1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን የሚገኙ አይሁድ የደኅንነት ስጋት

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 13 2016

ጀርመን ሀማስን ጨምሮ ሌሎች አሸባሪ ያለቻቸው ቡድኖች በጀርመን እንዳይንቀሳቀሱ ብታግድም፣ ለየሁዲዎች የምታደርገውን ጥበቃም ለማጠናከር ቃል ብትገባም፣ የሁዲዎች ግን አሁንም በሀገሪቱ የወደፊቱ እጣቸው ያሳስባቸዋል። አይሁዶች ከሺህ ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ታሪክ ባላቸው በጀርመን ወደፊት መኖር መቻላቸውን እየተጠራጠሩ ነው ።

https://p.dw.com/p/4Xxwq
ባለፈው እሁድ ለእስራኤል ድጋፋቸውን ለመግለጽ በርሊን ብራንድቡርገር ቱር አደባባይ ለተሰባሰቡ በርካታ ሰዎች ንግግር ያደረጉት የጀርመን ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ጀርመን ለሚገኙ የሁዲዎችና ተቋማቶቻቸው መንግሥት የሚያደርገው ጥበቃ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል። 
የጀርመን መንግሥት እዚህም እዚያም በየሁዲዎች ላይ የሚፈጸሙና ሊፈጸሙ የሚችሉ ጥቃቶችን  መከላከል ሃላፊነቱ  መሆኑን በየአጋጣሚው እያሳወቀ ነው። ምስል Fabrizio Bensch/REUTERS

«አይሁዶች በጀርመን ወደፊት መኖር መቻላቸውን እየተጠራጠሩ ነው»

ናዚ ጀርመን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ወደ 6 ሚሊዮን  የሚገመቱ የሁዲዎችን ከጨፈጨፈ ብዙ አሥርት ዓመታት ተቆጥረዋል። በዛሬዋ ጀርመን ግን ከ100 ሺህ በላይ የሁዲዎች ይኖራሉ።ጀርመን ውስጥ የራሳቸው ቤተ እምነቶች (ሙክራቦች)፣ ትምህርት ቤቶች፣ የስፖርት ክለቦችና የመሳሰሉት ማኅበራትና መሰባሰቢያዎች ያሏቸው የሁዲዎች በተለያዩ ጊዜያት ፀረ-ሴማዊ አቋም ባላቸው ሰዎች ጥቃት ይሰነዘርባቸዋል። በዚህ የተነሳም ከብዙ ዓመታት አንስቶ ጀርመን የሚገኙ የየሁዲዎች ተቋማት የሚደረግላቸው ጥበቃ በፖሊስ ኃይልና በብረት አጥሮች ተጠናክሯል። ከተወሰኑ ጊዜያት ወዲህ ለተቋሞቻቸው የሚደረግ ጥበቃ ደረጃ ከፍ ማለቱን ጀርመን ዋና ከተማ በርሊን የሚገኙ የየሁዲዎች ማኅበር ቃል አቀባይ ኢያን ኪስሊንግ ለዶቼቬለ በኢሜል አስታውቀዋል። ከዛሬ 18 ቀን በፊት ከተጀመረው የሀማስ እስራኤል ጦርነት በኋላ ደግሞ ፣ ጀርመን የሚኖሩ የሁዲዎች ከቀድሞውም የባሰ ጥቃት ሊደርስብን ይችላል የሚል ስጋት ውስጥ ይገኛሉ። በተለይ በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን በሚገኝ አንድ ሙክራብ ላይ የጓዳ ሰራሽ ፈንጂ ጥቃት ከተሞከረና በአንዳንድ መኖሪያ ቤቶቻቸው ላይም  የየሁዲ ምልክቶች መደረግ ከጀመሩ በኋላ  በሰላም መኖር አንደማይችሉ እየተሰማቸው መሆኑን ለዶቼቬለ ገልጸዋል። 

በዛሬዋ ጀርመን ግ ከ100 ሺህ በላይ የሁዲዎች ይኖራሉ።ጀርመን ውስጥ የራሳቸው ቤተ እምነቶች (ሙክራቦች)፣ ትምህርት ቤቶች፣ የስፖርት ክለቦችና የመሳሰሉት ማኅበራትና መሰባሰቢያዎች ያሏቸው የሁዲዎች በተለያዩ ጊዜያት ፀረ-ሴማዊ አቋም ባላቸው ሰዎች ጥቃት ይሰነዘርባቸዋል።
ከብዙ ዓመታት አንስቶ ጀርመን የሚገኙ የየሁዲዎች ተቋማት የሚደረግላቸው ጥበቃ በፖሊስ ኃይልና በብረት አጥሮች ተጠናክሯል።ምስል Rainer Jensen/dpa/picture alliance


« ከባድ አደጋ ላይ እንዳለሁ ይሰማኛል። ድባቡም ከሚገባው በላይ ተባብሷል።የሁዲዎች በማንኛውም ጊዜ ጥቃት ሊደርስባቸው እንደሚችል ነው የሚሰማቸው።»
«ይህ በግልጽ ቁጣ ነው። ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ቁጣ ነው።የሁዲዎችን ለመቃወም የትላልቅ እንቅስቃሴዎች አካል የመሆን ፍላጎት ነው እኔን የሚያስፈራኝ ። »
የበርሊን ነዋሪው የዶቼቬለ የአማርኛ ክፍል ዘጋቢ ይልማ ኃይለ ሚካኤል እንደሚለው የሀማስ-እስራኤል ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ጀርመን የሚገኙ የሁዶች  በእስራኤል ያለው ችግር ወደ ጀርመንም መምጣቱ አይቀርም የሚል ስጋታቸው እያየለ መጥቷል። ይህ የሆነውም በጀርመን ፀረ ሴማዊ እንቅስቃሴዎች እየተባባሱ በመሄዳቸው ነው። ከዚህ በመነሳትም መንግሥት ከዚህ ቀደም የሚያደርግላቸው ጥበቃ እንዲያጠናከርላቸው የሚያሳስቡ  ድምጾች ጎልተው መሰማት ጀምረዋል።ፀረ ሴማዊ ጥቃት በጀርመን

የዶቼቬለዋ አክስል ሮቮልት እንደዘገበችው ከቅዳሜ መስከረም 26 ቀን 2016 ዓመተ ምኅረቱ ጥቃት ወዲህ ጀርመን ከሚገኙ የሁዲዎች ብዙዎቹ  ከቤታቸው እንኳን መውጣት አይደፍሩም። በጀርመን የአይሁድ ተማሪዎች ማኅበር አስተባባሪ ዴቦራህ ኮጋን ለዶቼቬለ እንደተናገረችው ጀርመን የሚገኙ የሁዲዎች ከዚህ ቀደም በሀገሪቱ ደኅንነታችን የተጠበቀ እንደሆነ ነበር የሚያስቡት፤ አሁን ግን ይህ እየሆነ አይደለም የሚል ድምዳሜ ላይ ሊደርሱ ተቃርበዋል። «በርግጥ ሙክራቡ ላይ ጥቃት በመፈጸሙ በጣም ደንግጫለሁ።በተለይም ይህ በጣም ጥቂት ማኅበረሰብ የሚኖርበት አካባቢ በመሆኑ እንዲህ ዓይነት ነገር አልጠበቅኩም ነበር።እዚህ ቢያንስ ደኅንነቴ የተጠበቀ ነው ብለህ ታስባለህ።አሁን እንደምናየው ግን የሚታየው ይህ አይደለም።በአንዳንድ የአይሁዶች ተቋማት አጠገብ ሳልፍ አንዳንድ ጊዜ አንድ የፖሊስ መኮንን ብቻ ሲጠብቅ አያለሁ። ብዙ ጊዜም በአካባቢያቸው የሚሆነውን ከመመልከት ይልቅ የእጅ ስልካቸውን ሲያዩ ነው የማያቸው።» 
የጀርመን መንግሥት እዚህም እዚያም በየሁዲዎች ላይ የሚፈጸሙና ሊፈጸሙ የሚችሉ ጥቃቶችን  መከላከል ሃላፊነቱ  መሆኑን በየአጋጣሚው እያሳወቀ ነው።

የዶቼቬለዋ አክስል ሮቮልት እንደዘገበችው ከቅዳሜ መስከረም 26 ቀን 2016 ዓመተ ምኅረቱ ጥቃት ወዲህ ጀርመን ከሚገኙ የሁዲዎች ብዙዎቹ  ከቤታቸው እንኳን መውጣት አይደፍሩም። በጀርመን የአይሁድ ተማሪዎች ማኅበር አስተባባሪ ዴቦራህ ኮጋን ለዶቼቬለ እንደተናገረችው ጀርመን የሚገኙ የሁዲዎች ከዚህ ቀደም በሀገሪቱ ደኅንነታችን የተጠበቀ እንደሆነ ነበር የሚያስቡት፤ አሁን ግን ይህ እየሆነ አይደለም የሚል ድምዳሜ ላይ ሊደርሱ ተቃርበዋል። 
የዶቼቬለዋ አክስል ሮቮልት እንደዘገበችው ከቅዳሜ መስከረም 26 ቀን 2016 ዓመተ ምኅረቱ ጥቃት ወዲህ ጀርመን ከሚገኙ የሁዲዎች ብዙዎቹ  ከቤታቸው እንኳን መውጣት አይደፍሩም። ምስል Axel Rowohlt/DW

ባለፈው እሁድ ለእስራኤል ድጋፋቸውን ለመግለጽ በርሊን ብራንድቡርገር ቱር አደባባይ ለተሰባሰቡ በርካታ ሰዎች ንግግር ያደረጉት የጀርመን ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ጀርመን ለሚገኙ የሁዲዎችና ተቋማቶቻቸው መንግሥት የሚያደርገው ጥበቃ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል። «በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ከተፈጸሙ ግፎች በኋላ የሁዲዎች እንደገና በሀገራችን መኖራቸው ተአምር ነው። ይህን ልንፈልገውና ልንጠብቀውም የሚገባን ተአምር ነው። አስፈላጊ መሆኑን ባልመኝም፣በየሁዲ ተቋማት ዙሪያ ጥበቃችንን ማጠናከር አለብን። ከኃላ ታሪካችን በመነሳት የየሁዲዎችን ሕይወት ማቆየት የኛ ልዩ ሃላፊነታችንና ስልጣናችን ነው። በዴሞክራሲያችን መሠረት ላይ የተቀረጸ ነው። የየሁዲዎችን ሕይወት መጠበቅ የመንግሥታችን ሃላፊነት ነው። የህዝባዊ ግዴታችንም ነው።»


ከትናንት በስተያ እሁድ በምሥራቅ ጀርመኑ በዛክሰን አንሀልት ፌደራዊ ክፍለ ግዛት ውስጥ በሚገኘው «ዴሳው ሮስላው» በተባለ ከተማ በተካሄደው የሙክራብ ምረቃ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ሀገራቸውን ጨምሮ በመላው ዓለም የተሰራጨውን ፀረ ሴማዊነት እንቅስቃሴ «አሳፋሪ» ሲሉ አውግዘው ከዚህ ቀደም ናዚ ጀርመን በየሁዲዎች ላይ የፈጸመው ጥቃት በሀገሪቱ እንዳይደገም ጀርመን የያዘችው አቋም የጸና እንደሆነ ቃል ገብተዋል።  «ከመስከረም 26ቱ ከባድ ጥቃት በኋላ  ጀርመን ጨምሮ በመላው ዓለም ፀረ ሴማዊነት እና ኢብዓዊ የሆነ ጥላቻ፣ በኢንተርኔትና፣በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች፣በአሳፋሪ ሁኔታ  ሲሰራጭ ቆይቷል። ጀርመኖች በኢይሁዶች ላይ ባካሄዱት  ጭፍጨፋ በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል ፈጸሙ ።በዚህ የተነሳም «ጨርሶ አይደገምም» የሚለው አቋማችን የማይሰበር ሊሆን ይገባል።»። በጀርመን የፀረ አይሁድ እንቅስቃሴ እና የመንግስት የጸና አቋም

የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ በጀርመን የሀማስንና የደጋፊዎቹን እንቅስቃሴዎች እንዲሁም የሳሚዱን ማኅበርን አግደዋል። ጀርመን ሀማስን ጨምሮ ሌሎች አሸባሪ ያለቻቸው ቡድኖች በጀርመን እንዳይንቀሳቀሱ ብታግድም፣ ለየሁዲዎች የምታደርገውን ጥበቃም ለማጠናከር ቃል ብትገባም፣  የሁዲዎች ግን አሁንም በሀገሪቱ የወደፊቱ እጣቸው ያሳስባቸዋል።
የመስከረም 26ቱን የሀማስን ጥቃት ፣አሸባሪ ተብሎ የሚታሰበው «ሳሚዱን» የተባለው  የፍልስጤም ህዝባዊ ነፃ አውጭ ግንባር ቡድን ደጋፊዎች በበርሊን ኖይኮለን በተባለው ክፍለ ከተማ ጣፋጮችን በማደል ማወደሳቸው የጀርመን መንግሥትን በእጅጉ አስቆጥቷል። ምስል Sascha Meyer/dpa/picture alliance

የጀርመን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ናንሲ ፌዘር በበኩላቸው በጀርመን ፀረ ሴማዊነትን ለመከላከል ይረዳል ያሉት «የዴሞክራሲ ማራመጃ ሕግ» በአፋጣኝ እንዲጸድቅ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ጥሪ አቅርበዋል። ፌዘር እንዳሉት ሕጉ ዴሞክራሲን ለማጠናከርና ጽንፈኝነትን ለመከላከል ለሚሰሩ ማኅበራትና ድርጅቶች ወደፊት የተሻለ የገንዘብ ድጋፍ እንዲያገኙ ይረዳል። በፌዘር አባባል ፀረ-ሴማዊነትን መከላከያው መንገድ የፀጥታ ጥበቃ ተቋማትን ማጠናከር ብቻ አይደለም፤ይልቁንም ማኅበራዊ ኃይሎችን ማበርታትም ጭምር እንጂ ። በጀርመን ፀረ ሴማዊ አቋም የሚያራምዱ የተለያዩ አካላት መኖራቸውን ያነሳው ይልማ ሕጉ ያስፈልጋል የተባለበትን ተጨማሪ ምክንያቶች ጠቅሷል።

ከዛሬ 18 ቀን በፊት ከተጀመረው የሀማስ እስራኤል ጦርነት በኋላ ደግሞ ፣ ጀርመን የሚኖሩ የሁዲዎች ከቀድሞውም የባሰ ጥቃት ሊደርስብን ይችላል የሚል ስጋት ውስጥ ይገኛሉ።
ከብዙ ዓመታት አንስቶ ጀርመን የሚገኙ የየሁዲዎች ተቋማት የሚደረግላቸው ጥበቃ በፖሊስ ኃይልና በብረት አጥሮች ተጠናክሯል። ከተወሰኑ ጊዜያት ወዲህ ለተቋሞቻቸው የሚደረግ ጥበቃ ደረጃ ከፍ ማለቱን ጀርመን ዋና ከተማ በርሊን የሚገኙ የየሁዲዎች ማኅበር ቃል አቀባይ ኢያን ኪስሊንግ ለዶቼቬለ በኢሜል አስታውቀዋል። ምስል Rolf Zöllner/IMAGO

የመስከረም 26ቱን የሀማስን ጥቃት ፣አሸባሪ ተብሎ የሚታሰበው «ሳሚዱን» የተባለው  የፍልስጤም ህዝባዊ ነፃ አውጭ ግንባር ቡድን ደጋፊዎች በበርሊን ኖይኮለን በተባለው ክፍለ ከተማ ጣፋጮችን በማደል ማወደሳቸው የጀርመን መንግሥትን በእጅጉ አስቆጥቷል። የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ በጀርመን የሀማስንና የደጋፊዎቹን እንቅስቃሴዎች እንዲሁም የሳሚዱን ማኅበርን አግደዋል። ጀርመን ሀማስን ጨምሮ ሌሎች አሸባሪ ያለቻቸው ቡድኖች በጀርመን እንዳይንቀሳቀሱ ብታግድም፣ ለየሁዲዎች የምታደርገውን ጥበቃም ለማጠናከር ቃል ብትገባም፣  የሁዲዎች ግን አሁንም በሀገሪቱ የወደፊቱ እጣቸው ያሳስባቸዋል። በአሁኑ ጊዜ በጀርመን በየሁዲዎች ላይ በሚደርሰው ጥቃት በእጅጉ የምታዝነው በጀርመን የየሁዲ ተማሪዎች ማኅበር አስተባባሪ ዴቦራህ ኮጋን አይሁዶች ከሺህ ዓመታት በላይ ያስቆጠረ ታሪክ ባስቆጠሩበት በጀርመን ወደፊት መኖር መቻላቸውን እየተጠራጠሩ ነው ትላለች ።
«በጀርመን ከ1ሺ 700 ዓመታት በላይ ኖረናል። ለእኔ የሁዲዎች ሁሌም የጀርመን አካል ናቸው ነውየፈረንሳይ የሁዲዎች ሥጋት የምለው። ብዙዎች አሁን በጀርመን መጻኤ እድል ይኑር አይኑራቸው እያሰቡ ነው። ከነዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላ ያ ሁሉ ከደረሰብን በኋላ፣ እንደዚህ ዓይነት ነገሮች መድረሳቸው ያሳዝናል።»

የሀማስ ሚሊሽያዎች መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጋዛ ሰርጥ ተነስተው እስራኤል ውስጥ በፈጸሙት ጥቃት ቢያንስ 1400 ሰዎች ሞተዋል ሲሉ የእስራኤል ባለስልጣናት ተናግረዋል። አብዛኛዎቹም ሰላማዊ መሆናቸውን ገልጸዋል። ጋዛ የሚገኘው የሀማስ የጤና ሚኒስቴር ደግሞ ከጥቃቱ በኋላ እስራኤል በወሰደው የአጸፋ እርምጃ ከ5700 በላይ አብዛኛዎቹ ሰላማዊ የሆኑ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን አስታውቋል።የእስራኤልና የሀማስ ጦርነት በርካታ ሰላማዊ ህዝብ መጨረሱ በሌላው ዓለም የሚገኙ የተለያዩ ወገኖችን አስቆጥቷል። 

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ