በዛሬዉ አንድ ለአንድ ዝግጅታችን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር የዉጪ ግንኙነት አማካሪ ዶክተር ሽጉጥ ገለታን አነጋግረናል።ዶክተር ሽጉጥ እንደሚሉት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (ኦነሠ) ጋር ግንኙነት የለዉም።የኦነሠ ታጣቂዎችም ሰላማዊ ሰዎችን ማገት፣ማፈናቃል ሲበዛም መግደላቸዉን የሚያረጋግጥ በጥናት የተደገፈ መረጃ የለዉም።
ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን የግጭት፣የፖለቲካ ዉዝግብና የምጣኔ ሐብት ቀዉስ ለማቃለልም መንግሥት ከታጣቂዎች ጋር መደራደር፣ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመንቀሳቀስ መብት ማክበር፣ አባላትና ደጋፊዎቻቸዉን ማንገላታቱን ማቆም፣ የዘጋቸዉን ፅሕፈት ቤቶቻቸዉን መክፈት ይገባዋል-እንደ ዶክተር ሽጉጥ እምነት።
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ከተመሠረተ 50 ዓመት በልጦታል በዚሕ ረጅም የትግል ዘመን አንድም ጊዜ ለስልጣን አልበቃም።ብዙዎች እንደሚገምቱት የ50 ዘመን አጠቃላይ ትግሉም ከግብ አልደረሰም,።ዶክተር ሽጉጥ ግን የኦሮሞ ሕዝብ ዛሬ ለደረሰበት ደረጃ ያደረሰዉ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ባይ ናቸዉ።
«የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተባብሮ ይሠራል።አሁንም እየሠራ ነዉ።----በሚቀጥለዉ ምርጫ ይወዳደራል--------የአማራ ሕዝብን አይጠላም-----የመገንጠል ዓላማ የለዉም---» ያላሉ ዶክተር ሽጉጥ ገለታ።
ነጋሽ መሐመድ
ሙሉዉን ቃለ መጠይቅ ያድምጡ