1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጽንፈኝነት በአውሮጳ

ማክሰኞ፣ የካቲት 5 2016

ጽንፈኞቹ ስደተኞች ከነዘር ማዘራቸውን ከሃገራችን ይውጡ በማለት የሚያደርጉት ውትወታ በአብዛኛው ለምርጫ ቅስቀሳ ተብሎ ነው ቢባልም በሕብረተሰቡ ግን እንዲህ አይነት አደገኛ አስተሳሰቦች እየተስፋፉ መምጣታቸውን በተለያዩ የአውሮጳ ሃገሮች ጽንፈኞች ወደስልጣን መምታት መጀመራቸው የዚህ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል

https://p.dw.com/p/4cLjV
Deutschland Berlin 2024 | Demonstration gegen Rechtsextremismus
ምስል Ebrahim Noroozi/AP/picture alliance

በአውሮጳ እያገረሸ ያለው የጽንፈኝነት ስጋት

በአውሮጳ የቀኝ አክራሪ ፓርቲዎች የነበሩና ያሉ ቢሆንም በአሁኑ ወቅትግን በተለይም በስደተኞች ላይ የሚያቀነቅኑት ጽንፈኛ አቋም ምክንያት ወደ ስልጣን የሚመጡበት አጣሚዎች እየተስተዋለ ነው። በኔዘርላንድስ ምርጫ ስደተኛ ጠል የሆነው የቀኝ አክራሪ ፓርቲ አሸነፈጽንፈኞቹ ስደተኞች ከነዘር ማዘራቸውን ከሃገራችን ይውጡ በማለት የሚያደርጉት ውትወታ በአብዛኛው ለምርጫ ቅስቀሳ ተብሎ ነው ቢባልም በሕብረተሰቡ ግን እንዲህ አይነት አደገኛ አስተሳሰቦች እየተስፋፉ መምጣታቸውን በተለያዩ የአውሮጳ ሃገሮች ጽንፈኞች ወደስልጣን መምታት መጀመራቸው የዚህ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል።

Deutschland Berlin | Demonstration gegen Rechtsextremismus
ምስል Christoph Strack/DW

ይህ አዲሽ ክስተት አደለም። ጽፈኛ አክራሪ ፓርቲዎች በኒዘርላንድ፣ በፖላንድ፣ በጣልያንና በሃንጋሪ ስልጣን ላይ ተቆናጠዋል። በጀርመን የሚገኘው AFD የተባለ ፓርቲ በህቡእ ባካሄደው ስብሰባ በሃገሪቱ የሚገኙ ስደተኞች፤ የጀርመን ዜግነት ያላቸውን ጨምሮ እስከነዘር ማንዘራቸው በገፍ ለማባረር የተወያዩበት ስብሰባ በጋዜጠኞች ለአደባባይ ከወጣ በኋላ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ጀርመናውያን ወደ አደባባይ በመውጣት ቃውሞአቸውን ገልጸዋል። እየገለጹም ይገኛሉ።

ይልማ ሃይለሚኬኤል

እሸቴ በቀለ