1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመኑ «ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ» ጉባኤ እና ኢትዮጵያ

ሰኞ፣ ኅዳር 10 2016

የቡድን 20 “ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ” በጎርጎሮሳዊው 2017 ጀርመን የቡድን 20 ፕሬዝደንት ሳለች የተጀመረ ነው። ጉባኤው ለውጥ ፈላጊ የአፍሪካ ሀገራትን፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን እና አጋሮችን በማሰባሰብ የልማት ጉዳዮችን የማስተባበር እና በኢንቨስትመንት ላይ ለመወያየት የተወጠነ ነው።

https://p.dw.com/p/4ZEBy
ቡድን 20 “ኮምፓክት ዊዝ አፍሪቃ” ጉባኤ በርሊን
ቡድን 20 “ኮምፓክት ዊዝ አፍሪቃ” ጉባኤ በርሊን ምስል Markus Schreiber/Pool AP/dpa/picture alliance

በጀርመን የኮምፓክት ፎር አፍሪቃ ጉባኤ እና ኢትዮጵያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ መሪዎች የሚሳተፉበት የቡድን 20 “ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ” ጉባኤ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል። በጀርመን አዘጋጅነት በሚካሔደው ጉባኤ ከአፍሪካውያን መሪዎች በተጨማሪ የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኡርሱላ ፎን ደርላየን፣ የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኤማኑዌል ማክሮ የኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩተ እየተሳተፉ ነው።ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በበርሊን ተቃዉሞ ገጠማቸው
የቡድን 20 “ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ” በጎርጎሮሳዊው 2017 ጀርመን የቡድን 20 ፕሬዝደንት ሳለች የተጀመረ ነው። ጉባኤው ለውጥ ፈላጊ የአፍሪካ ሀገራትን፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን እና አጋሮችን በማሰባሰብ የልማት ጉዳዮችን የማስተባበር እና በኢንቨስትመንት ላይ ለመወያየት የተወጠነ ነው።
በኮምፓክት ዊዝ አፍሪቃ የኢንቨስትመንት አማራጭ ለአፍሪቃ  ብሎም ለኢትዮጵያ የሚኖረውን አንድምታ በተመለከተ የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል በርሊን ውስጥ ያገኛቸውን ኢትዮጵያውያን አነጋግሯል። 

ይልማ ኃይለሚካኤል 

ታምራት ዲንሳ 

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር