1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ምርት ለመሸጥ የመንገዶች መዘጋጋት ተፅእኖ ፈጥሯል»

ሰኞ፣ መስከረም 28 2016

ከሐምሌ 2015 ዓ.ም. መጨረሻ ጀምሮ በአማራ ክልል በፋኖና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በተካሄደው ጦርነት በሰሜን ሸዋና በአብዛኛው በምዕራብ አማራ የሚገኙ 1,226 ከፍተኛ፣ መካከለኛና አነስተኛ ኢንዳስትሪዎችና በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞቻቸው ሥራ ማቆማቸውን የአማራ ክልል ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/4XIdj
የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዱ ሁሴን፣ ከመብራት መቆራረጥ ጋር ያለውን ችግር ለመፍታት ከሚመለከተው አካል ጋር በጋራ እየተሰራ ነው ብለዋለ፣ የክልሉን ሰላም ወደ ነበረበት ለመመለስም ሁሉም የክልሉ ነዋሪዎች እንዲተባበሩ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጠይቀዋል፡፡
በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አህመዲን መሐመድ በወቅቱ ለጋዜጠኞች እንዳሉት የክልሉ ሰላም መደፍረስ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፣ ሆኖም በተቃራኒ ጎራ የተሰለፉ ያሏቸው አካላት ለሰላም ዝግጁ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ምስል Alemnew Mekonnen/DW

በአማራ ክልል 1ሺህ 226 ፋብሪካዎችና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ሥራ አቁመዋል

በአማራ ክልል በተፈጠረው የሰላም መደፍረስ ምክንያት ባለፉት ሁለት ወራት ከ1,200 በላይ ፋብሪካዎች ስራ ማቆማቸውን የአማራ ክልል መንግሥት አስታወቀ፣ በበሕር ዳር ከተማ የሚገኙ ፋብሪካዎች ደግሞ ጥሬ እቃ ለማስገባትና ምርት ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለመላክ የመንገድ በተደጋጋሚ መዘጋት ለስራቸው እንቅፋት መሆኑን ተናግረዋል፣ የአማራ ክልል ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ትናንት በባሕር ዳር የሚገኙ አንዳንድ ፋብሪካዎችን ጎብኝተዋል፡፡ ከሐምሌ 2015 ዓ ም መጨረሻ ጀምሮ በአማራ ክልል በፋኖና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በተፈጠረው ጦርነት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ከፍተኛ ላይ ጉዳቶች ደርሰዋል። በሰሜን ሸዋና በአብዛኛው በምዕራብ አማራ የሚገኙ 1 ሺህ 226 ከፍተኛ፣ መካከለኛና አነስተኛ ኢንዳስትሪዎችና በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞቻቸው ሥራ ማቆማቸውን የአማራ ክልል ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ በተለይ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡ በአማራ ክልል የኢንተርኔት መቋረጥ በባንክ አገልግሎት፣ በግብረ ሰናይ እና የምርምር ሥራዎች ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ

የሰሜን ቀጠና ባኢካ ኢንዱስትሪ ጠቅላላ የንግድ ድርጅት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ሞላ ባይሌ፣ ምንም እንኳ ቀደም ሲል ወደ ፋብሪካቸው የገባ ጥሬ እቃ ቢኖርም ምርት ወደ ውጪ አውጥቶ ለመሸጥ የመንገዶች በፀጥታ ሁኔታ መዘጋጋት ተፅእኖ ፈጥሯል ብለዋል።
ከሐምሌ 2015 ዓ ም መጨረሻ ጀምሮ በአማራ ክልል በፋኖና በመከላከያ ሠራዊት መካከል በተፈጠረው ጦርነት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ከፍተኛ ላይ ጉዳቶች ደርሰዋል። በሰሜን ሸዋና በአብዛኛው በምዕራብ አማራ የሚገኙ 1 ሺህ 226 ከፍተኛ፣ መካከለኛና አነስተኛ ኢንዳስትሪዎችና በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞቻቸው ሥራ ማቆማቸውን የአማራ ክልል ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ በተለይ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል፡፡ምስል Alemnew Mekonnen/DW

የሰሜን ቀጠና ባኢካ ኢንዱስትሪ ጠቅላላ የንግድ ድርጅት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ሞላ ባይሌ፣ ምንም እንኳ ቀደም ሲል ወደ ፋብሪካቸው የገባ ጥሬ እቃ ቢኖርም ምርት ወደ ውጪ አውጥቶ ለመሸጥ የመንገዶች በፀጥታ ሁኔታ መዘጋጋት ተፅእኖ ፈጥሯል ብለዋል። የመብራት መቆራረጥ ደግሞ ሌላው ለሥራቸው ከፍተኛ ጫና እንደፈጠረባቸው አመልክተዋል፡፡ባሕር ዳር የሚገኘው የአዮዲን ጨው አምራች ፋብሪካ የጥራት ቁጥጥር ኃላፊ አቶ አወቀ ዓለማየሁ ግብዓት ወደ ፋብሪካው ለማስገባት የትራንስፖርት አማራጭ ቸግር እንደሆነባወቸው አመልክተዋል።ትናንት በፋብሪካዎች ጉብኝት ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዱ ሁሴን በበኩላቸው በመንገዶች መዘጋት ፋብሪካዎቹ ጥሬ ምርት ማስገባትና ምርት ማሰራጨት እንዳልቻሉ መረዳታቸውን ገልጠዋል፡፡አማራ ክልል ሰዎች በድርቅ የተነሳ እየሞቱ ነው

ትናንት በፋብሪካዎች ጉብኝት ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዱ ሁሴን በበኩላቸው በመንገዶች መዘጋት ፋብሪካዎቹ ጥሬ ምርት ማስገባትና ምርት ማሰራጨት እንዳልቻሉ መረዳታቸውን ገልጠዋል፡፡
የመብራት መቆራረጥ ደግሞ ሌላው ለሥራቸው ከፍተኛ ጫና እንደፈጠረባቸው አመልክተዋል፡፡ባሕር ዳር የሚገኘው የአዮዲን ጨው አምራች ፋብሪካ የጥራት ቁጥጥር ኃላፊ አቶ አወቀ ዓለማየሁ ግብዓት ወደ ፋብሪካው ለማስገባት የትራንስፖርት አማራጭ ቸግር እንደሆነባወቸው አመልክተዋል።ምስል Alemnew Mekonnen/DW

በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አህመዲን መሐመድ በወቅቱ ለጋዜጠኞች እንዳሉት የክልሉ ሰላም መደፍረስ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፣ ሆኖም በተቃራኒ ጎራ የተሰለፉ ያሏቸው አካላት ለሰላም ዝግጁ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዱ ሁሴን፣ ከመብራት መቆራረጥ ጋር ያለውን ችግር ለመፍታት ከሚመለከተው አካል ጋር በጋራ እየተሰራ ነው ብለዋለ፣ የክልሉን ሰላም ወደ ነበረበት ለመመለስም ሁሉም የክልሉ ነዋሪዎች እንዲተባበሩ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጠይቀዋል፡፡

ዓለምነው መኮንን

ኂሩት መለሰ

እሸቴ በቀለ