በኦሮሚያ በዞን መዋቅር የተነሳው ውዝግብ ቀጥሏል
ዓርብ፣ ነሐሴ 19 2015በኦሮሚያ ክልል ጉጂና ምስራቅ ቦረና ዞኖች አዋሳኝ ላይ የሚገኘው ጎሮዶላ በተባለ ወረዳ ከዞን መዋቅር ጋር ተያይዞ የተነሳው ተቃውሞ አሁንም አለመብረዱን ነዋሪዎች ገለጹ። በክልሉ ምስራቅ ቦረና በሚል ከጉጂ፣ ቦረና እና ባሌ ዞኖች የተወሰኑ ወረዳዎችን ቆርሶ የተመሰረተው አዲስ ዞን አሁንም የህዝብ ቅሬታ መነሻ እንደሆነ ቀጥሏል ነው የተባለው። በተለይም ። የቦረናን ድርቅ ለመቋቋም ድጋፍ እየተደረገ ነዉ ተባለእንደ በጉጂ ዞን ስር ይተዳደር የነበረውና አሁን ላይ ምስራቅ ቦረና ስር እንዲተዳደር በአዲሱ መዋቅር የተወሰነበት ጎሮ ዶላ ወረዳ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ ቀጥሎ በርካቶች ትናንት በተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ በአፈሳ መታሰራቸውም ተነግሯል ። ነዋሪዎቹ አስተያየትና የህክምና ምንጮች ማስረጃ ትናንት በገቢያ ስፍራ የተነሳውን ተቃውሞ ለማርገብ የጸጥታ ኃይሎች ወሰዱ በተባለው እርምጃ ሰዎች ተጎድተዋል፡፡የፀጥታ ስጋት የፈጠረው ግጭት በጉጂ ዞንስሜ ይቆይ ብለው አስተያየታቸውን የሰጡን አንድ የጎሮዶላ ወረዳ ሐራቀሎ ከተማ ነዋሪ በትናንቱ የተቃውሞ ሰልፍ በርካቶች መታሰራቸውንና ሰልፉን ለመበተን በተወሰደ እርምጃ የተጎዱም መኖራቸውን ገልጸውልናል፡፡ “14 የወረዳው አመራሮችን ጨምሮ እስከ 150 የሚሆኑ ሰዎች እንዲፈቱና የህዝቡ ጥያቄ ይመለስ በሚል በሀራቀሎ ከተማ ትናንት ገበያም ስለነበር ሰው ሰላማዊ ሰልፍ አድርጎ ነበር፡፡ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ሰልፉን ለመበተን ሰው ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈጽመው መንገድ ላይ ያገኙትን ሁሉ የመከላከያ ካምፕ ወደሚባል ጊቢ ሲያግዟቸው ነበር፡፡ ትናንት ብቻ በግምት ወደ 200 የሚሆኑ ሰዎች ታስረዋል የሚል እምነት አለን፡፡ ከዚያ ከተደበደቡም ከፍተኛ ጉዳትም ያስተናገዱ ነበር፡፡ ወደ ሰባት ሰው ወደ ህክምና ማዕከል መግባታቸውን ተመልክቻለሁ፡፡” የኦሮሚያ ክልል አዲስ ዞን ያስከተለዉ ዉዝግብ
ከዚህ በፊት የጎሮወረዳ አስተዳዳሪ የነበሩ ገልገሎ ኦዶ፣ ምክትላቸው አሪቲ ጃርሶ፣ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ የነበሩት ኃይሌ ኦዶ እና ሌሎች 14 የወረዳው አመራሮች ነገሌ ቦረና ተወስደው መታሰራቸውንና እስካሁንም አለመፈታታቸው ተደጋግሞ ተነግሯል። እንደ እኚህ ነዋሪ አስተያየት በዚህ በጎሮዶላ እየተደረገ ነው በተባለው የህዝብ ተቃውሞ የነዋሪዎች ህይወት ክፉኛ ተመሰቃቅሏል፡፡ በወረዳዋ ከዞን መዋቅሩ ጋር ተያይዞ በተነሳው ጥያቄ መረጋጋትም ባለመኖሩ ማህበረሰቡ ተረጋግቶ ኑሮውን መምራት ተስኖታልም፡፡ ይህ ሁኔታ ዛሬም በወረዳዋ ከተማ ሐርቀሎ ቀጥሎ መስተዋሉን በማስረዳት፡፡ “ስለዚህ ማህበረሰቡ ላይ ጉዳቱ ከፍቷል፡፡ ዛሬ ጠዋት ደግሞ አዲስ የተመደቡ አመራሮች ህዝቡ ስብሰባ እንዲወጣ ሲጠይቁ ነበር፡፡ ህዝቡ ደግሞ አንወጣም የታሰሩ ይፈቱ ጥያቄያችንም ከመሰረቱ ምላሽ ያግኝ በማለት ሱቁን ሁሉ ዘግቶ ከተማውን ለቆ እየወጣ ነው፡፡ መንግስትም ህዝቡ እየጠየቀ ላለው ጥያቄ ቀና ምላሽ እየሰጠ አይደለም፡፡ አሁን በጎሮ ዶላ ያለው ሁኔታ ጥሩ አይደለም፡፡ ትራንስፖርት ጨምሮ እንቅስቃሴው ዝግ ነው፡፡”በቦረናው ድርቅ ለተጎዱ በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን ድርጅቶች እርዳታ
ሌላኛዋ የከተማዋ ነዋሪ እንዳሉትም በትናንቱ ሰላማዊ ሰልፍ ሰዎች ከመጎዳታቸውም በተጨማሪ ሁኔታው የከተማዋን መታወክ ጨምሯል፡፡ “ብዙ ሰው ነው የታሰረው፡፡ አሁን ከተማዋ መረጋጋት ውስጥ አይደለችም፡፡ ህዝብም ለችግር ተዳርገዋል” ሲሉ አለመረጋጋቱ በእለት ተእልት ኑሮ ላይ ያስከተለውን አሉታዊ ተጽእኖ አስረድተውናል፡፡የፀጥታ ስጋት ሆኖ የቀጠለው የጉጂ እና ምሥራቅ ቦረና ዞን መዋቅር
በትናንቱ ሰልፍ የተጎዱ ሰዎች መኖራቸውን በማስመልከት አንድ የሀርቀሎ ጤና ጣቢያ የህክምና ባለሙያንም አስተያየት ጠይቀን ነበር፡፡ ስማቸው እንዲጠቀስ እንደማይፈልጉ ገልጸው አስተያየታቸውን የሰጡን እኚህ የህክምና ባለሙ፤ “በትናንቱ አለመረጋጋት እለቱም ገበያ ስለነበር ሰዎች ተጎድተዋል፡፡ ወደ እና ከመጡ ሰባት ሰዎች ግን የከፋውን ጉዳት ያስተናገዱት አንድ ሰው ናቸው፡፡ ስድስቱ የመረጋገት እና የመደብደብ አደጋ እንጂ ያን ያህል የከፋ ጉዳት አላስተናገዱም” ብለዋል፡፡
በጎሮ ዶላ ከዚህ በፊትም ተደጋግሞ ተስተውሏል በተባለው ተቃውሞ ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸውና ከጉጂ ወደ ነጌሌ ቦረና የሚወስደው ዋና መንገድ ላይ መስተጓጎሎች መድረሳቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡
ስለነዋሪዎቹ ቅሬታ ከአከባቢው ባለስልጣናት ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት በተለይም የወረዳው አዲስ አስተዳዳሪ አቶ ጌቱ ጩሉቄ እና ለምስራቅ ቦረና ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ታጁራ ኦዳ በተደጋጋሚ ጊዜያት ደውለን የጽሁፍ መልእክትም ብንልክላቸው ምላሽ ባለማግኘታችን አስተያየታቸውን ማካተት አልተቻለም፡፡ ከአንድ ወር በፊት በጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤ ከምክር ቤቱ አባላት ጉዳዩን አስመልክቶ ጥያቄ ተነስቶ በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽ ሲሰጥበት የዞን መዋቅር ውሳኔው የተላለፈው የማህበረሰቡን የልማትና ጸጥታ ሁኔታን ተጠቃሚነት ከግምት ያስገባ ነው ተብሎ ውሳኔውም የማይቀለበስ ብለው ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡
ስዩም ጌቱ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ