1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን ለፍልስጥኤም ትሰጥ የነበረውን የልማት ዕርዳታ ልታጤን ነው

ሐሙስ፣ ጥቅምት 1 2016

ጀርመን ለፍልስጥኤም ትሰጥ የነበረውን የልማት ዕርዳታ ልታጤን መሆኑን አስታወቀች። የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ ዛሬ ለፓርላማው ባደረጉት ንግግር ሃገራቸው ለፍልስጥኤማውያን የምትሰጠው የልማት ዕርዳት ለታጣቂዎች እንደማይደርስ ማረጋገጥ ትሻለች ።

https://p.dw.com/p/4XSuu
Bundestag | Olaf Scholz - Regierungserklärung zur Lage in Israel
ምስል Bernd von Jutrczenka/dpa/picture alliance

ጀርመን ፍልስጥኤም ትሰጥ የነበረውን የልማት ዕርዳታ ልታጤን ነው

ጀርመን ለፍልስጥኤም ትሰጥ የነበረውን የልማት ዕርዳታ ልታጤን መሆኑን አስታወቀች። ዩናይትድስቴትስ እና ጀርመንን ጨምሮ አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት በሽብርተኝነት የፈረጁት የፍልስጥኤም ታጣቂ ቡድን ሃማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት መስንዘሩን ተከትሎ በጀርመን ፍልስጥኤም የትብብር ግንኙነት ላይ እንደሚያጠላ ተገለጿል።  የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ ዛሬ ለፓርላማው ባደረጉት ንግግር ሃገራቸው ለፍልስጥኤማውያን የምትሰጠው የልማት ዕርዳት ለታጣቂዎች እንደማይደርስ ማረጋገጥ ትሻለች ።በውዝግብ የታጀበው የኔታንያሁ የበርሊን ጉብኝት ጀመራሄ መንግስት ሾልዝ ሃማስ በእስራኤል ላይ ፈጽሟል ላሉት ጥቃት ድጋፍ በመስጠቷ ኢራንን እንዲሁም  የፍልስጥኤሙን ፕሬዚዳንት መሐሙድ አባስን ወቅሰዋል።  ፕሬዚዳንት አባስ ታጣቂ ቡድኑን  በግልጽ አላወገዙም በሚል ነው ከወደ ጀርመን ወቀሳው የቀረበባቸው ።

የጀርመን ፓርላማ በስብሰባ ላይ
ጀርመን ለፍልስጥኤም ትሰጥ የነበረውን የልማት ዕርዳታ ልታጤን መሆኑን አስታወቀች። ዩናይትድስቴትስ እና ጀርመንን ጨምሮ አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት በሽብርተኝነት የፈረጁት የፍልስጥኤም ታጣቂ ቡድን ሃማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት መስንዘሩን ተከትሎ በጀርመን ፍልስጥኤም የትብብር ግንኙነት ላይ እንደሚያጠላ ተገለጿል።ምስል Michael Kappeler/dpa/picture alliance

ይልማ ኃይለሚካኤል

ታምራት ዲንሳ 

እሸቴ በቀለ