1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሂትለር የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ 100ኛ ዓመት

ማክሰኞ፣ ኅዳር 4 2016

የሂትለርደጋፊዎች ፣በአዳራሹ የነበሩትን ባለሥልጣናት በአንድ ክፍል ሰብስበው አሰሩ።ሂትለር ፣በርሊን ያለው መንግሥት ከስራ እንደተወገደ፣ በሚመጡት ቀናትም የባቫርያ ግዛት ዋና ከተማ ሙኒክን ነጻ ካወጡ በኋላ ወደ በርሊን እንደሚሄዱ ተናገረ። ያኔም የአንደኛው የዓለም ጦርነት የጀርመን ጀግና ጀነራል ሉድንዶርፍ ከሂትለር ጋር መቀላቀላቸውን አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/4YlMB
Deutschland 100. Jahrestag des gescheiterten Hitler-Putschs vom 9. November 1923
ምስል United Archives/picture alliance

የሂትለር የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ 100ኛ ዓመት


 

አዶልፍ ሂትለር የናዚ ጀርመን መሪ ከመሆኑ አስቀድሞ ፣በጎርጎሮሳዊው ህዳር 8 እና 9 ፣ 1923 የዛሬ መቶ ዓመት በደቡባዊ ጀርመንዋ ፌደራዊ ግዛት በባቫሪያ ከደጋፊዎቹ ጋር ያካሄደው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የጀርመንን ታሪክ የቀየረ ክስተት ነው። መፈንቅለ መንግሥት ቢከሽፍም ከአስር ዓመት በኋላ ሂትለር የሀገሪቱ ከፍተኛው የስልጣን ማማ ላይ እንዲደርስ የመጀመሪያው እርምጃ ሆኗል። ሂትለር ያኔ የቫይመር ሪፐብሊክ በተባለው የጀርመን ፖለቲካዊ ስርዓት ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የተወሰኑ ጽንፈኞች አንዱ ነበር።የአይሁዳውያን ኑሮ በጀርመን ህዳር 8 ቀን 1923 ምሽት ላይ ማዕከላዊ ሙኒክ በሚገኘው ቡርገርብሮይኬለር በተባለው ስፍራ የባቫርያ መንግሥት ባለስልጣናት እና ሌሎች ታዋቂ እንግዶች በተገኙበት በጎርጎሮሳዊው 1918 ዓም የጀርመን ንጉሳዊ ስርዓት ተገርስሶ የቫይመር ሪፐብሊክ የተተካበት ህዝባዊ አብዮት መታሰቢያ በዓል እየተካሄደ ነበር። በዚያ ምሽት ነበር ሂትለር ቢያንስ ሁለት ሺህ ከሚሆኑ ደጋፊዎቹ ጋር ወደ ስፍራው በማቅናት የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ያካሄደው።

በዚህ ዓይነት መንገድ በጎርጎሮሳዊው 1933 በተካሄደ ምርጫ ሥልጣን የያዘው ሂትለር በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ናዚ ጀርመን እስክትሸነፍና በዚህም ሰበብ የራሱን ሕይወት እስካጠፋበት ጊዜ ድረስ ለ12 ዓመታት ጀርመንን መርቷል።
ህዳር 1923ቱ መፈንቅለ መንግሥት የከሸፈበት ሂትለር በተለያየ መንገድ ትግሉን ቀጥሎ ከአስር ዓመት በኋላ የመሪነት ምኞቱን አሳካ። ሂትለርን ለመሪነት ካበቁት ምክንያቶች ውስጥ የያኔው የሀገሪቱ ኤኮኖሚ መዳከም አንዱ ነበር እንደ ዶክተር አስፋወሰን። ምስል The Print Collector/Heritage-Images/picture alliance

የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው ሂደት

የዛሬ መቶ ዓመት በሙኒክ የሆነውን መለስ ብለው ያስታወሱት በጀርመን የአፍሪቃ ጉዳይ አማካሪ ፣ደራሲና የፖለቲካ ተንታኝ ዶክተር ልዑል አስፋወሰን አስራተ ካሳ እንደተናገሩት ሂትለር በሙኒክ የሞከረው መፈንቅለ መንግሥት ፣ አርአያው የነበረው የጣሊያኑ አምባገነን ፋሺስት ቤኒቶ ሙሶሎኒ ከአንድ ዓመት በፊት በሮም ሞክሮ የተሳካለት ዓይነት መፈንቅለ መንግሥት ነበር። ሂትለርና ባልደረቦቹ በዓሉ በሚከበርበት ቡርገርብሮይኬለር ሲደርሱ በዚያ ያልተጠበቀው ሆነ። ቪሊ ብራንት የጀርመንን ታሪክ ያደሱበት ቅጽበትየሂትለር ታጣቂ ደጋፊዎች ፣በአዳራሹ የነበሩት ባለሥልጣናትና እንግዶች በአንድ ክፍል ሰብስበው አሰሩ።ሂትለር በአዳራሹ በርሊን ያለው መንግሥት  ከስራ እንደተወገደ፣ በሚመጡት ቀናትም የባቫርያ ግዛት ዋና ከተማ ሙኒክን ነጻ ካወጡ በኋላ ወደ በርሊን እንደሚሄዱ ተናገረ። በወቅቱም የአንደኛው የዓለም ጦርነት የጀርመን ጀግና ጀነራል ሉድንዶርፍ ከሂትለር ጋር መቀላቀላቸውን  አስታወቁ።
 

 ናዚ ጀርመን በለኮሰው ጦርነት ብዙ ሰዎች በግፍ ተገድለዋል። ከመካከላቸው ከስድስት ሚሊዮን በላይ እንደሚሆኑ የተገመቱ አይሁዶች ይገኙበታል። ከፍተኛ መጠን ያለው ሀብትና ንብረትም ወድሟል። በናዚ ጀርመን የደረሰው ጥፋት 78 ዓመት አልፎታል።
ጦርነቱ ካበቃበት ከ1945ዓም አንስቶ ለ4 ዓመታት በአራት ኃያላን መንግሥታት ተይዛ  የቆየችው ጀርመን በ1949 ምዕራብና ምሥራቅ ተብላ ተከፈለች። ከ41 ዓመት በኋላ በጎርጎሮሳዊው 1990 ዳግም ተዋኃደች። ምስል United Archives/picture alliance

መፈንቅለ መንግሥቱ እንዴት ከሸፈ?

 

የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው በማግስቱ ህዳር ዘጠኝም  ቀጥሎ የታጠቁ የሂትለር ፓርቲ ኃይሎች አንድ ወታደራዊ ጦር ሰፈር ያዙ። ሙኒክ መሀከል ላይ የጀግኖች መታሰቢያ ወደሚገኝበት ስፍራም ተሰልፈው ሄዱ ። በዚህ መሀል የባቫርያ መንግሥት ወታደሮችንና ፖሊሶችን ልኮ ጥቃት ከፈተባቸው። የሂትለር ታጣቂዎችም በአጸፋው በመንግሥት ኃይሎች ጥቃት ሰነዘሩ። በዚህ የተኩስ ልውውጥም ቢያንስ 14 ናዚዎችና 4 የፖሊስ መኮንኖች ተገደሉ። የመንግሥት ኃይሎችም ሂትለርንና ግብረ አበሮቹን ማሳደድ ጀመሩ። የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውም ከሸፈ። ተሰውሮ የነበረው ሂትለር ከሁለት ቀናት በኋላ ተይዞ ታሰረ ።እርሱና ከፍተኛ የጦር መኮንኑ ከ6 ወር በኋላ ተፈረደባቸው። ሂትለር አምስት ዓመት ቢፈረድበትም ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ በአመክሮ ተለቋል።ጀነራል ሉድንዶርፍ ደግሞ በአንደኛው የዓለም ጦርነት ያሳዩት ጀግንነት ግምት ውስጥ ገብቶ በናጻ ተለቀቁ።
 

መፈንቅለ መንግሥት ቢከሽፍም ከአስር ዓመት በኋላ ሂትለር የሀገሪቱ ከፍተኛው የስልጣን ማማ ላይ እንዲደርስ የመጀመሪያው እርምጃ ሆኗል። ሂትለር ያኔ የቫይመር ሪፐብሊክ በተባለው የጀርመን ፖለቲካዊ ስርዓት ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የተወሰኑ ጽንፈኞች አንዱ ነበር።
አዶልፍ ሂትለር የናዚ ጀርመን መሪ ከመሆኑ አስቀድሞ ፣በጎርጎሮሳዊው ህዳር 8 እና 9 ፣ 1923 የዛሬ መቶ ዓመት በደቡባዊ ጀርመንዋ ፌደራዊ ግዛት በባቫሪያ ከደጋፊዎቹ ጋር ያካሄደው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የጀርመንን ታሪክ የቀየረ ክስተት ነው። ምስል United Archives/picture alliance

ሂትለር እንዴት ሥልጣን ያዘ ?

 

የህዳር 1923ቱ መፈንቅለ መንግሥት የከሸፈበት ሂትለር በተለያየ መንገድ ትግሉን ቀጥሎ ከአስር ዓመት በኋላ የመሪነት ምኞቱን አሳካ። ሂትለርን ለመሪነት ካበቁት ምክንያቶች ውስጥ የያኔው የሀገሪቱ ኤኮኖሚ መዳከም አንዱ ነበር እንደ ዶክተር አስፋወሰን።የአውስሽቪትዝ መታሰቢያ 75 ተኛ ዓመት  በዚህ ዓይነት መንገድ በጎርጎሮሳዊው 1933 በተካሄደ ምርጫ ሥልጣን የያዘው ሂትለር በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ናዚ ጀርመን እስክትሸነፍና በዚህም ሰበብ የራሱን ሕይወት እስካጠፋበት ጊዜ ድረስ ለ12 ዓመታት ጀርመንን መርቷል። ጦርነቱ ካበቃበት ከ1945ዓም አንስቶ ለ4 ዓመታት በአራት ኃያላን መንግሥታት ተይዛ  የቆየችው ጀርመን በ1949 ምዕራብና ምሥራቅ ተብላ ተከፈለች። ከ41 ዓመት በኋላ በጎርጎሮሳዊው 1990 ዳግም ተዋኃደች። ናዚ ጀርመን በለኮሰው ጦርነት ብዙ ሰዎች በግፍ ተገድለዋል። ከመካከላቸው ከስድስት ሚሊዮን በላይ እንደሚሆኑ የተገመቱ አይሁዶች ይገኙበታል። ከፍተኛ መጠን ያለው ሀብትና ንብረትም ወድሟል። በናዚ ጀርመን የደረሰው ጥፋት 78 ዓመት አልፎታል። ይሁንና አሁን ጀርመንን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮጳ ሀገራት ቀኝ ጽንፈኞች እየተስፋፉ ነው። ያኔ ከደረሰው ጥፋት ምን ትምሕርት መውሰድ ይቻል ይሆን? ልዑል ዶክተር አስፋወሰን መፍትሄው ወደዱም ጠሉም በዴሞክራት ፓርቲዎች እጅ  ነው ብለዋል። ዴሞክራት ፓርቲዎች ልዩነታቸውን አጥብበው አንድ ቢሆኑ  ቢሆኑ ችግሩ ሊቀረፍ ይችላል የሚል እምነት አላቸው።

ኂሩት መለሰ

ታምራት ዲንሳ