ትምህርትአፍሪቃ
ጫማ ጠራጊ የኮሌጅ ተማሪዎች
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 16 2013ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ከተማ ጎዳናዎች ላይ በርካታ በሱሶች የተጠመዱ ታዳጊዎችን ማየት የተለመደ ነው። በአንጻሩ ደግሞ ከገጠር ወደ ከተማ መጥተው ባገኙት አነስተኛ ስራ ተሰማርተው፣ ራሳቸውን ሲረዱ የሚስተዋሉ ታዳጊዎች ቁጥርም የዛኑ ያህል ቀላል የሚባል አይደለም ። ለዚህም የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዶቻችን ጥበቢቱ ጥላሁን፣ ሰንበቶ በኔ እና ደሞዜ ዳንጊሶ ጥሩ ምሳሌ ሊሆኑ ይችላሉ። በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ የሚገኙት እነዚህ ወጣቶች ጎዳናዎች ላይ ጫማ በማጽዳት ወይም በሊስትሮ ስራ ተሰማርተው ለእለት ኑሮና ለትምህርት ቤት ክፍያ የሚያሰፈልጋቸውን ወጪ በራሳቸው ይሸፍናሉ። « የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች» #GirlZOffMute ዘጋቢ ወጣት ሊሻን ዳኜ ወደ ስራ ቦታቸው ሄዳ አወያይታቸዋለች።
ሊሻን ዳኜ
ሸዋንግዛው ወጋየሁ / ልደት አበበ