Eshete Bekeleቅዳሜ፣ የካቲት 23 2016ኢትዮጵያውያን ቅኝ ሊገዛቸው የሞከረውን የጣሊያን ጦር ተባበረው ቢያሸንፉም እርስ በርስ ባደረጉት ጦርነት ብርቱ ሰብአዊ ቀውስ መድረሱን ርዕሰ-ብሔር ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የዓድዋ ድል 128ኛ ዓመት ሲከበር ተናገሩ። በሱዳን የግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ለተቸገሩ ርዳታ እንዳያቀርቡ መተላለፊያ መከልከል በጦር ወንጀል ሊያስጠይቅ እንደሚችል ፎልከር ቱርክ አስጠነቀቁ። የቻድ ወታደራዊ መሪ ማሐማት ኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ በሀገራቸው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ እንደሚወዳደሩ አስታወቁ። በጋዛ ርዳታ ከጫነ የከባድ ተሽከርካሪዎች ቅፍለት አቅራቢያ በተከፈተው ተኩስ በርካታ ሰዎች በጥይት ተመትተው መቁሰላቸውን የተመ ታዛቢዎች ቡድን አስታወቀ