በጀርመን አይሁዶች ላይ የደረሰው በደል 85ተኛ ዓመት መታሰቢያ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 29 2016ማስታወቂያ
የዛሬ 85 ዓመት ጀርመን ውስጥ በአይሁዶች ላይ የተፈፀመው ግፍ ዛሬ በጀርመን ታስቧል። በጎርጎሮሳውያኑ ህዳር 9 ለህዳር 10 አጥቢያ 1938 ዓም በመላ ጀርመን የሚገኙ የይሁዲዎች ሙክራቦች ፣ ሱቆችና መኖሪያ ቤቶች በናዚዎች ትዕዛዝ እንዲወድሙ ተደርጓል ።አይሁድ በመሆናቸው ብቻ የተገደሉ፣ የተደበደቡና የታሰሩ ቁጥር ቀላል የሚባል አልነበረም ።
በጀርመን አይሁዶች ላይ የተፈፀመው ግፍ 75 ተኛ ዓመት መታሰቢያበጀርመን ታሪካዊ ቤተ መዘክር መረጃ መሠረት በጥቃቱ 1,300 ሰዎች ተገድለዋል። 1,400 ሙክራቦች ወድመዋል ወይም ተጎድተዋል፤7 ሺህ ሱቆች ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል። ጥቃቱ ህዳር 10ም ቀጥሎ ቁጥራቸው ወደ 30ሺህ የሚደርስ ወንድ አይሁዶች ወደ ማጎሪያ ካምፖች ተወስደዋል።
ከ85 ዓመት በኋላ ዛሬ ፀረ ሴማናዊነት በጀርመን ብቻ ሳይሆን በሌላው የዓለም ክፍልም ተባብሷል። እለቱን ምክንያት በማድረግ የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝን ጨምሮ የጀርመን መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።
ጀርመን በሚገኙ አይሁዶች ላይ የዛሬ 85 ዓመት ስለ ተፈጸመው ግፍ መታሰቢያ እና በጀርመንና በሌሎችም ሀገራት አሁን ስለተባባሰው ፀረ ሴማዊነት ከበርሊኑ ወኪላችንን ይልማ ኃይለሚካኤልን የስልክ ቃለ ምልልስ አድርገናል።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ