1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢሰመኮ 53 ግለሰቦች አዋሽ አርባ መታሰራቸውን አረጋገጠ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 30 2015

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለን፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ ም/ቤት አባል አቶ ዮሐንስ ቧያለውን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት አባል ዶ/ር ካሣ ተሻገርን ጨምሮ 53 ሰዎች አዋሽ አርባ ውስጥ ባለ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ መታሰራቸው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አረጋገጠ።

https://p.dw.com/p/4VwIv
ፎቶ ከማኅደር፤ ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ተይዘው ደቡብ አፍሪቃ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለን፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለውን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ካሣ ተሻገርን ጨምሮ 53 ሰዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እዝ አዋሽ አርባ ውስጥ ባለ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ መታሰራቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አረጋገጠ። ፎቶ ከማኅደር፤ ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ተይዘው ደቡብ አፍሪቃ ምስል Kim Ludbrook/dpa/picture alliance

53 ሰዎች አዋሽ አርባ መታሰራቸው


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለን፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለውን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶ/ር ካሣ ተሻገርን ጨምሮ 53 ሰዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እዝ አዋሽ አርባ ውስጥ ባለ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕራብ ዕዝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ መታሰራቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አረጋገጠ። ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች የተቀብሩ ፈንጂዎች እንዲመክኑ ኢሰመኮ ጥሪ አቀረበበጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ የሰጡ የተቋሙ የሥራ ኃላፊ «የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ በሚቆይበት ጊዜ ሰዎችን ከማሰቃየት ተግባር የመቆጠብ፣ በሕይወት የመኖር መብትን የማስከበር እና በገለልተኛ አካል የመዳኘት መብትን የመሳሰሉ መብቶች መከበር እንዳለባቸው እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚፈቀዱ እርምጃዎች ቢኖሩ እንኳን የሕጋዊነት፣ የአስፈላጊነት እና የተመጣጣኝነት መርህን ማክበር አለባቸው» ብለዋል። ባለቤታቸው ነሐሴ 16 ቀን 2015 ዓ. ም ነው አዲስ አበባ ውስጥ ተይዘው ወደ አዋሽ አርባ መወሰዱን ከኮሚሽኑ መስማታቸውን የገለፁት ፖለቲከኛ ወይዘሮ ቀለብ ስዩም ባለቤታቸው ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸው መሆኑን በመግለጽ በማንነታቸው ብቻ መታሰራቸውን ገልፀዋል። የአቶ ክርስትያን ታደለ እና የዶክተር ካሳ ተሻገር ጠበቃ እስሩ ሕገ ወጥ ነው በሚል በፍርድ ቤት ጀምረውት የነበረው አካልን ነፃ የማውጣት ክስ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ድንጋጌ የሚሻር በመሆኑ ክሱን ለማቋረጥ መገደዳቸውን ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል። 

 ፎቶ ከማኅደር፤ የኢሰመኮ አርማ
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የሥራ ኃላፊ በጉዳዩ ላይ ለዶቼ ቬለ በሰጡት ተጨማሪ ማብራሪ «የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ በሚቆይበት ጊዜ ሰዎችን ከማሰቃየት ተግባር የመቆጠብ፣ በሕይወት የመኖር መብትን የማስከበር እና በገለልተኛ አካል የመዳኘት መብትን የመሳሰሉ መብቶች መከበር እንዳለባቸው እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚፈቀዱ እርምጃዎች ቢኖሩ እንኳን የሕጋዊነት፣ የአስፈላጊነት እና የተመጣጣኝነት መርህን ማክበር አለባቸው» ብለዋል። ፎቶ ከማኅደር፤ የኢሰመኮ አርማምስል Ethiopian Human Rights Commission


ሰለታሳሪዎች የኢሰመኮ የክትትል ግኝት ምን ይላል ?
ኢሰመኮ በአማራ ክልል የተደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ እስካሁን አደረግሁት ባለው ክትትል፣ ግኝቶች፣ እና ተያያዥ ጉዳዮች ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ጋር መወያየቱን አስታውቋል። ኮሚሽኑ የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ 53 ወንድ እስረኞች አዋሽ አርባ ውስጥ በሚገኝ ጊዜያዊ ማቆያ የሆነ ወታደራዊ ካምፕ መታሰራቸውን በአካል አመራሮቹ ተገኝተው መመልከታቸውን አረጋግጧል። በአዲስ አበባው የፌዴራል ፖሊስ ማቆያ ጣቢያ ከፍተኛ መጣበብ በመፈጠሩ ታሳሪዎቹ ወደዚያ ሥፍራ መወሰዷቸውን እንደተረዳም ኢሰመኮ ገልጿል።
«እጅግ አብዛኛዎቹ ታሳሪዎች ብሔራቸው አማራ፣ እምነታቸው ኦርቶዶክስ ክርስቲያን መሆኑንና ለእስር የተዳረጉት በብሔር ማንነታቸው ብቻ መሆኑን እንደሚያምኑ፣ ከፊሎቹ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተያዙበትና ቤታቸው በተበረበረበት ወቅት በራሳቸውና በቤተሰብ አባል ላይ ድብደባ፣ ብሔር ተኮር ስድብ፣ ማጉላላት፣ ዛቻና ማስፈራራት እንደደረሰባቸው ሆኖም በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ከሆኑ በኋላ የተፈጸመ ድብደባ ወይም አካላዊ ጥቃት አለመኖሩን፣ ከፊሎቹ በተለይም ከአማራ ክልል ተይዘው የመጡ ሰዎች ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ ቤተሰቦቻቸው የት እንዳሉ እንኳን እንደማያውቁ አስረድተዋል።» በማለት የኢሰመኮ መግለጫ አስታውቋል።ኢሰመኮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአማራ ክልል ብቻ እንዲወሰን ለመንግስት ጥሪ አቀረበ
ኮሚሽኑም ከፖሊስ ኃፊዎች ጋር ባደረገው ውይይት በእስር ወቅት ተፈጽመዋል ስለተባሉ የሥነ ምግባር ጥሰቶች ተገቢው ማጣራት እንዲደረግ፣ ታሳሪዎቹ ከቤተሰብ ለሚፈልጉት አቅርቦት አዲስ አበባ በሚገኘው የፖሊስ ቢሮ አማካኝነት እንዲመቻች፣ ከቤተሰብ መገናኛ ስልክና ጉብኝት ለሚፈልጉም በአፋጣኝ እንደሚመቻች መግባባት ላይ መደረሱም ተገልጿል። በኮሚሽኑ የሰብዓዊ መብቶች ክትትልና ምርመራ ሥራ ክፍል ከፍተኛ ዳይሬክተር ዶ/ር ሚዛኔ አባተ ለዶቼ ቬለ በሰጡት ተጨማሪ ማብራሪያ፤ «የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተደንግጎ በሚቆይበት ጊዜ ሰዎችን ከማሰቃየት ተግባር የመቆጠብ፣ በሕይወት የመኖር መብትን ማስከበርን እና በገለልተኛ አካል የመዳኘት መብት የመሳሰሉት መከበር አለባቸው። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚፈቀዱ እርምጃዎች ቢኖሩ እንኳን የሕጋዊነትን፣ አስፈላጊነትን እና የተመጣጣኝነትን መርህ መከበር አለባቸው።» ብለዋል።

ቤተሰብ የታሰረባቸው አስተያየት

ባለቤታቸው ነሐሴ 16 ቀን 2015 ዓ. ም መያዙን ያስታወቁት ፖለቲከኛ ቀለብ ስዩም «በወቅቱ ለምን እንደተያዘ እና በምን ምክንያት ለዚህ እንደተዳረገ ጠይቀን ምንም ማብራሪያ አላገኘንም» በማለት ገልፀዋል። ባለቤታቸው ከፌዴራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ መወሰዳቸውን በማመልከትም፤ «ነሐሴ 20 ጀምሮ ግን የት እንደተወሰደ ከመናገር ውጪ እርግጠኛ ሆነው የት እንደሚገኝ ሳያውቁ መቆየታቸውን፣ ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና ለሌሎች አካላት በተደጋጋሚ መጠየቃቸውን የተናገሩት ወይዘሮ ቀለብ ስዩም አሁን ግን አዋሽ አርባ እንደሚገኙ ከኮሚሽኑ እንደተገለፀላቸው ተናግረዋል።«የታራሚዎች በተጨናነቀ ሁኔታ መያዝ አሳሳቢ ነው»ኢሰመኮ
ባለቤታቸው ምንም የፖለቲካ ተሳትፎ እንደሌላቸው እና የእሥሩ ምክንያት በፖለቲካ ውስጥ የማደርጉትን ተሳትፎ ለማደናቀፍ ጭምር ታስቦ የተደረገ ስለመሆኑ፣ ሌሎችም የሚሳተፉበት የፖለቲካ ድርጅት የባልደራስ አመራሮች እና አባላትም ወደዚሁ ስፍራ ተወስደው መታሰራቸውንም ተናግረዋል።

የምክር ቤት አባላቱ አካልን ነፃ የማውጣት ክስ መቋረጥ

ከአቶ ክርስትያን ታደለ እና ከዶክተር ካሣ ተሻገር ጠበቆች አንዱ የሆኑት ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ለዶቼ ቬለ «እሥሩ ሕገ ወጥ ነው በሚል በፍርድ ቤት ጀምረውት የነበረው አካልን ነፃ የማውጣት ክስ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ድንጋጌ የሚሻር በመሆኑ» ክሱን ለማቋረጥ መገደዳቸውን ገልፀዋል።የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የዘጠኝ ወራት ዘገባ
በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከመደንገጉ በፊትም ሆና በኋላ በሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች፤ በጋዜጠኞች እና በማኅበረሰብ አንቂዎች ላይ ያነጣጠሩት የእስር እና አፍኖ የመሰወር ጥቃቶች ሊቆም ይገባል የሚሉ ጥያቄዎች በስፋት ይስተዋላሉ።

ፎቶ ከማኅደር፤ የኢሰመኮ  ዋና ጽሕፈት ቤት ሕንጻ አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በአማራ ክልል የተደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ እስካሁን አደረግሁት ባለው ክትትል፣ ግኝቶች፣ እና ተያያዥ ጉዳዮች ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ጋር መወያየቱን አስታውቋል። ፎቶ ከማኅደር፤ የኢሰመኮ ዋና ጽሕፈት ቤት ሕንጻ አዲስ አበባምስል Solomon Muchie/DW

ሰሎሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ