ጦርነቱን ለማብቃት የመፍትሄ ሀሳቦችና የመንግሥት አቋም
ሰኞ፣ ጥቅምት 29 2014ማስታወቂያ
መንግሥት በሰሜን ኢትዮጵያ ከሕወኃት ጋር እያደረገ ባለው ጦርነት እስካሁን የወሰደው ምንም አይነት የአቋም ለውጥ አለመኖሩ ተገለጸ። የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሣ በአፍሪካ ሕብረት ማዕቀፍ ስር እየተንቀሳቀሰ ላለው ልዑክ ቡድን በመርህ ደረጃ ኢትዮጵያ ድጋፍ እያደረገች መሆኑን ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። ሆኖም እስካሁን የቀረበ የመፍትሄ ሀሳብ አለመኖሩን አስታውቀዋል። ባለፈው ሐሙስ እና ዓርብ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተው የተመለሱት በአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ አምባሳደር ጀፈሪ ፌልትማን ስላደረጉት ምክክር ፍሬያማነትም ተጠይቀው፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሕብረት በኩል ለሚቀርበው የመፍትሄ ሀሳብ ቅድሚያ ትሰጣለች ነው ያሉት። ስለጦርነቱ መፍተሄ የተጠየቁት አንድ ባለሙያ በበኩላቸው ዘላቂ መፍትሄ የሚያመጣን ድርድር ለማድረግ ተጠያቂዎች መኖር አለባቸው ይላሉ።
ስዩም ጌቱ
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ