1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን አንድነት ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 14 2016

ምዕራብ እና ምሥራቅ በሚል ለሁለት ተከፍሎ የነበረው ጀርመን የተዋሀደበት 33ተኛ ዓመት ትናንት ምሽት አዲስ አበባ በሚገኘው ሰፊው የጀርመን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተከበረ ። የጀርመን ውኅደት ቀን ይፋዊ በዓል ጀርመን ውስጥ በየዓመቱ በጎርጎሪዮሱ አቆጣጠር (October 3) ይከበራል ።

https://p.dw.com/p/4Y1Ox
Äthiopien Addis Abeba | Feier Wiedervereinigung in Deutschen Botschaft
ምስል Solomon Muche/DW

33ተኛ ዓመቱ ጀርመን ውስጥ ከ3 ሳምንት በፊት ተከብሯል

ምዕራብ እና ምሥራቅ በሚል ለሁለት ተከፍሎ የነበረው ጀርመን የተዋሀደበት 33ተኛ ዓመት ትናንት ምሽት አዲስ አበባ በሚገኘው ሰፊው የጀርመን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተከበረ ። የጀርመን ውኅደት ቀን ይፋዊ በዓል ጀርመን ውስጥ በየዓመቱ በጎርጎሪዮሱ አቆጣጠር (October 3) ይከበራል ። ዘንድሮ ጀርመን ውስጥ መስከረም 22 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ተከብሯል ። አዲስ አበባ ጀርመን ኤምባሲ ውስጥ ትናንት ተከናውኖ በነበረው ሥነ ሥርዓት ላይ አራት ሚኒስትሮችን ጨምሮ ሚኒስትር ድዔታዎች ፣ የተለያዩ ሃገራት አምባሳደሮች፣ የጀርመን ድርጅቶች ሠራተኞች እና በርከት ያሉ ሌሎች እንግዶች ታድመዋል ።

የጀርመን ዳግም ውህደትበምስራቅ ጀርመን የሰላም አብዮት አቀጣጣይነት ምክንያት የተሳካ ነው ያሉት በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ሽቴፈን ዐውር ለጀርመን ውህደት የተወሰደው የሰላም ጥረት በጀርመን ታሪክ ውስጥ አስደሳች ከሆኑት ሁነኛ ክስተቶች ዋነኛው ነበር ሲሉ ትናንት ምሽት ኤምባሲው ውስጥ በተከበረው 33 ኛው የጀርመን ውሕደት ቀን ላይ ገልፀዋል።

ይህ ሲባል ግን ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ አልነበረም ያሉት አምባሳደር ዐውር ለዓመታት በጠላትነት ይተያዩ በነበሩ መንግሥታት ሥር የነበረን ማህበረሰብ እንደገና ማዋሃድ አንዱ ፈታኝ የታሪኩ ሂደት እንደነበር አስታውሰዋል። የምስራቅ ጀርመንን በመቶ ሺህ የሚቆጠር የጦር ሰራዊት በጥቂት ወራት ውስጥ እንዲበተን ማድረግም ማዋሃድ ሌላው የወቅቱ ሀገራቸው ያለፈበት ፈታኝ ገዳይ እንደነበርም ቃኝተዋል።

ጀርመን የተዋሀደበት 33ተኛ ዓመት ትናንት ምሽት አዲስ አበባ በሚገኘው ሰፊው የጀርመን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተከብሯል
ምዕራብ እና ምሥራቅ በሚል ለሁለት ተከፍሎ የነበረው ጀርመን የተዋሀደበት 33ተኛ ዓመት ትናንት ምሽት አዲስ አበባ በሚገኘው ሰፊው የጀርመን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተከብሯልምስል Solomon Muche/DW

የኢትዮጵያመንግሥት ከሕወኃት ጋር ያደረገው የተኩስ ማቆም ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበርና የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ለመተግበር የሚደረገውን ጥረት ሀገራቸው እንደሚደግፍ የገለፁት አምባሳደሩ «በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ከኢትዮጵያ ወዳጆቻችን ጎን እንቆማለን ብለዋል። አክለውም ታሪካችንን መነሻ በማድረግ የኢኮኖሚ ግንባታችንን ፣ በውህደቱ ዋዜማ የነበረን ትጥቅ የማስፈታት ልምዳችንን እና ዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብን በመፍጠር ረገድ ያለንም ልምዳችንን ለማጋራት በኢትዮጵያ በኩል ፍላጎት ካለ ዝግጁ ነን» ብለዋል።

ጀርመኖቹ የፖለቲካ ልዩነቶቻቸውን እንዴት መፍታት እንደቻሉ፣ ሁለት የተለያዩ ሥርዓቶች ዲሞክራሲያዊ እና የበልፀገ ማህበረሰብ ለመገንባት እንዴት ወደ አንድ እንደመጡ ያሳዩበት እና ብዙ ልንማርበት የምንችለው ነው ሲሉ የጀርመንን ውሕደት የገለፁት የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ የበርሊን ግንብ የፈረሰበትን ታሪክ እና ያስገኘውን ውጤት አሞግሰዋል።

ለስኬታማ የአገር እንድነት የሽግግር ሥራ ለሰሩት ጀርመኖች እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እወዳለሁ ሲሉም ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

ጀርመን የተዋሀደበት 33ተኛ ዓመት ትናንት አዲስ አበባ በሚገኘው ሰፊው የጀርመን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተከብሯል ።
ጀርመን የተዋሀደበት 33ተኛ ዓመት ትናንት ምሽት አዲስ አበባ በሚገኘው ሰፊው የጀርመን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተከብሯል ። አራት የኢትዮጵያ ሚኒስትሮች ፣ ሁለት ሚኒስትር ድዔታዎች፣ የተለያዩ ሀገራት አምበሳደሮች የልዩ ልዩ የጀርመን ድርጅቶች ሠራተኞች እና በርከት ያሉ ሌሎች እንግዶችም ታድመዋልምስል Solomon Muche/DW

በኢትዮጵያ እና በጀርመን መካከል በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በንግድ ጠንካራ ግንኙነት መኖሩን የገለፁት አምባሳደር ሽቴፈን ዐውር ከዚህ በላቀ የንግድና የኢኮኖሚ ትስስሩ እንዲጠናከር ምቹ ሁኔታን እንደሚሹ ገልፀዋል።

የጀርመን ውህደት 33ኛ ዓመት በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው የጀርመን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ትናንት ምሽት ላቅ ባለ ሥነ ሥርዓት ሲከበር አራት የኢትዮጵያ ሚኒስትሮች ፣ ሁለት ሚኒስትር ድዔታዎች፣ የተለያዩ ሀገራት አምበሳደሮች የልዩ ልዩ የጀርመን ድርጅቶች ሠራተኞች እና በርከት ያሉ ሌሎች እንግዶችም ታድመዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ