1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፔሎሲ ጉብኝት የቀሰቀሰው የቻይና የጦር ልምምድ

ሰኞ፣ ነሐሴ 2 2014

እሁድ ዕኩለ ቀን ያበቃል ተብሎ የነበረውና ቻይና በታይዋን ዙሪያ የምታካሒደው ወታደራዊ ልምምድ ቀጥሏል። ልምምዱ የተጀመረው የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት ቻይናን በማስቆጣቱ ነበር።ታይዋን የውጊያ ልምምዱን ለወረራ መዘጋጃ አድርጋለች ስትል ቻይናን ከሳለች። ወታደራዊ ልምምዱ ጸረ ሰርጓጅ መርከብ የጦር መሳሪያዎች ጨምሯል

https://p.dw.com/p/4FGzl
China fliegt weitere Manöver über Taiwan
ምስል Gong Yulong/Xinhua/Xinhua News Agency/picture alliance

ማኅደረ ዜና፦ የፔሎሲ የታይዋን ጉብኝት የቀሰቀሰው የቻይና የጦር ልምምድ

በሳምንቱ መጨረሻ  ቻይና የግዛቴ አካል ናት በምትላት ታይዋን ሰማይና ባህር ላይ  ያሳየችው ወታደራዊ ልምምድና ያሰወነጨፈቻቸው ሚሳይሎች ፤ አካባቢውን የጦር ቀጣና አድርገውት ነው የሰነበቱት። ቻይናን መሳሪያ ያስመዘዘውና ሀይል ጉልበቷን ለወዳጅ ጠላት ለማሳየት ያስገደዳት የአሜሪካዋ አፈጉባኤ ወይዘሮ ናንሲ ፔሎሲ ባለፈው ማክሰ|ኞና እሮብ በታይዋን ያደረጉት ጉብኝት መሆኑ ተገልጿል።  

የአፈጉባኤ ፔሎሲ ጉብኝት ምንነት፤ የቻይና ቁጣና ዛቻ እንዴትነትና በታይዋን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ የሚኖረው ወሳኘነት የዛሬው የዜና ማህደር ትኩረት ነው፤ አብራችሁን ቆዩ።  
 የ82 አመቱ ነባር ፖለቲከኛ አፈጉባኤ ናሲ ፔሎሲ ከጥቂት የምክርቤት አባሎቻቸው ጋር ባለፈው ማክሰኞ ምሽት ዋና ከተማ ታይፔ ገብተው በማግሱት የተመለሰበት አጭር የታይዋን ጉብኝት ይህን ያህል ውዝግብ መፍጠሩና ሚሳይልና ጄቶች ማሰለፉ ሊገርም ይችላል። ሆኖም ግን ቻይና ገና ከጅምሩ የአፈጉባኤዋ ጉብኝት ሌላ ትርጉም ያለውና የግዛቷንም አንድነት ጥይቄ ውስጥ የሚያስገባ መሆኑን በመግለጽ መቃወሟን፣ እንዲሁም በአሜሪክና ቻይና መካከል ያለውን ፍክክርና  ውድድርም ሲከታተል ለቆየ  ይህ ክስተት የሚያስደንቀው እይሆንም። 

China | Taiwan | Militärische Übungen Chinas vor Taiwans Küste
ምስል Photo by various sources/AFP

ዛሬ 23 ሚሊዮን ህዝብ ያላትና የዳበረ ካፒታሊዝም እንደገንባች የሚነገርላት ታይዋን፤ እ እ እ በ1949 ዓም ዋናውን ቻይና በሊቀመንበር  ማኦሴቱንግ የሚመራው የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ሰራዊት ሲቆጣጠረው፤ ተሸናፊው የያኔው የቻይና መሪ ቺያንካይ ቼክና ፓርቲያቸው ኩሚንታግ ወደ ደሴቱቱ በማፈግፈግ የስደት መንግስት የመሰረቱባት ነበረች። ያያኔው ኮሚኒስቶች እንቅስቅሴና ድል ያሰጋቸው ምዕራባውያን በታይዋን የቻይና የስደት መንግስትን ይሁንታና ድጋፍ ስጥተውት ቆይተዋል። እ እ እ በ1971 አም በቻይና እስከ ተተካችበት ጊዜ  ድረስም ታይዋን በመንግስታቱ ድርጅት የቻይና ህጋዊ ተወካይ ሁና ነበር የቆየችው። ከዚያ በኋላ ግን ታይዋን ከጥቂት በጣት ከሚቆጠሩ አገሮች በስትቀር ሉዑላዊ አገር ተብላ አትታውቅም። ቻይናም፤ አገሮች ከታይዋን ጋር የባህል፣ የንግድና ኢኮኖሚ ግኝኑነት ከማድረግ ባለፈ፤ ያገራዊ ዕውቅና የሚሰጡ ከሆነ አጥብቃ ስትቃወም ነው የቆየችው። በዚህም ምክኒያት ብዙዎቹ አገሮች አሜርካንን ጨምሮ፤ የቻይናን መንግስት  ታይዋንን የሚጨምረውን አንድ ቻይና ፖሊሲ ተቀብለው በተለያየ ደረጃም ቢሆን ከሁለቱም ጋር ሲሰሩ ነው የቆዩት። ይሁን እንጂ በታይዋን ነጻነትን የሚሹና አገር መሆኑን የሚመኙ ዜጎች እንዳሉም ነው የሚታወቀው። በተለይ ባለፈው ምርጫ ወደ ስልጣን የመጡት ፕሪዝዳንቷ ወይዘሮ ሳኢ ኢንግ ዌንና ፓርቲያቸው ፕሮግሬሲቭ ፓርቲ፤ ታይዋን  ነጻ አገር እንድትሆን የሚፍለጉና ጉድኝታቸውም ይበልጥ ከአሜሪካ ጋር እንደሆነ ነው የሚሚታወቀው።  አሜሪካም በመርህ ደርጃ የአንድ ቻይናን ፖሊሲ አራምዳለሁ ትበል እንጂ፤ በተለይ በአሁኑ ከቻይና ጋር ባለው ውድድርና ፉክክር ምክኒያት፤ የታይዋንን ነጻነት የመደገፍ አዝማሚያ እንዳላት ነው በብዙዎች ዘንድ በተለይም በቻይና የሚታመነው።  

በአሜሪካ መንግስት ሁለተኛዋ ከፍተኛ ባለስልጣን እንደሆኑ የሚነገርላቸውና የፕሬዝድንቱ የፖሊቲካ አጋር የሆኑት ወይዘሮ ናንሲ የታይዋን ጉብኝት፤ ከቻይና ብርቱ ተቃውሞ የገጠመውም የጉብኝቱ አንደምታ የቻይናን ሉዑላዊነት የሚጥስና ለታይዋን የነጻነት ፋላጎት በር የሚከፍት ነው ተብሎ እንደሆነ  ግልጽ ነው።  ወይዘሮ ናንሲም በተቃውሞ መሀልም ቢሆን ወደ ታይፔ ከዘለቁ በኋላ ከታይዋን ባለስልጣኖች ጋር ያደረጓቸው ውይይቶችና ያሰሟቸው ንግግሮች የቻይናዎቹን ጥርጣሬ የሚያረጋግጥ ሆኖ ታይቷል። “ወደዚህ የመጣንበት ምክኒያት ለታይዋን ያለንን ያማያወላውል ድጋፍ ለመግለጽ ነው” በማለት ያሰሙት ንግግር ቻይና የአፈጉባኤዋን ግብኝት የተቃወመችበትን ምክኒያት ትክክለኝነት የሚያሳይ ተደርጎ  በብዙዎች ዘንድ ተወስዷል።  

BG: Alltag in Taiwan
ምስል ANN WANG/REUTERS

ወይዘሮ ናንሲ ገና ጉብኝታቸውን ሳይጨርሱ ግን፤ ቻይና ከፍተኛ የሆነ ወታደራዊ ሀይሏን በታይዋን ባህርና ሰማይ ላይ በማሰማራት፤ ደሲቲቲን ኢላማ ውስጥ በማስገባት የሚሳይል የተኩስ ጭምር የሚሰማበት  የጦር ልምምድ ስታደርግ ነው የስነበተችው።፡ በወይዘሮ ናንሲና  ቤተሰባቸው ላይም የጉዞ እገዳ ያደረገች ሲሆን፤ በኣየር ነብርትና ወታደራዊ ጉድዮች በመሳሰሉ ከአማሪካ  ጋር የነበራትን የግንኑነት መስመሮችን ማቋረጧንም አስታውቃለች።  በታይዋንም በአንዳንድ ሸቆጦች ላይ የማዕቀብ ውሳኔ የተላለፈ ሲሆን፤ የእያክባቢው ንግድም በዚሁ እንቅስቅሴ ታውኮ ነው የክረመው። ይህ የቻይና ፈጣን እርምጃና የተፈጠረው የፖለቲካ ትኩሳት ለአንድንዶች በሩቅ ምስራቅም ሌላ ዩክሬን እንዳይፈጠር የሚያሰጋ ሁኗል።  ቀድሞ የሲንጋፖር የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ባለሙያ የንበሩትና ያአካብቢውን ፖለቲካ የሚከታተሉት ሚስተር ቢላሃሪካውሲካ በቁጣናው ለተክሰተው  ውጥረትና ቀውስ  አፈጉባኤ ናንሲ ፖሊስን ተጠያቂ ያደርጋሉ። “ለታይዋን  ድጋፍን ለማሳየት፤ ካፈጉባኤዋ  ጉብኝት የበለጡና የተሻሉ በርክታ መገዶች ነበሩ” በማለት እንደውም ጉብኝቱ  ወደፊት አሜሪካም ሆነች ሌሎች ለታይዋን ሊሰጡ የሚችሉትን እርዳታና ድጋፍ የሚያደናቅፍ ነው በማለት እርምጃውን ፖለቲካዊ  ስህተት ብለውታል። 

ቀድሞ የአውስትራሊያ ጠቅላይ ሚኒስተር የነበሩት ሚስተር ኬቪን ሩድም ቻይና የፔሎሲን ጉብኝት አሜሪካ እ እ በ1982 የተቀበለችውን የአንድ ቻይና ፖሊሲ እንደተወቸው አድርጋ እንድታይ የሚይደርጋት ሊሆን ይችል ሲሉ፤ እሳቸውም ጉብኝቱ አሁን ለተፈጠረው ችግር ብቻ ሳይሆን ለወደፊትም ሊከሰቱ ለሚችሉ ችግሮች ምክኒያት ሊሆን እንደሚችል ነው ያሳሰቡት  
ሚስተር ሂንርይ ኩያኑ ዋንግ  በፔጂንግ ሴንተር ፎር ቻይና ግሎባላይዜሺን  የተባለ ድርጅት ፕሬዝዳንት፤ የአፈጉቤዋ ጉብኝት ላለፉት አርባና አምሳ አመታት በሁለቱ አገሮች መካከል ተገንብቶ የነብረውን የዲፕሎማሲ ድልድይ የሰበረ መሆኑን በመግለጽ፤ ፡በተለይ በዚህ የሁለቱ አገሮች ግንኑነት ዝቅተኛ ደረጃ ላይ በሆነበት ግዜ መሆኑ፤ ሁለተኛ አለም በዩክሬን ቀውስና የሀይል እጥረት ተወጥሮ በተያዘበት ግዜ መሆኑ የበለጠ አስከፊ አድርጎታል ። ሚስተር ዋንግ አክለውም ወይዘሮ ናሲ በጸረ ቻይና አቋማቸው የሚታወቁ በመሆናቸው ጉብኝቱን ለአገር ውስጥ የፖለቲካ ፍጆታና ለግል ስሜት መግለጫ ተጠቅመውበታል ባይ ናቸው። በመጭው የአሜሪካ  የምክርቤት ምርጫ ፓርቲያቸው አብላጫ ድምጽ ያገኛል ተብሎ ስለማይጠበቅ ወይዘሮ ናንሲ ምናልባትም ከፖለቲካ ህይወታቸው እንኳ ባይሆን ከአፈጉቤነታቸው መነስታቸው የማይቀር በመሆኑ እንደተባለውም ይህን ግዜ አፈጉቤዋ የግል ወይም የፓርቲያቸውን የፖለቲካ ፍላጎት ለማራመድ ሳይጠቀሙበት አልቀሩም።  
የአሜሪካ መንግስት ባለስልጥናት ግን የወይዘሮ ናሲ ጉብኝት አሜሪካ በቻይናም ሆነ በታይዋን ላይ ያላት ፖለሲ መለወጡን አያሳይም ነው የሚሉት። የኋይት ሀውስ ቃል አቀባይ፤ በአካባቢው የተፈጠረው ውጥረትና በዚህ ምክኒያትና ቻይና አሁን እየወስደችው ባለው እርምጃ ማንም ተጠቃሚ አይሆንም በማለት፤ አሜሪካ ባንድ ቻይና ፕሊሲዋ ላይ  ምንም አይነት ለውጥ ያላደረገች መሆኑን ነው አጠንክረው የገለጹት ። 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንም አሜሪካ በአፈጉቤዋ የታይይዋን ጉብኝት ቀውስ እንዲፈጠር የማትፈልግ መሆኑን በመግለጽ፤ ቻይና ውጥረት ከሚፈጥሩ  እርምጃዎች እንድትቆጠብ አሳስበዋል። ፡የወይዘሮ ናንሲ ጉብኝት ሰላማዊ መሆኑ ግልጽ ነው። ያልተመጣጠነና  ነገሮችን የሚያባብሱ  እርምዳዎችን ለመውሰድ የሚይስችል ምንም አይነት አሳማኝ ምክኒያት የለም” ፤በማለት ቻይና ያቋረጠቻቸውን የግንኑነት መስመሮችንም እንድትቀጥል ጭምር ጠይቀዋልል። በክምቦድያው የደቡብ ምስራቅ እስያ አገሮች ስብሰባ ከተገኙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ውስጥ ፤ ከአውትራሊያና ጃፓን ሚኒስትሮች ጋርም የጋራ መገለጭ በማውጣት የቻይናን እርምጃ ኮንነዋል። ቻይና ለዚህ መግለጫ አጸፋ በሚመስል መልኩ ከአውስትራሊያ ኤምባሲዋ ባወጣችው መግለጫ፤ አሚሪካ የማትታመንና ዋና ችግር ፈጣሪ ናት በማለት ቻይና ያሜሪካ የጠብ አጫሪ ባህሪ ሰለባ እንደሆነችና   የወስደችው እርምጃም ሉዑላዊነትና ለማስከበር የተወስደ እርምጃ መሆኑን አስታውቃለች።  

China / Japan Chinesische Raketen landen in Japans AWZ
ምስል Andre M. Chang/ZUMAPRESS.com/picture alliance


 በታይዋን ዙሪያና ሰማይ ላይ ሲካሄድ የቆየው  የጦር ልምምድ ትናንት ዕሁድ ዕኩለ ቀን ላይ እንደሚያበቃ ታቅዶ የነበር ቢሆንም፤ ሌላ ዙር የባህር ላይ የጦር ልምምድ ከዛሬ ጀምሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል። የተራዘመ የጦር ልምምድና የመሳሪያ ክምችት ከስጋት አልፎ ጦርነት ላለመቀስቀሱ ዋስትና የለም። ከሁሉም በላይ ታይዋን የቻይና ወታደራዊ እንቅስቃሴ የአካባቢውን ሰላም የሚያውክና አደገኛ የሆነ እርምጃ ነው በማለት ጩሀ  እይተናገረች ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሚስተር ጆሴፍ ዉ “ በጣም አደገኛ፤  ግጭት ቀስቃሽ፣ የአካባቢውን ሰላም የሚያደፍርስ የአለምን ንግድ ያሚያውክ” በማለት እንቅስቅሴው ፈጥኖ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል። ቻይና ግን  ሰሚ ጆሮ ያላት አይመስልም፤ የጦር መከቦቿን በታይዋን ባህር ማርመስመሷን እንደቀጠለች ነው፡፤ 

የቻይና የሰሞኑ ወታደራዊ እንቅስቅሴና ያሳየችው ዝግጁነት ባለሙያዎች እንደሚሉት ቻይና ለራሷም  መተማመንን የፈጠረላትና ታይዋንን በቀላሉ ለመክበብና ካስፈልገም በቁጥጥሩ ስር ለማድረግ የምትችል መሆኑን ያሳየችበት ነው ። በመሆኑም ታይዋን ከመቼውም ግዜ ይበልጥ በቻይና ቀለበት ውስጥ ናት እየተባለ ነው። ጥያቄው ግን ቻይና በወታደራዊ እርምጃ ታይዋንን  ለመቆጣጠርር ብትቃጣ” አሜርካስ በታይዋን ጎን ተሰልፋ ጣልቃ ተተገባ ይሆን? የሚለው ነው። ፕሬዝዳንት ባይደን ይህን ተጠይቀው ሲመልሱ “ ልክ ነው  ይህን ለማድረግ ቃል አገብተናል” ነው ያሉት። እናም ቻይና የግዝቴ አካል ናት በምትላትና በጦር ሀይሏ በክበበቻት ታይዋን ብትገባ፤ አሚርካም ዘላ በመግባት ደግሞ ሌላ ዩክሬን በታይዋን ይፈጠር ይሆን?‹። የሁሉም ስጋት ነው። 

ገበይው ንጉሴ 

እሸቴ በቀለ