1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለፓሪስ ኦሎምፒክ ተፎካካሪ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ደማቅ አቀባበል

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 23 2016

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ ዛሬ ሲገቡ በሻርል ደጎል አውሮፕላን ማረፊያ በፓሪስ እና አካባቢው በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ። የፓሪስ ኦሎምፒክ 2024 ባለፈው ዐርብ በይፋ ተጀምሯል ። የተወሰኑ ሃገራትም በሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት ጀምረዋል ።

https://p.dw.com/p/4ivGx
Olympia 2024 | Äthiopiens Olympia-Team kommt in Paris an
ምስል Haimanot Tiruneh/DW

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ ዛሬ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ ዛሬ ሲገቡ በሻርል ደጎል አውሮፕላን ማረፊያ በፓሪስ  እና አካባቢው በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ። 

የፓሪስ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ በአውሮፕላን ማረፊያው በመገኘት አትሌቶቹን እና የልዑካን ቡድን አባላትን አነጋግራለች ።

የፓሪስ ኦሎምፒክ 2024 ባለፈው ዐርብ በይፋ ተጀምሯል ። የተወሰኑ ሃገራትም በሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት ጀምረዋል ።

ኢትዮጵያም በፓሪስ ኦሎምፒክ ተሳታፊ በሆነው የኦሎምፒክ ቡድኗ ሜዳሊያ ልታስመዘግብበት በሚጠበቀው የወንዶች የዐሥር ሺህ ሜትር ሩጫ ፉክክር ተሳታፊ የሆኑ አትሌቶች እና በሌሎች ርቀቶች በማጣሪያ  የሚሳተፉ ተፎካካሪ አትሌቶች ዛሬ ማለዳ ፈረንሳይ ፓሪስ ገብተዋል ።

ለአትሌቶቹ እና አብረዋቸው ለተጓዙ ልዑካን ቡድኖች በሻርል ፈጎል ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊፊያ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በአውሮፕላን ማረፊያው በፓሪስ  እና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። የአበባ ሥጦታም አበርክተውላቸዋል።  

ሃይማኖት ጥሩነህ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ