1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦነግ ለኦሮሚያ ክልል ችግር መንግሥትን ተጠያቂ አደረገ

ረቡዕ፣ መስከረም 23 2016

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ ፣ወቅታዊ መግለጫ በኦሮምያ እየተፈጠረ ነው ላለው ሰፊ ማህበራዊ ቀውስ መንግሥትን ተወቃሽ ያደርጋል፡፡ መንግስት ሸኔ ያለውን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ለማጥፋት በሚወስደው ወታደራዊ እርምጃ ምክንያት ዓለም አቀፍ ረጂ ተቋማትም የአከባቢውን ማህበረሰብ ከሰቆቃው መታደግ አልቻሉም ሲል ትችቱን ሰንዝሯል፡፡

https://p.dw.com/p/4X75C
የፓርተው ቃል አቃባይ አቶ ለሚ ገመቹም በአስተያየታቸው አክለው “ያለፉትን አምስት ኣመታት ህዝቡ የተረጋጋ ኑሮን ሲመራ አልነበረም፡፡ ገበሬው በመስክ የዘራውንም በቆሎ ታጣቂዎች ይገቡበታል በሚል እንዲወድም ሆኗል፡፡ አሁንም ብሆን ህዝቡ ከውጪ የሚጠብቀው የእህል ምርት የለውም፡፡ ዓለማቀፍ ረጂ ተቋማትም ቢሆን ለአከባቢው ትኩረት የሰጠ ባለመሆኑ እርዳታው እንዲደርስላቸው ጥሪ ያቀረብንበት ነው ይህ መግለጫ” ብለዋል።
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ወቅታዊ መግለጫው እየተፈጠረ ነው ላለው ሰፊ ማህበራዊ ቀውስ መንግሥትን ተወቃሽ ያደርጋል፡፡ መንግስት ሸኔ ያለውን የኦሮሮሞ ነጻነት ሰራዊትን ለማጥፋት በሚወስደው ወታደራዊ እርምጃ ምክንያት ዓለም አቀፍ ረጂ ተቋማትም የአከባቢውን ማህበረሰብ ከሰቆቃው መታደግ አልቻለም ሲል ትችቱን ሰንዝሯል፡፡

«በአራቱ የወለጋ ዞኖች፣ በኢሉባቦር እና ቡኖ በደሌ ወረዳዎች ኅብረተሰቡ ለከፋ የምግብና መድኃኒት እጦት ተዳርጓል» ኦነግ

ምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ ግጭት በተስፋፋባቸው አከባቢዎች ህብረተሰቡ በመድኃኒትና የምግብ እጦት ከፍተኛውን ስቃይ እያሳለፈ ነው ሲል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመለከተ። ፓርቲው ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ ህብረተሰቡ ላይ እየደረሰ ነው ላለውም የበዛ እንግልት እና ሰቆቃ መንግስትን በተጠያቂነት ወቅሷል። መንግስት በበኩሉ በግጭት ቀስቃሽነት የወቀሳቸውን ታጣቂዎች ህብረተሰቡ እየገፋ ላለው የመከራ ህይወት በምክኒያትነት ጠቅሶ፤ ታጥቀው ክልሉን ያምሳሉ ባላቸው ላይ እርምጃ በመውሰድ መረጋጋት በተፈጠረባቸው አከባቢዎች ላይ ምግብና መድሃኒትን ተደራሽ ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት እያደረኩ ነው ብሏል፡፡ የኦነግ የአገር ማረጋጋት ጥሪና የመንግሥት አስተያየት

ኦነግ በሰሞኑ መግለጫው በኦሮሚያ በተለይም በአራቱ የወለጋ ዞኖች እና በኢሉባቦር እና ቡኖ በደሌ ወረዳዎች ህብረተሰቡ ለከፋ የምግብና መድኃኒት እጦት ተዳርጎ በከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቋል ብሏል፡፡ ፓርቲው በዚሁ መግለጫ እንዳብራራው በተለይም ላለፉት አምስት ዓመታት በከፋ ጦርነት ውስጥ መቆየቱን የገለጸው በምዕራብ ኦሮሚያ አራቱ የወለጋ ዞኖች ውስጥ የነበረው ሁኔታ ህብረተሰቡ አርሶ ጎተራውን ባለመሙላቱ ለርሃብ መዳረጉንና ፣በከፋው ግጭት ህብረተሰቡ ወባን ጨምሮ ለተለያዩ ወረርሽኞች መጋለጡን አንስቷልም፡፡ በምእራብ ኦሮሚያ 6 ዞኖች በ129 ወረዳዎች እና 7 ከተማ አስተዳደሮች ውስጥ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በረሃብና በሽታ መፈተናቸውንም መግለጫው አትቷል፡፡ 

ዶክተር ለገሰ «በሁሉም አከባቢ መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የሚወስዳቸው እርምጃዎች ውጤት እያስገኙ ነው። በተለይም በምዕራብ ኦሮሚያ ‘ሸኔ’ በለኮሰው ግጭት መንግስት የዜጎችን ደህንነት ለማስከበር ሲል እርምጃ ወስዷል፡፡ እነዚህ ታጣቂዎች ኃይል የሚያገኙት የማህበረሰቡ መገልገያ መንገዶችን በመዝጋት የሸቀጦችና መድኃኒቶች ማጓጓዣን በማስተጓጎል እንደመሆኑ፤ ህብረተሰቡ አይጎዳም ማለት አይቻልም፡፡ መንግሥት እነዚህን ነገሮች ለመቀነስ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል።»ብለዋል
ፓርቲው መንግስት ላይ ስለሰነዘረው ወቀሳ እና በአከባቢው ላይ ማህበረሰቡ እያሳለፈ ነው ስለተባለው ሰቆቃ ተጠይቀው ለዶቼ ቬለ ማብራሪያ የሰጡት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ፤ የቀውሱ ዋነኛ መነሻው የታጣቂዎች እንቅስቃሴ ነው ብለዋል።ምስል Private


የፓርቲው ቃል አቀባይ አቶ ለሚ ገመቹ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ተጨማሪ ማብራሪያ እዳብራሩት የተጠቀሱት ቁጥሮች ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች መሆኑንና ጉዳቱ ከዚህም ሊልቅ እንደምችል ገልጸዋል፡፡ “ያወጣነው መረጃ እንዲሁ ለማለት ሳይሆን በተጨባጭነት ከየሐኪም ቤቶች እና ማህበረሰቡ የተሰበሰቡ ናቸው፡፡ መረጃዎቹን ከአደረጃጀታችን በተጨማሪ የኦሮሞ ሐኪሞች ማህበርም ያወጣ እንደመሆኑ ተጨባጭ ነው፡፡ እጃችን ላይ ያለውን ተጨባጭ መረጃ ነው ያስቀመጥነው፡፡ ህብረተሰባችን ሐኪም እና ሐኪም ቤት ለማግኘት ሰፊ ርቀት ይሄዳል፡፡ እንደዚያም ተጉዘው ግን መድኃኒት እንኳ ማግኘት ከባድ ነው። በአጠቃላይ ምዕራብ ኦሮሚያ ላለፉት አምስት ዓመታት የጦርነት አውድማ ነው የሆነው።”ስለ ኦሮሚያ ክልል አለመረጋገትና እልባቱ የኦነግ መግለጫ


የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ወቅታዊ መግለጫው እየተፈጠረ ነው ላለው ሰፊ ማህበራዊ ቀውስ መንግሥትን ተወቃሽ ያደርጋል፡፡ መንግስት ሸኔ ያለውን የኦሮሮሞ ነጻነት ሰራዊትን ለማጥፋት በሚወስደው ወታደራዊ እርምጃ ምክኒያት ዓለማቀፍ ረጂ ተቀቋማትም የአከባቢውን ማህበረሰብ ከሰቆቃው መታደግ አልቻለም ሲል ትችቱን ሰንዝሯል፡፡ የፓርተው ቃል አቃባይ አቶ ለሚ ገመቹም በአስተያየታቸው አክለው “ያለፉትን አምስት ኣመታት ህዝቡ የተረጋጋ ኑሮን ሲመራ አልነበረም፡፡ ገበሬው በመስክ የዘራውንም በቆሎ ታጣቂዎች ይገቡበታል በሚል እንዲወድም ሆኗል፡፡ አሁንም ብሆን ህዝቡ ከውጪ የሚጠብቀው የእህል ምርት የለውም፡፡ ዓለማቀፍ ረጂ ተቋማትም ቢሆን ለአከባቢው ትኩረት የሰጠ ባለመሆኑ እርዳታው እንዲደርስላቸው ጥሪ ያቀረብንበት ነው ይህ መግለጫ” ብለዋል።

ፓርቲው በዚሁ መግለጫ እንዳብራራው በተለይም ላለፉት አምስት ዓመታት በከፋ ጦርነት ውስጥ መቆየቱን የገለጸው በምዕራብ ኦሮሚያ አራቱ የወለጋ ዞኖች ውስጥ የነበረው ሁኔታ ህብረተሰቡ አርሶ ጎተራውን ባለመሙላቱ ለርሃብ መዳረጉንና ፣በከፋው ግጭት ህብረተሰቡ ወባን ጨምሮ ለተለያዩ ወረርሽኞች መጋለጡን አንስቷልም፡፡ በምእራብ ኦሮሚያ 6 ዞኖች በ129 ወረዳዎች እና 7 ከተማ አስተዳደሮች ውስጥ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በረሃብና በሽታ መፈተናቸውንም መግለጫው አትቷል፡፡ 
ኦነግ በሰሞኑ መግለጫው በኦሮሚያ በተለይም በአራቱ የወለጋ ዞኖች፣ በኢሉባቦር እና ቡኖ በደሌ ወረዳዎች ህብረተሰቡ ለከፋ የምግብና መድኃኒት እጦት ተዳርጎ በከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቋል ብሏል፡፡ ምስል Seyoum Getu/DW


የኦሮሚያ ክልል አለመረጋጋት እና የዜጎች ሰቆቃፓርቲው መንግስት ላይ ስለሰነዘረው ወቀሳ እና በአከባቢው ላይ ማህበረሰቡ እያሳለፈ ነው ስለተባለው ሰቆቃ ተጠይቀው ለዶቼ ቬለ ማብራሪያ የሰጡት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ፤ የቀውሱ ዋነኛ መነሻው የታጣቂዎች እንቅስቃሴ ነው ብለዋል፡፡ “በሁሉም አከባቢ መንግሥት የሕግ የበላይነትን ለማስከበር የሚወስዳቸው እርምጃዎች ውጤት እያስገኙ ነው። በተለይም በምዕራብ ኦሮሚያ ‘ሸኔ’ በለኮሰው ግጭት መንግስት የዜጎችን ደህንነት ለማስከበር ሲል እርምጃ ወስዷል፡፡ እነዚህ ታጣቂዎች ኃይል የሚያገኙት የማህበረሰቡ መገልገያ መንገዶችን በመዝጋት የሸቀጦችና መድኃኒቶች ማጓጓዣን በማስተጓጎል እንደመሆኑ፤ ህብረተሰቡ አይጎዳም ማለት አይቻልም፡፡ መንግሥት እነዚህን ነገሮች ለመቀነስ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል። መንግስት በተቆጣጠራቸው ሰፊ አከባቢዎች እነዚህን የሸቀጦች እና መድኃኒት አቅርቦቶችን እያቀላጠፈ ይገኛል።”
ላለፉት አምስት አምስት ዓመታት መረጋጋት የተሳነው በተለይም የምዕራብ ኦሮሚያ አከባቢ ለሚሊዮኖች መፈናቀልና ለሺዎች መገደል ምክንያት መሆኑ በተደጋጋሚ ተዘግቧል፡፡
ስዩም ጌቱ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ