ጀርመን፤ የጃዋር መሐመድ የምስጋና ጉዞ
ቅዳሜ፣ ግንቦት 27 2014ማስታወቂያ
ይህ የጉዟቸው አንደኛው አላማ ሲሆን ሌላኛዋ አላማ በብዙ ውጥንቅጥ ውስጥ የምትገኘው ኢትዮጵያ ላይ ሰላም እንዲሰፍን ለማስቻል በሚደረግ ጥረት ውስጥ ደጋፊዎቻቸው የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ለማሳሰብ ነው ተብሏል። ጉብኝታቸው አውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካን የሚያካልል ሲሆን በቀጣይ ደግሞ ፈረንሳይ፣ ኔዘርላንድስ እና ቤልጄም ከመሳሰሉ የአውሮፓ ሀገራት ከደጋፊዎቻቸው ጋር ከተገናኙ በኋላ ወደ ሰሜን አሜሪካ እንደሚያቀኑ ስብሰባውን እየተከታተለ የሚገኘው የዶይቸ ቬለ ባልደረባ ታምራት ዲንሳ ዘግቧል። አቶ ጃዋር መሐመድ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ ለሁለት ዓመት ገደማ ያህል በእስር ላይ መቆየታቸው ይታወሳል።
ታምራት ዲንሳ
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ልደት አበበ