1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጥር 6 ቀን 2016 የዓለም ዜና

Eshete Bekeleሰኞ፣ ጥር 6 2016

በአዲስ አበባ የሚገኘው የንፋስ ስልክ ቀለም ፋብሪካ ብርቱ የእሳት አደጋ ደረሰበት። የሱዳን ጦር በዋይት ናይል ግዛት በፈጸመው ድብደባ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን ተገደሉ። በሺሕዎች የሚቆጠሩ ትራክተሮች እና አስር ሺሕ ገደማ የጀርመን ገበሬዎች በበርሊን ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ። ከቀዝቃዛው ጦርነት ወዲህ ትልቁ በተባለ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO) ወታደራዊ ልምምድ የብሪታኒያ 20 ሺሕ ወታደሮች እንደሚሳተፉ የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ግራንት ሻፕስ ገለጹ። የጋዛ የጤና ሚኒስቴር በእስራኤል እና በሐማስ መካከል ውጊያ ከተቀሰቀሰ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ24 ሺሕ በላይ መድረሱን አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/4bGVl
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ስለዚሕ ዝግጅት

ስለዚሕ ዝግጅት

PODC-DW-Amharisch-News-DWcom

የዓለም ዜና

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና የዜና ትንታኔዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ።