1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ታዋቂዉ የጥበብ ሰው ሃብታሙ ማሞ

እሑድ፣ ሚያዝያ 23 2014

ሜድ ኢን ቻይና፣ ታሰጨርሺኛለሽ፣ እሾሃማ ፍቅር፣ ላገባ ነው የሚሉ ፊልሞቸ በአብዛኛው የጥበብ ታዳሚ የሚታወቁ ናቸው። በእነዚህና ሌሎች ሰራዎቸ በደራሲነት ዳይሬክተርነተና በፊልም ሰሪነት እንዲሁም በመጽሐፍና ግጥም ደራሲነት እያገለገለ ነው አርቲስት ሃብታሙ ማሞ

https://p.dw.com/p/4AbJ4
Habtamu Mamo, äthiopischer Schauspieler & Regisseur
ምስል Bright Studio

ታዋቂዉ የጥበብ ሰው ሃብታሙ ማሞ


ሜድ ኢን ቻይና፣ ታሰጨርሺኛለሽ፣ እሾሃማ ፍቅር፣ ላገባ ነው የሚሉ ፊልሞቸ በአብዛኛው የጥበብ ታዳሚ የሚታወቁ ናቸው። በእነዚህና ሌሎች ሰራዎቸ በደራሲነት ዳይሬክተርነተና በፊልም ሰሪነት እንዲሁም በመጽሐፍና ግጥም ደራሲነት እያገለገለ ያለው የጥበብ ባለሙያ እንግዳችን ነው። 

የብዙ የኪነ-ጥበብ ሰዎቸ መፍለቂያ በሆነው መርካቶ ሰባተኛ ተወልዶ ያደገው ደራሲ፣ ዳይርክተርና ተዋናይ ሃበታሙ ማሞ የታላላቆቹን የጥበብ ሰራዎችን እያየ ወደ ጥበብ ዓለም እንዳዘነበለ ነግሮናል። ዘርፈ ብዙው የጥበብ ባለሙያ ሃብታሙ ማሞ በተለይ እሱ በተወነባቸው ፊልሞቸ የተሰጠውን ገጸ-ባሕሪ መሰሎ ሳይሆን ሆኖ እንደሚተውን የጥበብ አጋሮቹ ይገልሉ። ከትወና ሌላ በዳይርክተርነት፣ መጽሐፍ ደራሲነትና ፕሮዲዩሰርነተ እንዲሁም ግጥም በመጻፍ ይታወቃል። እስካሁን ካበረከታቸው የጥበብ ውጤቶቸ ዋና ዋናዎቹን እንዲህ አወጋን።
የጥበብን ጥሪ ተቀብሎ ለህብረተሰቡ የሚያበረከተው አገልግሎት ከምንም በለይ እንደሚያረካው በዚሀም ደሰተኛ እንደሆነ ገልጾልናል ዘርፈ በዙው የጥበብ ሰው ሃበታሙ ማሞ። 

በፊልሞቹና በድርሰት ሰራዎቹ ከተደራሰኢያን የሚሰጡት ጥልቅና ገንቢ አስተያየቶች አሁን ለደረሰበት ደረጃ አወንታዊ አስተዋፆ እንዳደረጉለት የሚናገረው አርቲስት ሃብታሙ በግል ህይወቱም ደስተኛ፤ ላመነበት እስከ መጨረሻው አስፈላጊውን መስዋእት የሚከፍልና እማይጨነቅ መሆኑን ነግሮናል።ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማድመጫን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን። 
 

Habtamu Mamo, äthiopischer Schauspieler & Regisseur
ምስል Film production
Habtamu Mamo, äthiopischer Schauspieler & Regisseur
ምስል Film production


ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር 
አዜብ ታደሰ