1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እንወያይ፤ በአማራ ክልል የቀጠለዉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ማቆምያዉ የት ነዉ?

እሑድ፣ ኅዳር 30 2016

ለአማራ ክልሉ ሰብዓዊ ቀዉስ ተጠያቂዉ ማን ነዉ? በትግራይ ጦርነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተገድለዋል። አሁንም በአማራና በኦሮሚያ ክልል ጦርነቱ ቀጥሏል። መንግሥት ከቀዉስ ማትረፍ ፖሊሲዉን ማቆም አለበት፤ ጠ/ሚኒስትሩ ስልጣን መልቀቅ አለባቸዉ፤ በሃገሪቱ የተኩስ አቁም ታዉጆ ዉይይት መጀመር አለበት» ይላሉ ተወያዮች እርሶስ?። እርሶስ? ይጻፉልን!

https://p.dw.com/p/4Zz9D
በአማራ ክልል በመንግሥት ጦር ሰራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በሚካሄድ ጦርነት ሲቪሎች ጉዳት ደርሶባቸዋል
በአማራ ክልል የድሮን ጥቃት ህጻናትን ጨምሮ ንጹኃን ዜጎች ተገደሉ ምስል Amanuel Sileshi/AFP

ለአማራ ክልሉ ሰብዓዊ ቀዉስ ተጠያቂዉ ማን ነዉ?

ለኢትዮጵያ የጦርነት አዙሪት ተጠያቂዉ ማን ነዉ? ከዚህ ቀደም በትግራይ የሁለት ዓመት ጦርነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከሁለቱም ወገኖች ህይወታቸውን አጥተዋል። በአፋር ክልልም ብዙ ሰዎች ተገድለዋል። አሁንም በአማራና በኦሮሚያ ክልል ጦርነቱ ቀጥሏል። መንግሥት ከቀዉስ ማትረፍ ፖሊሲዉን ማቆም አለበት፤ ጠ/ሚኒስትሩ ስልጣን መልቀቅ አለባቸዉ፤ በሃገሪቱ ሁሉ፤ የሚካሄዱ ጦርነቶች በሙሉ በተኩስ አቁም መቆምና ዉይይት መጀመር አለበት» ሲሉ ተወያዮች አስተያየት ሰጥተዋል። 

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶችን ለማክበር በቀዳሚነት የፈረመችበት ፤የተመድ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች ስምምነት 75ኛ ዓመት ነው፤ ዛሬ ። ኢትዮጵያ ስምምነቱን በቀዳሚነት ትፈርም እንጂ፤ ሀገሪቱ ዛሬም ድረስ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተደጋግሞ የሚሰማባት ሀገር ሆንዋል። እንደዉም ተባብሷል የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም። በኢትዮጵያ አማራ ክልል በፌደራል መንግሥት ወታደሮች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ለወራት በቀጠለዉ ጦርነት ሳቢያ ተፈጽመዋል የሚባሉ  የሰብዓዊመብት ጥሰቶች  አንዱ ማሳያነዉ። በጦርነቱ ምክንያት  በርካታ ሰላማዊዜጎች በሰዉ አልባ አዉሮፕላን ወይም በድሮን  ጭምር መገደላቸውንየሰብዓዊ መብት ድርጅቶች የሚያወጡት ዘገባ ያሳያል።  በማንነት ላይያተኮረን ግድያ ሸሽተዉ ከሌሎች ክልሎች ወደ አማራ ክልል  የመጡ ዜጎችምበረሃብ እየሞቱ እንደሆንም ይነገራል።

በ2015 ዓ.ም መጨረሻ መንግሥት የክልል ልዩ ኃይሎችን እንደ አዲስ ለማዋቀር ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት እና የፋኖ ታጣቂዎች በሚያደርጉት ግጭት፤በክልሉ በርካታ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን እያስከተለ ነዉ። የየብስ ትራንስፖርትአገልግሎት በመስተጓጎሉ ምክንያት የክልሉነዋሪ በአየር ትራንስፖርት ካልሆነ ከመሃል አገር አሊያም ከሌሎች ክልሎች ጋር የሚያደርገው መስተጋብር በእጅጉ ፈተና ላይ ወድቋል። ከማህበራዊ መስተጋብሩ በተጨማሪ ወደ ክልሉ የሚገቡ እና ከክልሉ ወደ ሌሎች አከባቢዎች የሚሄዱ ምርትና ሸቀጦችን ማጓጓዝም አይቻልም። በክልሉ  ቱሪዝምን የመተዳደሪያምንጫቸዉ ያደረጉ በርካታ ሰዎችም፤  ዘርፉ በጦርነቱክፉኛ በመመታቱ የዕለት ጉርስ አሳጥቷቸዋል።

 በሌላ በኩል ጦርነቱን ተከትሎ ቢያንስ ላለፉት አራት ወራት የተቋረጠው የኢንተርኔት አገልግሎትም የክልሉን  ነዋሪ ሃሳቡንበነጻነት የመግለጽ መብቱን ተቀምቷል። አገልግሎቱ በመቋረጡ በክልሉእየተፈፀሙ ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በሚገባ  እንዳይሰሙ ተደርጓል የሚሉአሉ።

ይህንንተከትሎ ከሳምንታት በፊት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው መግለጫም በክልሉ እየተካሄደ ባለው ግጭት ምክንያት እየተፈፀሙ ያሉ የድሮን ጥቃቶች እና ሌሎች የሰብዓዊ ጥሰቶች እንዳሳሰበው መግለጹ ይታወሳል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሰሞኑን በሰጠዉ መግለጫ በአማራ ክልል የሚታየዉ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን አሳሳቢ ብሎታል። በዛሬዉ ዉይይታችን የአማራ ክልል ጦርነት፡ የቀጠለዉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት፤ እና መፍትሄዉን ይቃኛል፤ በዚህ ዉይይት ላይ ሃሳባቸዉን በመስጠት እንዲሳተፉ የጋበዝናቸዉ፤  

ወ/ሮ ቅድስት አሳልፍ  የዓለም ዕርቅ እና ሰላም ግብረሰናይ ድርጅት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ ከአዲስ አበባ፤ 

ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ፤ የሕግ እና የፌደራላዊ ሥርዓት ምሁር ከፍራንክፈርት ጀርመን

አቶ ያሬድ ኃይለማርያም፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ከአዲስአበባ፤ እንዲሁም  

እዉቁ ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው  ናቸው።  

ተወያዮች«ለመሆኑ በአማራ ክልል በሀገር መከላከያ ሰራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል እየተካሄደ ያለውን ጦርነት እንዴት ይታያል? በጦርነቱየሚሰሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችስ እንዴት ይገመገማሉ? ኢትዮጵያ ከገባችበት ከጦርነት አዙሪት እንዴት ነው መውጣት የሚቻለው?ዘላቂዉ መፍትሄስ ምንድን ነዉ ? ሰላም ለማስፈን በተለይ  ከመንግስትስ ምን ይጠበቃል?ከተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችስ?ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብስ?» በሚሉ ነጥቦች ላይ ያላቸዉን ሃሳብ ሰጥተዋል። ተወያዮች፤ ካነስዋቸዉ ነጥቦች መካከል፤

«ከዚህ ቀደም በትግራይ የሁለት ዓመት ጦርነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከሁለቱም ወገኖች ህይወታቸውን አጥተዋል። በአፋር ክልልም ብዙ ሰዎች ተገድለዋል። አሁንም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል ጦርነቱ ቀጥሏል። መንግሥት ከቀዉስ ማትረፍ ፖሊሲዉን ማቆም አለበት፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን መልቀቅ አለባቸዉ፤ በሃገሪቱ ሁሉ፤ የሚካሄዱ ጦርነቶች በሙሉ በተኩስ አቁም መቆም እና ዉይይት መጀመር አለበት ብለዋል።» እርሶስ ምን ይላሉ አስተያየቶን ይጻፉልን!

አዜብ ታደሰ