1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ

ቅዳሜ፣ መስከረም 19 2016

"የዋጋ ንረቱ ግዜ ሳይለይ ማሻቀቡ ሳያንስ አሁን የተደረገው የነዳጅ ዋጋ ማሻሻያ መንግስት በሀገሪቱ ወስጥ ያለውን የዋጋ ግሽበት እቀንሳለሁ ማለቱን የማይታሰብ ያደርገዋል" የምጣኔ ሃብት ባለሙያ

https://p.dw.com/p/4X0Rj
በአዲስ በባ የነዳጅ ማደያዎች ወረፋ
አዲስ አበባ ከገኙ የዳጅ መቅጃዎች በአንዱምስል Solomon Muchew/DW

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪና የኑሮ ውድነት

 

መስከረም 19 ቀን 2016 የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማሻሻያ መደረጉን የንግድ እና ቀጠናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር   አስታውቋል ከአርብ መስከረም 19 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ  ቤንዚን በሊትር - 77 ብር ከ79 ሣንቲም. ነጭ ናፍጣ በሊትር - 79 ብር ከ75 ሣንቲም. ኬሮሲን በሊትር - 76 ብር ከ75 ሣንቲም ሆኗል። የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር - 70 ብር ከ83 ሣንቲም፤ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር - 62 ብር ከ36 ሣንቲም፤ ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር - 61 ብር ከ83 ሣንቲም  በሚል የችርቻሮ መሽጫ ዋጋ ማስተካከያ ተድርጎበታል  ።
ከ ዛሬ አመት በፊት  በመንግስት ድጎማ እየተደረገለት 15 ብር ከ 76 ሳንቲም ይሽጥ የነበረው አንድ ሌትር ቤንዚን   አሁን ወደ  77 ብር ከ 65 ሳንቲም ከፍ ብሏል    የአንድ ሌትር ናፍጣ ከ 19 ብር ከ 02 ሳንቲም ወደ 79 ብር  ከ 75 ሳንቲም ማሻቀብ  ወጥቷል   ። ይህ ብቻ ሳይሆን  በአዲስ አበባ ባሉ የነዳጅ ማደያዎች ነዳጅ ለመቅዳት ተደርድረው ወረፋ የሚጠብቁ  መኪኖችን ማየት የተለመደነው
መንግስት የአለም ገበያን የተከተለ የነዳጅ አቅርቦት ይኖረኛ በሚል ሀሳብ ጭነቱን ከራሱ አውርዶ ወደ ማህበረስቡ ለማሻገር  እየሞከረነው  ነው፤ ነገር ግን  በአለም ሆነ አልሆነ በሀገሪቱ ላይ በሁሉም ዘርፍ የሚታየው የዋጋ ንረት አሁን ካለው የዋጋ ግሽበት አንፃር በኢኮኖሚው ላይ  ከባድ ጫና ይፈጥራል

የድሬዳዋ አሽከርካሪዎች ነዳጅ ለመቅዳት በወረፋ ላይ
የድሬዳዋ አሽከርካሪዎች ነዳጅ ለመቅዳት በወረፋ ላይ (ምስል ከክምችት ክፍላችን)ምስል DW/M. Teklu

የነዳጅ ዋጋ በ ቅርቦትም በፍላጎትም  ላይ ተፀኖ  የሚያደርግ ነው ሲሉ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶክተር አለማየሁ ከበደ ለ DW   ተናግረዋል፣

DW ተዘዋውሮ ያናገራቸው የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች  ነዳጅ ለማግኘት የሚጠብቁት ወረፋ እና  የዋጋ ጭማሪው እንሱንም ድንበኞቻቸውንም እንደሚጎዳ ይናገራሉ ።

የዋጋ ንረቱ ግዜ ሳይለይ ማሻቀቡ ሳያንስ አሁን የተደረገው የነዳጅ ዋጋ ማሻሻያ መንግስት በሀገሪቱ ወስጥ ያለውን የዋጋ ግሽበት እቀንሳለሁ ማለቱን የማይታሰብ  ያደርገዋል ሲሉ የምጣኔ ሀብት ተንታኙ አቶ ፍትህአውቅ የወንድወስን   ለ DW ተናግረዋል።
 

ሃና ደምሴ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር