ፖለቲካእስያ
ጀርመን ለዩክሬን የምታቀብላቸው ረቂቅ ጦር መሣሪያዎች
ሐሙስ፣ ግንቦት 25 2014ማስታወቂያ
የጀርመን መንግሥት ረቂቅ የጦር መሣሪያዎችን ለዩክሬን ለማቀበል ቃል መግባቱ ተሰምቷል። ረቂቅ የጦር መሣሪያዎቹ የመካከለኛ ርቀት ተወንጫፊ ሮኬቶችን ያካትታል ተብሏል። ከጀርመን ባሻገር ዩናይትድ ስቴትስም ለዩክሬን ሌሎች ዘመናዊ እና ረቂቅ ጦር መሣሪያዎችን አቀርባለሁ ብላለች። የጀርመን እና ዩናይትድ ስቴትስን ውሳኔ በመከተል ብሪታንያም ዘመናዊ ጦር መሣሪያዎችን ለዩክሬን በማቀበሉ በኩል አለሁበት ብላለች። የሩስያ መንግሥት በክሬምሊን ቤተመንግሥት ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ በኩል ዛሬ ባወጣው መግለጫ የምዕራቡ ዓለም መንግስታት ለዩክሬን ጦር መሣሪያ ማቀበላቸው «ለዩክሬናውያን ተጨማሪ መከራን የሚያመጣ ነው» ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ይህን በተመለከተ ከበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ጋር ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ቃለ መጠይቅ አድርጌ ነበር።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ