የዶናልድ ትራምፕ 4ኛ ክስ ምን ለየት ያደርገዋል?
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 9 2015ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞው ፕሬዚፈንት ዶናልድ ትራም ላይ በዚህ ዓመት አራተኛው ክስ ዛሬ ማለዳ ቀርቦባቸዋል ። ክሱም በጆርጂያ የምርጫ ውጤትን ለማስቀየር በመሞከር በሚል ነው ክሱ የቀረበባቸው ። ፕሬዚዳንቱ እና ደጋፊዎቻቸው ክሱን በማጣጣል ለቀጣዩ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የገንዘብ እና ድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻቸውን ቀጥለዋል ።
አስተያየት ሰጪዎች እንደሚናገሩት ዶናልድ ትራምፕ ከዚህ ቀደም የቀረቡባቸው ሦስት ክሶችየተመሰረቱት በዩናይትድ ስቴትስ የፌዴራል መንግሥቱ ነበሩ ። የጆርጂያው ግን በፌዴራል ሳይሆን በዩናይትድ ስቴትስ አንድ ግዛት የቀረበ ነው ። ምናልባት ዶናልድ ትራምፕ ወደፊት ቢመረጡ ቀደም ብለው የቀረቡባቸውን ሦስት ክሶች ውድቅ የማድረግ ሥልጣን ይኖራቸዋል ። የጆርጂያው ግን ከፌዴራሉ ሥልጣን ውጪ ስለሆነ ሌላ አጣብቂን ውስጥ ሊከታቸውም ይችላል ።
ለመሆኑ የጆርጂያው ክስ ለምን አሁን ተጀመረ? ከሌሎቹ ክሶችስ ምን ለየት ያደርገዋል?የጆርጂያ ግዛት ላይ ባለፈው ምርጫ ምን ተከስቶ ነበር፤ ዶናልድ ትራምፕስ በስልክ የንግግር ቅጂ ላይ ይፋ እንደሆነው ምን የሚያስከስሳቸው ነገር ተገኘ? የዋሽንግተን ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግረነዋል ።
አበበ ፈለቀ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ