የጀርመን መንግስት ለሳዑዲ አረቢያ ጦር መሳሪያ እንዲሸጥ መወሰኑ
ሐሙስ፣ ጥር 2 2016ማስታወቂያ
ጀርመን ዳግም ለሳዑዲ አረቢያ ጦር መሳሪያ እንድትሸጥ የሐገሪቱ መንግስት መወሰኑ ትናንት በይፋ ተነግሯል።የጀርመን የጦር መሳሪያዎች ለሳዑዲ አረቢያ እንዳትሸጡ የሐገሪቱ መንግስት ከ5 ዓመት በፊት ወስኖ ነበር።ያኔ ጦር መሳሪያ እንዳይሸጥ የጀርመን መንግስት የወሰነዉ የሳዑዲ አረቢያ ነገስታት እዉቁን ሳዑዲ አረቢያዊ ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾጂን አስገድለዋል በሚል ጥርጣሬና የሰብአዊ መብት ይረግጣሉ፣ በየመኑ ጦርነት ሰላማዊ ሰዎችን አስገድለዋል በሚል ምክንያት ነበር።አሁን በሥልጣን ላይ ያለዉ የጀርመን ተጣማሪ መንግስት 150 ኢሪስ ቲ የተባሉ የዓየር-ላየር ተመዝግዛጊ ሚሳዬሎችና 48 ተዋጊ ጄቶች ለሳዑዲ አረቢያ እንዲሸጥ ወስኗል።ያለፈዉ ዉሳኔ የተሻረበት ምክንያት እያነጋገረ ነዉ።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ