1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ገበሬዎች እና የጣምራዉ መንግሥት ዉዝግብ

ሰኞ፣ ጥር 6 2016

የጀርመን ገበሪዎች ተቃዉሞ እንደቀጠለ ነዉ። ባለፈዉ ሳምንት መጀመርያ በጀርመን በተለያዩ ከተሞች መንግሥት የሚሰጠን ድጎማ ቀንሶብናል ሲሉ ገበሪዎች የአደባባይ ተቃዉሞ አድርገዋል። ጀርመን ከባቡር አሽከርካሪ እስከ አራሽ ገበሪ ለተቃዉሞ አደባባይ በመዉጣታቸዉ፤ ጀርመን በተቃዉሞ ሙድ ዉስጥ ገብታለች ሲሉ የተለያዩ ጋዜጦች በርዕስነት ይዘዉ ዘግበዋል።

https://p.dw.com/p/4bG6L
የጀርመን ገበሪዎች አድማ እና ጥምሩ መንግሥት
የጀርመን ገበሪዎች አድማ እና ጥምሩ መንግሥት ምስል Florian Gaertner/photothek/IMAGO

ከገበሪዎች በተጨማሪ ዳቦ ጋጋሪዎች የወተት ተዋጽኦ አምራቾች በአድማዉ ላይ ተገኝተዋል። የባቡር ሹፌሮችም አድማ መተዉ ነበር።

የጀርመን ገበሬዎች ተቃዉሞ እንደቀጠለ ነዉ። ባለፈዉ ሳምንት መጀመርያ በጀርመን በተለያዩ ከተሞች መንግሥት የሚሰጠን ድጎማ ቀንሶብናል ሲሉ ገበሪዎች የአደባባይ ተቃዉሞ አድርገዋል። ገበሪዎች ለተቃዉሞ ይዘዉት በወጡት የማረሻ ትራክተር ሰፋፊ ጎዳናዎች በመዘጋታቸዉ፤ በተለያዩ ቦታዎች የትራፊክ መጨናነቅ ተከስቶ ነበር። የገበሪዎች ተቃዉሞን ተከትሎ የጀርመን ጣምራዉ መንግሥት የናፍጣ ድጎማ እንዲሁም ገበሪዎች ትራክተር ሲገዙ ቀረጥ ለመቀነስ ሃሳብ ቢያቀርብም ገበሪዎች እንደማይቀበሉ ተናግረዋል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የእርሻ መሣርያ ተሽከርካሪዎቹን ከሚነዱት በተጨማሪ የተቃዉሞ ሰልፉን በግብርና ምርት ስር የተሰማሩ ፤ ዳቦ ጋጋሪዎች፤ የምግብ አቅራቢዎች ፤ የወተት ተዋጽኦ አምራቾች የመሳሰሉ ባለሞያዎች እና የኩባንያ ሰራተኞች ተቀላቅለዉታል። መዲና በርሊን ላይ ብቻ ወደ 10, 000 የሚጠጉ ሰዎች በተቃዉሞ ላይ ተሳትፈዋል። ገበሪዎች የእርሻ ትራክተሮቻቸዉን ይዘዉ በርሊኑ ብራንድቡርግ በር ተብሎ በሚታወቀዉ የበርሊን ምልክት አካባቢ ተቃዉሞዋቸዉን አሳይተዋል። የተቃውሞ ሰልፉ የበርሊን ዋና ዋና አውራ ጎዳናዎችን፣ የተለያዩ የባቡር እና የአውቶቡስ ጣቢያዎችን እንዲዘጉ አስገድዷል። ፖሊስ 1,300 ገደማ መኮንኖች ለጥበቃ እንደተሰማሩ አስታውቋል። 

ከዚህ ሌላ የባቡር አሽከርካሪዎች የደሞዝ ጭማሪ እና የሥራ ሰዓት ይቀነስ ጥያቅያቸዉን በማስመልከት ተቃዉሟቸዉን ቀጥለዉ ነበር። በጀርመን ከባቡር አሽከርካሪ እስከ አራሽ ገበሪ መንግሥትን በመቃወም አደባባይ መዉጣታቸዉ ጀርመን በተቃዉሞ ሙድ ዉስጥ ገብታለች ሲሉ የተለያዩ ጋዜጦች በርዕስነት ይዘዉ ዘግበዋል። በጀርመን በተለያዩ ከተሞች ስለታየዉ ተቃዉሞ  የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤልን ስለጉዳዩ አነጋግረነዋል።

 

አዜብ ታደሰ

ታምራት ዲንሳ