1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፈንድቃ የኪነ-ጥበብ ማዕከል እንዳይፈርስ ጥሪ ቀረበ

ሐሙስ፣ ሰኔ 15 2015

የአዲስ አበባ ብሎም የኢትዮጵያ አንዱ ድምቀት የሆነዉ ፈንዲቃ የባህል ማዕከል የኢትዮጵያን ሕዝብ የጋራ ባህል፤ እውቀት፣ ታሪክና የአብሮነት መገለጫዎች በሙዚቃ፣ በባህላዊ ውዝዋዜ፣ በሥነ-ሥዕል፣ በሥነ-ጽሑፍ እና በተያዩ ኪነ-ጥባባዊ ክንዋኔዎች የሚያስተዋውቀዉ ማዕከል ፍረስ መባሉን ብዙዎችን አስደንግጧል አሳዝኗል።

https://p.dw.com/p/4Sxik
Fendika Cultural Center Faces Imminent Demolition
ምስል Meleku Belaye/DW

«የቱሪስቶች መዳራሻና የአገር በጎ ገጽ ግንባታ ማዕከል፣ ይፍረስ መባሉ ብዙዎችን አስደንግጧል አሳዝኗል።»

« ፈንድቃን ማፍረስ የማህበረሰቡን ብዙ ነገር ማፍረስ ነዉ። ፈንድቃ ዘር የለዉም፤ ፈንድቃ ኢትዮጵያን የያዘና ሁሉን ያቀፈ ነዉ።» 

Moers Festival 2021 | Fendika und Han Bennink
ፈንድቃ በጀርመን ታዋቂ የጃዝ ፌስቲቫል ላይ ምስል Kurt Rade

አዲስ አበባ እምብርት ካዛንችስ ላይ የሚገኘዉ የፈንዲቃ የባህል ማዕከል ባለቤት ሎሬት መላኩ በላይ ከተናገረዉ የተወሰደ ነዉ። አርቲስ መላኩ በላይ ፤ ከጎዳና ሕይወት በመነሳት ከታዳሚዎች በሚያገኛት የሽልማት ገንዘብ ትምህርቱን የተማረ፤ ሕይወቱን የቀየረ መሆኑ ላለፉት በርካታ ዓመታት ሲነገር ሲዘገብ ቆይቷል። ታዋቂዉ የባህል ተወዛዋዥ መላኩ በላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ የጀመረባትን የፈንድቃ የባህል ምሽት ቤት፤ ከስምንት ዓመታት በፊት ገዝቶ ወደ ባህል ማዕከልነት ማሻገር የቻለ ወጣት ነው፡፡ ይሁንና ሰሞኑን የኪነ-ጥበብ ባለሞያዉ መላኩ በላይ ያቋቋመዉ ይህ የባህል ማዕከል፤ ለልማት በሚል ከመንግሥት የመፍረስ ትዕዛዝ እንደወጣበት ተነግሯል።

Äthiopien Fendika Cultural Center
ሎሬት መላኩ በላይ ከአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ከማይክ ሐመር ጋር ምስል Meleku Belaye

 

የአዲስ አበባ ብሎም የኢትዮጵያ አንዱ ድምቀት የሆነዉ ፈንዲቃ የባህል ማዕከል የኢትዮጵያን ሕዝቦች ሁሉ የጋራ ባህል፤ እውቀት፣ ታሪክና የአብሮነት መገለጫዎች በሙዚቃ፣ በባህላዊ ውዝዋዜ፣ በሥነ-ሥዕል፣ በሥነ-ጽሑፍ እና በተያዩ ኪነ-ጥባባዊ ክንዋኔዎች የሚያስተዋውቅ፤ የበርካታ አገራት ቱሪስቶች መዳራሻ እና የአገር በጎ ገጽ ግንባታ ማዕከል፣ እንዲሁም የወጣቶች የዕውቀት ማበልፀጊያና የልምድ መለዋወጫ ማዕከል፤ በመሆኑ በሃገር ዉስጥብ ብሎም በተቀረዉ ዓለም ይታወቃል። ፈንድቃ ይፍረስ መባሉን ሰምተን ለፈንድቃ ባለቤት ሎሬት መላኩ ስልክ ደዉለን በጠየቅነዉ ጊዜ፤  ፈንድቃ ባህል ማዕከል የህዝብ ነዉ ሲል ነዉ የተናገረዉ።

Deutschland | Moers Festival in Deutschland | Äthiopiens Gamo-Kultursänger
መላኩ በላይ ከጋሞ ብሔረሰብ አባላት ጋር በጀርመን ምስል Melaku Belay

« አሁን ያለዉ ነገር ገሃድ የወጣ እና፤ እኔን የሚያሸማቅቅ ምንም ነገር የለም። ፈንድቃ ከእኔ አልፎ የህዝብ እንደሆነ፤በተፈጠረዉ ሁኔታ መስክሯል። ሁሉም ኢትዮጵያዉያን፤ ሁሉም አለም አቀፍ ዲፕሎማቶች፤ ናቸዉ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ስለፈንድቃ እየመሰከሩ ያሉት።»  

Äthiopien Fendika Cultural Center
ሎሬት መላኩ በላይ ከሆላንድ የክብር ሽልማትን ሲቀበልምስል Meleku Belaye

ሎሬት መላኩ እስቲ የተፈጠረዉን ነገር አጫዉተን ?

«ፈንድቃ የተፈጠረዉ ነገር፤ ስገዛዉ በሊዝ ነዉ። ሊዝ ማለት፤ 90 ዓመት ኮንትራት ከመንግስት ጋር መያዝ ነዉ። የ 30 ዓመት  ክፍያ ነበረዉ ፤ አስቀድሜ ከፍዬ የሰርተፍኬት ሽልማት ተከፍያለሁ።»

አንድ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተጠቃሚ በጻፉት አስተያየት፤

Deutschland | Moers Festival in Deutschland | Äthiopiens Gamo-Kultursänger
ፈንድቃ ከጋሞ ብሔረሰብ አባላት ጋር በጀርመን ምስል Melaku Belay

«ዋናው ቁም ነገር፤ ፈንድቃ የሚለው ሃሳብ በዓለም የትም ቦታ መልሶ መቁዋቁዋም በሚያስችለው ደረጃ የታማኝነት እዉቅና አግኝቷል ፤ ፈጥሩዋል። ይህ  በታላቅ ጥረት የሆነ ነገር ነው። የሚያሳዝነው: ካዛንቺስ "አዝማሪ ቤቶች" የኢትዬጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ሚና የተጫወቱ ሲሆኑ፤ ፈንዲቃ ብቸኛው የዛ ታሪክ አስተዋሽ ባለታሪክ በመሆኑ በማትረፍ ፈንታ ለማፍረስ መቸኮሉ ነው። ይህ የማገናዘብ ጉድለት መኖሩን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ምልክት ነው፤ ሲሉ አስተያየታቸዉን ጽፈዋል። በኢትዮጵያ የተለያዩ ሃገራት አምባሳደሮች የባህል ድልድይ የሆነዉ ፈንድቃ መነሳት ክስረት ፤ ሃገርን የሚጎዳ ሲሉ አስተያየታቸዉን ጽፈዋል።  አርቲስት መላኩ በላይ ወደሚያስተዳድረዉ የባህል ማዕከል በየዓመቱ ወደ 200,000 ጎብኚዎች ይመጣሉ። አርቲስ መላኩ በጣሊያን ስታር 2022፣ በቲኤዲ ህብረት 2022፣ በፕሪንስ ክላውስ ሎሬት 2020፣ ለሙዚቃ ቪዛ 2019 እና በፈረንሣይ ሜዳሊያ 2015 ተሸልሟል። አዲስ አበባ ልማት እንደሚያስፈልጋት በመረዳት በፈንድቃ ደመቅ ያለ ኢትዮጵያዊ ባህል እየተጋራን አካባቢውን ለማልማት የቢዝነስና የሕንፃ ፕላን አዘጋጅተናል። ዕቅዱ አሁን በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ፀድቋል ሲል አርቲስት መላኩ ተናግሯል።

Äthiopien Fendika Cultural Center
ሎሬት መላኩ በላይ ከፈረንሳይ አምባሳደር ሽልማት ሲቀበልምስል Meleku Belaye

የጃዛምባ ሙዚቃ ትምህርት ቤት መስራች፣ እና እዉቁ የጃዝ ጊታር ተጫዋች ሄኖክ ተመስገን፤ ፈንድቃ ይፈርሳል የሚለዉን ጉዳይ ሰምቶ በጥልቅ ማዘኑን ተናግሯል። “ፌንዲካ ለእኔ ትልቅ ትርጉም ያለዉ ማዕከል ነዉ፤ የመፍረሱ ዜና በእውነት አሳዛን ነው“

Äthiopien Fendika Cultural Center
ሎሬት መላኩ በላይ በኢትዮጵያ ከጣልያን አምባሳደር ጋር ምስል Meleku Belaye

ሄኖክ የዓለም አቀፍ የሙዚቃ ባንዶች በፈንዲቃ ትዕይንት ለማየትም ሆነ ለመሳተፍ ቅድሚያ እንደሚሰጡ እና ማዕከሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን እውቅና እና ዝና አጉልቶ አሳይቷል። ፈንድቃ ለባህል እና ኪነ-ጥበብ  አድናቂዎች እና ብሎም ለጎብኝዎች ዋነኛ ማዕከል መሆኑን፤ ለከተማዋ ብሎም ለሃገሪቱ የጥበብ ገጽታ አስተዋፅዖ ማድረጉንም አክሏል።

 

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ