1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የነሐሴ 15 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የስፖርት ዘገባ

ሰኞ፣ ነሐሴ 15 2015

በቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ፉክክር መክፈቻ ኢትዮጵያውያት አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመያዝ ሜዳሊያዎቹን ተቆጣጥረዋል ። የአትሌት ሲፈን ሐሰን በውድድሩ ማብቂያ ሚዛኗን ስታ መውደቋም መነጋገሪያ ነበር ። የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በስፖርቱ የገጽታ ግንባታ ላይ ቢገኝም፤ በመቶዎች የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን ዓምና በግፍ ጨፍጭፏል ተብሏል።

https://p.dw.com/p/4VPx9
በቡዳፔስት ውድድር ድል የተቀዳጁት ኢትዮጵያውያት አትሌቶች
በቅዳሜው ነሐሴ 13 እስከ 21 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የዐስር ሺህ ሜትር የሴቶች የሩጫ ፉክክር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ ርቀቱን በ31 ደቂቃ ከ27.18 ሰከንድ በማጠናቀቅ በአንደኛነት አሸንፋለች ። ኢትዮጵያውያቱ አትሌቶች ለተሰንበት ግደይ እና እጅጋየሁ ታዬም የሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ የውድድሩ የበላይ ሆነው ገነዋል ።ምስል Antonin Thuillier/AFP

ሣምንታዊ የስፖርት ዘገባ

በ19ኛው የቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ፉክክር መክፈቻ ቅዳሜ ዕለት ኢትዮጵያውያት አትሌቶች ዓለምን ባስደመመ መልኩ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ በመያዝ ሜዳሊያዎቹን በመላ ተቆጣጥረዋል ። የኔዘርላንዷ ሲፈን ሐሰን በውድድሩ ማብቂያ ላይ ሚዛኗን ስታ መውደቋም መነጋገሪያ ነበር ።  የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት በስፖርቱ ዘርፍ ስመጥር የእግር ኳስ ተጫዋቾችን ወደ ሳዑዲ ፕሮፌሽናል በማስፈረም የገጽታ ግንባታ ላይ ቢገኝም፤ በመቶዎች የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን የመን ድንበር ላይ በግፍ ጨፍጭፏል በሚል እየተከሰሰ ነው ። የዕለቱ ዐበይት የስፖርት ዘገባዎቻችን ናቸው። የእንግሊዝ ፕሬሚየር እና የጀርመን ቡንደስሊጋ ውጤቶችንም አጠር አድርገን እናቀርባለን ። 

አትሌቲክስ

በ19ኛው የቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ፉክክር መክፈቻ ቅዳሜ ዕለት ኢትዮጵያውያት አትሌቶች እጅግ አሸብራቂ ድል ተቀዳጅተዋል ። በተለይ ለሆላንድ ተሰልፋ የምትሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፋን ሐሰን በዚሁ የዐስር ሺህ ሜትር ርቀት ለረዥም ጊዜያት የነበራትን የበላይነት የተነጠቀችበት ፉክክር መሆኑ ብዙዎቹን የስፖርት አፍቃሪዎች አስፈንጥዟል ።

የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊው የዩናይትድ ስቴትሱ ኖሃ ሊሌስ ከፊት
የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊው የዩናይትድ ስቴትሱ ኖሃ ሊሌስ፤ የብር ሜዳሊያ አሸናፊው የቦትስዋናው አትሌት ሌጺሌ ቴቦጎ እንዲሁም የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤሩ የብሪታኒያው ዛርኔል ሁግስ በውድድሩ ፍጻሜ ወቅት ።ምስል Jewel Samad/AFP

በቅዳሜው ነሐሴ 13 እስከ 21 ቀን፣ 2015 ዓ.ም የዐስር ሺህ ሜትር የሴቶች የሩጫ ፉክክር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ ርቀቱን በ31 ደቂቃ ከ27.18 ሰከንድ በማጠናቀቅ በአንደኛነት አሸንፋለች ። ኢትዮጵያውያቱ አትሌቶች ለተሰንበት ግደይ እና እጅጋየሁ ታዬም የሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ የውድድሩ የበላይ ሆነው ገነዋል ። ከአትሌት ጉዳፍ ጋር ብርቱ ፉክክር ስታደርግ የነበረችው ኔዘርላንዳዊቷ አትሌት ሲፋን ሐሰን ውድድሩ ሊጠናቀቅ ጥቂት ሜትሮች ሲቀረው ወድቃለች ። ያገኘው ውጤትም ዐሥራ አንደኛ ነው ።

በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮ ስፖርት መርኃ ግብር ዋና አዘጋጅ ምስጋናው ታደሰ የቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ፉክክር  እየተከታተለ ነው ። አትሌቶቹ ገና ኢትዮጵያ በልምምድ ላይ ሳሉም በቅርበት ክትትል ሲያደርግ ነበር። የኢትዮጵያውያቱ አመርቂ ድልን ዓለም እንዴት እንደዘገበው እንዲህ ቅኝት ያደርግልናል ።

በወንዶቹ በ10,000 ሜትር በተካሔደ ውድድር  የተገኘው ውጤትስ እንዴት ይታያል? የዩጋንዳው አትሌት ጆሽዋ ቼፕቴጊ በ27 ደቂቃ ከ51 ሰከንድ 42 ማይክሮ ሰከንድ በመሮጥ በአንደኝነት አጠናቋል ። ኬንያዊው ዳንኤል ሲምዩ 2ኛ ደረጃ ሲያገኝ ሰለሞን ባረጋ እና በሪሁ አረጋዊ 3ኛ እና 4ኛ በመሆን ተከታትለው ገብተዋል። በተለይ የሰለሞንን አጨራረስ እንዴት ዐየኸው?

በአጠቃላይ ቅዳሜ ነሐሴ 13 ጀምሮ እስከ ነሐሴ 21 ቀን፣ 2015 ዓ.ም ድረስ   በሚካሄደው የቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ፉክክር ከኢትዮጵያውያን አትሌቶች ምን እንጠብቅ?

የቦትስዋናው አትሌት ሌጺሌ ቴቦጎ በአምስት ማይክሮ ሰከንድ ተበልጦ የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ሆኖ ለአፍሪቃ ታሪክ ሠርቷል ።
በመቶ ሜትር የሩጫ ፉክክር አፍሪቃ ወደ ሜዳሊያ ሰንጠረዥ ብቅ ማለቷ ሌላ አመርቂ ዜና ነው ። የቦትስዋናው አትሌት ሌጺሌ ቴቦጎ ከአሜሪካዊው ተፎካካሪ በአምስት ማይክሮ ሰከንድ ተበልጦ የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ሆኖ ለአፍሪቃ ታሪክ ሠርቷል ። የነሐስ ሜዳሊያው ለብሪታኒያው ዛርኔል ሁግስ ነው የተሰጠው ።ምስል Naoki Morita/AFLOSPORT/IMAGO

ከዛው ከቡዳፔስት ውድድር ሳንወጣ፦ በመቶ ሜትር የሩጫ ፉክክር አፍሪቃ ወደ ሜዳሊያ ሰንጠረዥ ብቅ ማለቷ ሌላ አመርቂ ዜና ነው ። የዩናይትድ ስቴትስu ኖሃ ሊሌስ 9 ደቂቃ ከ83 ማይክሮ ሰከንድ አሸንፎ ወርቅ ባጠለቀበት ፉክክር የቦትስዋናው አትሌት ሌጺሌ ቴቦጎ በአምስት ማይክሮ ሰከንድ ተበልጦ የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ሆኖ ለአፍሪቃ ታሪክ ሠርቷል ። የነሐስ ሜዳሊያው ለብሪታኒያው ዛርኔል ሁግስ ነው የተሰጠው ።

እግር ኳስ

የዓለማችን እጅግ ዝነኛ የእግር ኳስ ተጨዋቾችን በሀገሯ ለማጫወት በማስፈረም ላይ የምትገኘው ሣዑዲ ዓረቢያ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ክስ እየተሰነዘረባት ነው ። እግር ኳስንጨምሮ ለስፖርቱ በቢሊዮናት የሚቆጠሩ ዶላሮችን የምታፈሰው ሳዑዲ ዓረቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ደም በየመን ድንበር በኩል በከንቱ በማፍሰስ ገድላለች ሲል ሒውማን ራይትስ ዎች ዛሬ ባሰራጨው ዘገባው ገልጿል ።

«የሳዑዲ ባለሥልጣናት በዚህ ሩቅ ድንበር ከሌላው ዓለም ዕይታ ውጪ ሆነው በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች እና ተገን ጠያቂዎችን ገድለዋል» ብለዋል የሒውማን ራይትስ ዎች የፍልሰተኞች እና ስደተኞች ጉዳይ አጥኚ ናዲያ ሐርድማን ። «የሳዑዲ ገጽታን ለመገንባት በሚል ለፕሮፌሽናል የጎልፍ እና የእግር ኳስ ቡድኖች እንዲሁም ለታላላቅ የመዝናኛ ዝግጅቶች በቢሊዮን ዶላሮች ማፍሰስ ትኩረታችን ከዚህ እጅግ ከከፋው ወንጀል ሊያናጥበው አይገባም» ሲሉም አስጠንቅቀዋል ።

የነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅትየሳዑዲ ዓረቢያ እጅግ የናጠጡ የእግር ኳስ ቡድኖች የዓለማችን ምርጥ የእግር ኳስ ተጨዋቾችን ወደ ሀገራቸው እየጠሩ ማስፈረማቸው የሰሞኑ ዐቢይ የስፖርት ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል ።

የፖርቹጋሉ ምርጥ አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በሳዑዲ ፕሮ ሊግ
በመጀመሪያ የፖርቹጋሉ ምርጥ አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶን ከእነ ቤተሰቡ ማስመጣት የተሳካላት ሳዑዲ ዓረቢያ፦ አሁን ደግሞ የብራዚሉ ምርጥ ኔይማርን ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ፕሮፊ ሊጋ እንዲቀይር ማስቻሏ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል ።ምስል Mohammed Said/AA/picture alliance

በመጀመሪያ የፖርቹጋሉ ምርጥ አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶን ከእነ ቤተሰቡ ማስመጣት የተሳካላት ሳዑዲ ዓረቢያ፦ አሁን ደግሞ የብራዚሉ ምርጥ ኔይማርን ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ፕሮፊ ሊጋ እንዲቀይር ማስቻሏ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል ። እጅግ ዳጎስ ያለው የዝውውር ክፍያ የተጨዋቾቹን ካዝና መሙላቱ አይቀርም፤ በዋናነት ግን የሳዑዲ ዓረቢያ ገጽታን በመገንባቱ ረገድ ሚናው ከፍተኛ እንደሆነ ይነገራል ።

ቀደም ሲል እነ ቤንዜማ፤ ሳዲዮ ማኔ፤ ንጎሎ ካንቴ፤ ሩበን ኔቬስ፤ ሮቤርቶ ፊርሚኖ እና ጆርዳን ሔንደርሰንም ተጠቃሾች ናቸው ። ከሞራል አንጻር ተጨዋቾቹ በሳዑዲ ዓረቢያም ፕሮፌሽናል ሊግም ተጫወቱ የሳዑዲ በነዳጅ የናጠጡ ቱጃሮች በሚዘውሯቸው የእንግሊዝ በርካታ ቡድኖች የሚቀይረው ነገር ያለ አይመስልም ። በሳዑዲ ኮማንዶች እጅግ በአሰቃቂ የግፍ መንገድ ስለተገደለው ጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊም የሚያወራ የለም ። ይልቁንስ የሳዑዲ መንግስት በግፍ ኢትዮጵያውያኑን የጨፈጨፉ የድንበር ጠባቂዎቹን ጨምሮ ወታደሮቹ የታጠቋቸውን ዘመናዊ ጦር መሣሪያዎች ያገኘው ከአውሮጳውያን ዘንድ መሆኑንም የአውሮጳ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ሲናገሩ መደመጡ ያስደምማል ። 

እጅግ ከፍተኛ ቁጥር በተመዘገበበትት እና 76,000 ታዳሚዎች በተገኙበት የዓለም የሴቶች እግር ኳስ የፍጻሜ ፍልሚያ ስፔን እንግሊዝን 1 ለ0 ድል አድርጋ ዋንጫውን ወስዳለች ። ባለፈው ሳምንት በሱፐር ካፕ ዋንጫ ስፔን በሴቪያ ተወክላ ለፍጻሜው የእንግሊዙ ማንቸስተር ሲቲን ብትገጥምም የማታ ማታ የሽንፈትን ጽዋ ቀምሳለች ። በትናንቱ የፍጻሜ ግጥሚያ ግን የስፔን የሴቶች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በወንዶቹ የሴቪያ ቡድን የደረሰበትን ሽንፈት ተበቅሏል ።

የሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅትበትናንቱ የፍጻሜ ግጥሚያ፦ ስፔን በኦልጋ ካርሞና 29ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረችው ብቸኛ ግብ ነው ዋንጫውን ማንሳት የቻለችው ። ኦልጋ ከትናንቱ የፍጻሜ ግጥሚያ በኋላ ደስታዋን ብዙም ማጣጣም አልቻለችም ። የአባቷን ሞት መረዳቷን የስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዛሬ ዘግቧል ። የዘንድሮውን ውድድር በጋራ ያዘጋጁት አውስትራሊያ እና ኒው ዚላንድ ናቸው ። ቀጣዩን ውድድር አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጋራ ያሰናዳሉ ።

ስፔን እንግሊዝን 1 ለ0 ድል አድርጋ ዋንጫውን ወስዳለች ።
እጅግ ከፍተኛ ቁጥር በተመዘገበበትት እና 76,000 ታዳሚዎች በተገኙበት የዓለም የሴቶች እግር ኳስ የፍጻሜ ፍልሚያ ስፔን እንግሊዝን 1 ለ0 ድል አድርጋ ዋንጫውን ወስዳለች ። ምስል Catherine Ivill/Getty Images

ፕሬሚየር ሊግ

በእንግሊዝ ፕሬሚየር ሊግ፦ ክሪስታል ፓላስ እና አርሰናል ዛሬ ማታ ሁለተኛ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ ። ሁለቱም በዘንድሮ የፕሬሚየር ሊግ የመጀመሪያ ግጥሚያ ተጋጣሚዎቻቸውን ማሸነፍ የቻሉ ናቸው ።

በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በነበሩ ግጥሚያዎች፦ አንድ ተጨዋቹ በቀይ ካርድ ከሜዳ የተሰናበተበት ዌስትሀም ቸልሲን 3 ለ1 አሸንፏል ።   አስቶን ቪላ ኤቨርተንን 4 ለ0 ሲያደባይ ፤ ቅዳሜ ዕለት ማንቸስተር ሲቲ ኒውካስል ዩናይትድን 1 ለ0 አሸንፏል ። ማንቸስተር ዩናይትድ በቶትንሀም ሜዳ የ2 ለ0 ሽንፈት አስተናግዷል ። ብሬንትፎርድ ፉልሀምን በገዛ ሜዳው 3 ለ0 ኩም ሲያደርግ፤ ዎልቨርሀምፕተን በሜዳው የ4 ለ1 ብርቱ ሽንፈት በብራይተን ገጥሞታል ።  አሌክሲስ ማክ አሊስተር በ58ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ የተቀጣበት ሊቨርፑል ቦርመስን 3 ለ1 አሸንፏል ። ሊቨርፑል ማካሊስተር በቀይ ካርድ መሰናበቱ ተገቢ አይደለም በሚል ማመልከቻ እንደሚያስገባ ዛሬ ይፋ አድርጓል ።

 ቅዳሜ ይለት ቦሩስያ ዶርትሙንድኮሎኝን 1 ለ0 አሸንፏል ።
ቅዳሜ ይለት ቦሩስያ ዶርትሙንድ ኮሎኝን ሲግናል ኢዱና ፓርክ ስታዲየም ውስጥ 1 ለ0 አሸንፏል ። የዶርትሙንድ ዶኔይል ማሌን ግብ ከተቆጠረ በኋላ ደስታውን ሲገልጽ ። ምስል Alex Gottschalk/DeFodi Images/picture alliance

ቡንደስ ሊጋ

የሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ/ም የስፖርት ዝግጅትበጀርመን ቡንደስሊጋ አይንትራኅት ፍራንክፉርት ዳርምሽታድትን 1 ለ0 አሸንፏል ። ማይንትስ በዑኒዮን ቤርሊን የ4 ለ1 ሰፊ ሽንፈት ገጥሞታል ። ቅዳሜ ይለት ቦሩስያ ዶርትሙንድኮሎኝን 1 ለ0 አሸንፏል ።  ላይፕትሲሽ በባዬር ሌቨርኩሰን የ3 ለ2 ሽንፈት ገጥሞታል ። ሽቱትጋርት ቦሁምን 5 ለ0 የግብ ጎተራ አድርጎታል ። ፍራይቡርግ ሆፈንሀይምን 2 ለ1 ፤ እንዲሁም ቮልፍስቡርግ ሀይደንሀይምን 2 ለ0 አሸንፈዋል ። አውግስቡርግ ከቦሩስያ ሞይንሽንግላድባኅ ጋር አራት እኩል ነጥብ ሲጋራ፤ ባዬርን ሙይንሽን ቬርደር ብሬመንን በሜዳው  4 ለ0 ድል አድርጓል ።  

የሜዳ ቴኒስ፦

በዌምብሌ ሽንፈት የገጠመው ኖቫክ ጄኮቪች ካርሎስ አልካራዛን በሲንሲናቲ ፍጻሜ በማሸነፍ ሽንፈቱን ተበቅሏል ። በፍጻሜው ኖቫክ ጄኮቪች ያሸነፈው5-7 7-6 (9-7) 7-6 (7-4) ነው ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሠ