የባሻ አሸብር የጀርመን ተሞክሮ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 15 2016« ግጥም ለኔ ገጠመኜን፤ ሃዘን ደስታዬን ብሎም ህይወቴን ከልቤ አዉጥቼ የምተነፍስበት መሳርያዬ ነዉ። አንዳንድ ሰዉ የመናገር ተሰጥኦ አለዉ ። እኔ ግን የመናገር ተሰጥኦ የለኝም። ሃሳቤን በግጥም ስገልጽ የበለጠ የልቤን መጻፍ እና መናገር እችላለሁ» ሲል የሚናገረዉ በቅርቡ ለአንባብያን አምስተኛ የግጥም መድብሉን ያቀረበዉ ገጣሚ ሰለሞን ሞገስ ወልደየስ ወይም በቤት መጠርያ ስሙ ፋሲል ይባላል።
ገጣሚ ሰለሞን በጀርመን ባቫርያ ግዛት ዉስጥ መኖር ከጀመረ ወደ ስድስት ዓመት ገደማ ሆኖታል። ቤተሰብ የቅርብ ጓደኞቹ ሁሉ ፋሲል ሲሉ እንደሚጠሩት ነግሮናል። ገጣሚ ሰለሞን ሞገስ በቅርቡ በስደት ዓለም የመጀመርያ ያለዉን የግጥም መድብል ለአንባብያን አቅርቦ ተወድሶለታል። የመድብሉ ስያሜ «ባሻ አሸብር በጀርመን» ይላል። ይሁንና ገጣሚ ሰለሞን በስደት ዓለም የመጀመርያ ግጥብ መድብሌ ነዉ፤ ይበል እንጂ ከስድስት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ሳለ አራት የግጥም መድብሎችን አሳትሞ ለአንባብያን አቅርቧል። ከዚህ ቀደም ያሳተማቸዉ መድብሎቹ1,« » 2,« »3,« » እንዲሁም 4ኛዉ መድብሉ « » የሚል ስያሜን ይዟል። ታዋቂዉ የጥበብ ሰው ሃብታሙ ማሞ
ወደ ጀርመን ከመጣ እና በቅርቡ ለአንባብያን ያቀረበዉ የግጥም መጽሐፍህ «ባሻ አሸብር በጀርመን» የሚል ስያሜን ሰቶታል። በመድብሉ ሽፋን ላይ አንድ ጠና ያሉ ሰዉ፤ ኩታ ጋቢ ደርበዉ፤ ኮፍያ አጥልቀዉ፤ ከዘራ ይዘዉ፤ በፈረንጆቹ መሐል፤ በጀርመን ጎዳና ላይ ሲጓዙ፤ ግራ ቀኙን ሲያዩ፤ ይታያል። እና ባሻ አሸብር ማናቸዉ?የስደተኛዉ ማስታወሻ
«ብዙ የሥነ-ጽሑፍ ቤተሰቦች እና ወዳጆች እንደሚያዉቁት፤ ከታላላቆቹ የኢትዮጵያ የሥነ-ጽሑፍ ደራስያን እና ፀሐፊ ተዉኔቶች መካከል፤ አንዱ ጋሽ መንግሥቱ ለማ ወይም አብዬ መንግሥቱ ለማ ናቸዉ። አብዬ መንግሥቱ በዘመናቸዉ፤ በኢትዮጵያዉያን ዘንድ በጣም ታዋቂ እና ተወዳጅ የሆነ «ባሻ አሸብር በአሜሪካ» የሚል የሚያስቅ ግጥምን መጻፋቸዉ ይታወቃል። ባሻ አሸብር የተባሉት ገፀ ባህሪ ወደ አሜሪካ ለጉብኝት ሄደዉ ሳለ የገጠማቸዉን ሁኔታ ገጣሚ መንግሥቱ ለማ አስቂኝ በሆነ መንገድ ገጥመዋል። ይህ ግጥም መንግሥቱ ለማ እራሳቸዉ ያነበቡት ዩቲ ዮብ ዉስጥ ይገኛል። እኔም ባሻ አሸብር የተባሉትን ገፀ ባህሪ ወደ ጀርመን አምጥቼ የገጠመኝን ነገር ለገፀ-ባህሪዉ አላብሼ በግጥም አቅርቤዋለሁ። ይህን የግጥም እዚህ ጀርመን ዉስጥ በአንድ የኢትዮጵያ መድረክ ላይ አቅርቤዉ በጣም ስለተወደደም የመድብሉን ስም« ባሻ አሸብር በጀርመን» የሚል ስያሜን ሰጥቸዋለሁ።
ይህ የኔ የግል ተሞክሮ ነዉ፤ ሲል ገጣሚ ሰለሞን ሞገስ አጫዉቶናል። እንደ ገጣሚ ሰለሞን ሞገስ አንድ ኢትዮጵያዊ በዉጭ አገር እየኖረ ሥነ-ግጥምን እንዲሁም ሥነ-ጽሑፍን ለአንባብያን ብሎ አዘጋጅቶ በመጽሐፍ መልክ አሳትሞ ማቅረብ ከባድ ነዉ። በአንደኛ ደረጃ ከባህሉ ፤ ከቋንቋዉ በመራቃችን ነገሩን ከባድ ፈታኝ ያደርገዋል። በሁለተኛ ደረጃ በእርጋታ ቁጭ ተብሎ ጽፎ ለማሳተም በቂ ጊዜ ባለመኖሩ ነዉ ሲል ተናግሯል። ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ
ገጣሚ ሰለሞን ሞገስ በጀርመን ሲኖር ስድስት ዓመታት ገደማ ሆኖታል። ለዓመታት በጀርመን ገጠር ቼክ ሪፐብሊክ እና ጀርመን ድንበር ላይ መኖሩን ተናግሯል። አሁን ደግሞ በባቫርያ ግዛት መዲና በሆነችዉ በሙኒክ ከተማ እየኖረ ነዉ። በሙኒክ እና አካባቢዋ የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ በአብዛኛዉ ከስራ ዉጭ የግሉን ኑሮ የሚኖር መሆኑን እና አንዳንድ ጊዜ ብቻ ለአዲስ ዓመት፤ እንዲሁም ሌሎች መሰባሰብያ መድረክ ሲገኝ ተሰባስቦ በሙዚቃ ዘና እንደሚል፤ ባህላዊ ቡናንም በጋራ እንደሚጠጣ ገጣሚ ሰለሞን ተናግሯል። ይሁንና አብዛኛዉ ሰዉ በግሉ ኖሮ ላይ ብቻ አተኩሮ እንደሚኖር ነዉ የነገረን። ሃገሬ የጥበብ ምሽት
ገጣሚ ሰለሞን ሞገስ በሃገር ቤት ሳለ በተለያዩ ጋዜጦች ላይ ሰርቷል፤ የመድረክ አስተዋዋቂም ነበር፤ «ቆራልየዉ» የተሰኘዉን ሙዚቃን ጨምሮ ሌሎች የሙዚቃ ግጥሞችንም ደርሷል።
በጀርመን ሙኒክ ከተማ ነዋሪ የሆነዉ ገጣሚ ሰለሞን ሞገስ «ባሻ አሸብር» የተሰኘዉ የግጥም መድብሉ ለአንባብያን እንዲበቃ ለረዱት ኢትዮጵያዉያን ሁሉ ምስጋናን አቅርቧል። ገጣሚ ሰለሞን ሞገስ ለሰጠን ቃለ ምልልስ በዶቼ ቬለ ስም እያመሰገንን፤ ሙሉ ዝግጅቱን የድምጽ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ