት፤መጣር፤ ማስተዋወቅ ከጀመረ ሰወስት ዓመት ከመንፈቅ ፈጅቶበታል።የሚንስቴሩ የሕዝብ እና የዉጪ ግንኙነት ሐላፊ አቶ ገዛኸኝ አባተ እንደሚሉት ገዳን የማስጠናት ማስመዝገቡ ጥረት፤ ሒደት ከመስሪያ ቤታቸዉ ዋና ዋና ዓላማዎች አንዱ ነበር።ዉጤቱ አስደሳች።

 የገዳ ሥርዓት ኢትዮጵያ ዉስጥ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ፤ፖለቲካዊ ጫናዎችን ተቋቁሞ የቀጠለ፤ በሕዝብ የሚጠበቅና ሕዝባዊ ሥርዓት መሆኑ በጥናት ተረጋገጠ ይላሉ አቶ ገዛኸኝ።ጥናቱ የተደረገዉ አንዴና አንድ ሥፍራ አይደለም።

አዲስ አበባ በተሰየመዉ አስራ-አንደኛዉ የዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ሥብሰባ ላይ ከተካፈሉ መልዕክተኞች አንዳዶቹ ገዳ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪቃ ባሕላዊ እሴት አካል ጭምር ነዉ የሚል አስተያየት መስጠታቸዉ ተስምቷል።ሥራዓቱ በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ የቀረበዉ ሰነድ፤ አቶ ገዛኸኝ እንደሚሉት ያለምንም ተቃዉሞ ነዉ የፀደቀዉ።አቶ ገዛኸኝ እንደሚሉት ገዳ ዓለም አቀፍ ጥበቃ የሚደረግለት የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ ለኢትዮጵያ ድል፤ ለባሕሉ ባለቤቶች እርካታ ነዉ።ለአባገዳ ጃሎ ማዶ ደግሞ አስደሳች።

መረቁም አባገዳዉ።ገዳ በቅርስነት መመዝገቡ ባሕሉን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ በዉጤቱም የሐገር ጎብኚዎችን ቁጥር ለማሳደግ እንደሚጠቅም አቶ ገዛኸኝ አስታዉቀዋል።

 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ