1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት የሰላም ጥሪ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 25 2016

የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት አሁን በክልሉ የተፈጠረው የሰላም እጦት ከፍተኛ ቀውስ እንደፈጠረ ሰፋ ያለ ውይይት አድርጓል፡፡ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ተስፋሁን ይህን አስመልክተው እንደገለጡት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች አባሎቻቸውና ደጋፊዎቻቸው ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ ተልዕኮ ሊሰጧቸው እንደሚገባ ስምምነት ተደርሷል ብለዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4ars6
  የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት
በአማራ ክልል የሚንቃሳቀሱ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በክልሉ የሚደረገዉ ዉጊያና ግጭት በዉይይት እንዲፈታ ጠየቀምስል Alemnew Mekonen/DW

የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት የሰላም ጥሪ

በአማራ ክልል የሚንቃሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ትናንት በባሕር ዳር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡ የየምክር ቤቱ  አባላት ውይይታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ሰብሳቢው አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ሰብሳቢው እንዳሉት በቅርቡ በአገራችን ለሚካሄደው አገራዊ የምክክር መድረክ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላቶቻቸውን በማስተባበር ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አስፈላጊውን እገዛና ትብብር ያደርጋሉ፣ በውይይቱ ያለምንም ልዩነት ሁሉም ፓርቲዎች ወኪሎቻቸውን ለውይይቱ እንደሚያዘጋጁም መግባባት መደረሱን አመልክተዋል፡፡

በአማራ ክልል ሁለት ዞኖች ከ85 ሺህ በላይ እንስሳት ከድርቅ ጋር በተያያዘ መሞታቸውን ባለሥልጣናት ገለጹ

“ሀገር እንደ ሀገር ከገባችበት ቅራኔ ሊፈታ የሚችልና ታላቅ ተስፋ የተጣለበት የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን እንደ አማራ ክልል የትኛውም ዓይነት ጥያቄ ሊስተናገድበት የሚችል መድረክ ስለሆነ፣ በዚህ መድረክ የተገለለ ወይም አንዱ ተሳታፊ፣ አንዱ የማይሳተፍ፣ አንዱ አራጊ ፈጣሪ ሌላው ዳር ተመልካች እንዳይሆን ሁላችንም የፖለቲካ ፓርቲዎች በንቃት ተሳትፈን ተወካዮቻችንን ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ አስመርጠን የምንሳተፍ ይሆናል፣  ከምክክር ኮሚሽኑ ጋርም አብረን በትብብርና በጋራ ለመስራት ተስማምተናል፡፡” ብለዋል፡፡

አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ
አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ “ከምክክር ኮሚሽኑ ጋርም አብረን በትብብርና በጋራ ለመስራት ተስማምተናል” ብለዋልምስል Alemnew Mekonen/DW

በአማራ ክልል የሚንቃሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሥራ አስፈፃሚ አባል ዶ/ር ዘርይሁን ፍቅሩ በበኩላቸው የህዝቡ የቆዩ ጥያቄዎች የሚፈቱበት ዋናው መንገድ አገራዊ የምክክር መድረኩ በመሆኑ የሚወከሉ አባላት በንቃት የሚሳተፉ እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት አሁን በክልሉ የተፈጠረው የሰላም እጦት ከፍተኛ ቀውስ እንደፈጠረ ሰፋ ያለ ውይይት አድርጓል፡፡ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ተስፋሁን ይህን አስመልክተው እንደገለጡት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች አባሎቻቸውና ደጋፊዎቻቸው ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ ተልዕኮ ሊሰጧቸው እንደሚገባ ስምምነት ተደርሷል ብለዋል፡፡

 ዶ/ር ዘርይሁን ፍቅሩ
በአማራ ክልል የሚንቃሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሥራ አስፈፃሚ አባል ዶ/ር ዘርይሁን ፍቅሩ የህዝቡ የቆዩ ጥያቄዎች የሚፈቱበት ዋናው መንገድ አገራዊ የምክክር መድረኩ በመሆኑ የሚወከሉ አባላት በንቃት የሚሳተፉ እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡ምስል Alemnew Mekonen/DW

“ሰላም ካጣን ቆይተናል፣ ይህን ሰላም ወደ ነበረበት ለመመለስና ፖለቲካም እንደ ፖለቲካ ለመስራት የምንችለው፣ ሰላም ሲኖር ነው፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የራሳቸው የሆኑ አባላትና ደጋፊዎች አሉት፣ እነዚህ ደጋፊዎችና አባላት ለሰላም የራሳቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ፣ ባላቸው መዋቅርና አደረጃጀት ተልዕኮ እንዲያደርሱ ተወያይተን፣ ተግባብተናል” ብለዋል። 

ተፈናቃዮችን የማቋቋም ውጥንና የተፈናቃዮች ሥጋት

የአማራ ክልላዊ መንግስት ከአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (አዴን) ጋር ያደረገውን የሰላም ስምምነት የጋራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት እንደሚደግፈውና ይህ ዓይነት አስራር ተጠናክሮ እንዲቀጥልም  የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጥሪውን አቅርቧል በማለት አቶ ተስፋሁን ተናግረዋል፡፡

የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ብልፅግናን ጨምሮ 10 ያህል የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያቀፈ ነው፡፡     

ዓለምነው መኮንን