1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስርቆት፣ ዘረፋ፣ እገታና ሥርዓተ አልበኝነት በትግራይ

ሐሙስ፣ መስከረም 3 2016

በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች በንፁሃን ዜጎች፥ በተለይም በሴቶች ላይ የሚደርስ የጥቃት እና ግድያ ዜና መስማት የተለመደ ሲሆን አብዛኞቹ ለቀናት ከሚቆይ የማሕበራዊ ሚድያ ዘመቻ ውጭ ፍትህ የማረጋገጥ ተግባራትም በስፋት አይስተዋሉም

https://p.dw.com/p/4WLaD
በመቀሌ ከተማ ጨምሮ ሥርዓተ አልበኝነት ተንሰራፍቷል
የትግራይ ዋና ከተማ መቀሌ በከፊልምስል Millionen Hailesilassie/DW

ወንጀል መበራከቱን የክልሉ አስተዳደርም ያዉቀዋል

በትግራይ ትላልቅ ከተሞች ዘረፋ፣ሌብነት፣ እገታና ጥቃት እየተስፋፋ መሆኑን ነዋሪዎች አስታወቁ።የየከተማዉ ሕዝብ እንደሚለዉ እየከፋ የመጣዉ ሥርዓተ አልበኝነት ግድያ፣ ዝርፍያ እና እገታ የሕዝቡን እንቅስቃሴ እያወከ ነዉ። የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርም የፀጥታዉ ስጋት አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን አምኗል።
በመቐለ ከተማ ጨምሮ በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች በንፁሃን ዜጎች፥ በተለይም በሴቶች ላይ የሚደርስ የጥቃት እና ግድያ ዜና መስማት የተለመደ ሲሆን አብዛኞቹ ለቀናት ከሚቆይ የማሕበራዊ ሚድያ ዘመቻ ውጭ ፍትህ የማረጋገጥ ተግባራትም በስፋት አይስተዋሉም። ነሐሴ ወር አጋማሽ በመቐለ ከተማ ዓዲሓቂ ክፍለከተማ በጎዳና የተገደለችው ወጣት ዘዉዱ ሀፍቱ፥ ለቀናት አጀንዳ ሆና የቆየች ሲሆን የዘዉዱ ገዳዮች እስካሁን ሳይያዙ፥ ሌሎች የግድያ እና እገታ እንዲሁም ከፍተኛ የመብት ጥሰት ፍፄሜዎችም በስፋት እየተስተዋሉ ይገኛሉ።ከመቐለው ስልፍ ጋር በተገናኘ የታሰሩ የተቃዋሚፓርቲ አመራሮች ከእስር መለቀቃቸዉ

በአዲሱ ዓመት መግብያ ዕለት በማይጨው ከተማም እንዲሁ አንድ የዞን ባለስልጣን መገደሉ በመገናኛ ብዙሐን ተዘግቧል። እነዚህ የግድያ፣ ዝርፍያ እና ሌሎች ወንጀሎች መደጋገም እና በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች መንሰራፋት ሕብረተሰቡ ለከፍተኛ ስጋት ዳርገው ይገኛሉ። በትግራይ አሳሳቢ የፀጥታ ሁኔታ እየተስተዋለ ስለመሆኑ ከነዋሪው በዘለለ በአስተዳደሩም እሙን ነው። በቅርቡ መግለጫ ሰጥተው የነበሩ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች ወጥቶ መግባት ቅንጦት ሆንዋል ሲሉ ተናግረዋል። "ፍትህና ሰላም ላይ ትልቅ ችግር እንዳለን፣ ወደ ቀውስ ደረጃ መድረሱ የሚያጠራጥር አይደለም። በሶሻል ሚድያ የሚነሱ ችግሮች ስለሆኑ ብቻ አይደለም። በሁሉም አካባቢዎች ወጥቶ መግባት እንደቅንጦት የሚታሰብበት ሁኔታ ተፈጥሯል፣ ሰፊ ዝርፍያ አለ" ብለዋል።

መቀሌ
የመቀሌ ከተማ በከፊል ምስል EDUARDO SOTERAS/AFP

በትግራይ በተለያዩ የዝርፍያ ይሁን ሌላ ዓለማ ያላቸው ሰዎች ከሚፈፀም ወንጀል በተጨማሪ የፀጥታ ሀይሎችም እንዲሁ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሲፈፅሙ፣ እስከ ግድያ የሚደርስ ድብደባ ሲያደርሱ ተስተውሏል። ከዚህ በዘለለ መንግስት የማያውቃቸው እስርቤቶች ጭምሮ በክልሉ ስለመኖሩ ግዚያዊ አስተዳደሩ ጥናት አድርጎ እንደደረሰበት፣ በሰዎች ላይ እገታ ፈፅሞ ገንዘብ መቀበል መኖሩ ተመላክቷል። "መንግስት የማያውቃቸው እስርቤቶች አሉ። ይህ የሚያደርጉ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት የፈፀሙ፣ ሁሉም እየለየን ማስገባት ጀምረናል። በዘመቻ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ሁሉንም እናስራቸዋለን። ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ፥ ኤርትራውያን እየተጠለፉ ገንዘብ መቀበል አለ። ዛሬ ኤርትራዊ ብቻ ሊመስልህ ይችላል። ሀብታሞች እና ውጭ ሀገር ዘመድ ያላቸው ተጋሩ ላይም ጀምረዋል። ለማጣራት ብዙ ግዜ ወስዶብናል፥ በቅርቡ ግን ዋና ስራችን እነዚህ ቆሻሻዎች ፍርድ እንዲያገኙ የማድረግ ተግባር ነው" ብለዋል አቶ ጌታቸው ረዳ።ተፈናቃዮችና አዲስ ዓመት በመቐለ

ለዓመታት ጦርነት ባስተናገደችው፣ በርካታ ሕጋዊ ይሁን ሕገወጥ ጦር መሳርያ ባለበት፣ የመንግስት ይሁን የፀጥታ መዋቅር በሚፈለገው መጠን ባልሰፋበት ትግራይ ወንጀሎች ሊበራከቱ የሚችሉበት አጋጣሚ ሰፊ መሆኑ የሚገለፅ ቢሆንም አስተዳደሩ በፀጥታ እና ፍትህ ጉዳዮች በትኩረት አለመስራቱ በማንሳት ተቃዋሚዎች እና ሌሎች ይተቻሉ።

በመቀሌ በሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ታሰሩ

በትግራይ እየታዩ ባሉ ሰፊ የዝርፍያ ተግባራት ዙርያ በተደረገ የውይይት መድረክ የተናገሩት የትግራይ ምክትል ፕሬዚዳንት ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ፥ በሰብአዊ እርዳታ ጨምሮ በተለያየ የህዝብና መንግስት ሐብት ለሚፈፀም ምዝበራ መፍትሔው ስርዓታዊ ማስተካከል መሆኑ ተናግረዋል። ""ሰብአዊ እርዳታ ይሁን የብረታብረት ዝርፍያ እንዲሁም ሌሎች የተደረጉ ዝርፍያዎች እንዴት እንፍታቸው ነው ትልቁ ነገር። አያያዛችን ያዝለቀቅ ነው። አንድ ነገር ሲመጣ ለመያዝ እንሞክራለን ካዛ መልሰን ወደሌላ። ስርዓት አይደለም እየፈጠርን ያለነው። በእኔ አስተያየት ይህ ችግር ፖለቲካዊ ነው። በአንድ ዘመቻ የሚፈታም አይደለም። ስርዓት በማስተካከል ነው የሚፈታው" ብለዋል።

ወንጀል መስፋፋቱን ጊዚያዊ መስተዳድር እንደሚያዉቀዉ አቶ ጌታቸዉ አስታዉቀዋል
አቶ ጌታቸዉ ረዳ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድርምስል Million Haileselassie/DW

በዚህ ጉዳይ ዙርያ ከትግራይ ፖሊስ ኮምሽን ምላሽ ለማግኘት ለቀናት በተደጋጋሚ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ነጋሽ መሐመድ

ታምራት ዲንሳ