የኤሊዜ ውል 50 ኛ ዓመት
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 3 2004በዚሁ ስነ ስርዓት ላይ ለፈረንሳይ ጀርመን የጠበቀ ግንኙነት መሰረት የጣለው የእርቅ ውል 50ኛ ዓመት ባለፈው እሁድ ፈረንሳይ ውስጥ በተካሄደ ስነስርዓት ታስቧል ። የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክልና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ፍራንሷ ኦሎንድ በተገኙበት በዚሁ ስነ ስርዓት ላይ ውሉን የፈረሙት የዚያን ጊዜዎቹ የሁለቱ አገራት መሪዎች ተወድሰዋል ። የአውሮፓ ህብረት መሰረት የሆኑት ሁለቱ አገሮች ህብረቱ ያጋጠመውን የገንዘብ ቀውስ ለመፍታት በየጊዜው የሚያጋጥሙ ልዩነቶቻቸውን እያጠበቡ በጋራ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው ። የጀርመንና የፈረንሳይ ግንኙነት የእርቅ ውልና አስተምህሮቱ የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ።
ኃያላኑ የአውሮፓ ሃገራት ጀርመን ና ፈረንሳይ እንዲህ እንደ አሁኑ ጥብቅ ወዳጅ ሳይሆኑ ወደ 100 ዓመት ለሚጠጋ ዘመን በጠላትነት የሚተያዩ ባላጋራዎች ነበሩ ። ሁለቱ ሃገራት ለዘመናት ሆድና ጀርባ ሆነው የቆዩትም በተለያዩ ጊዜያት ባካሄዷቸው ጦርነቶች ምክንያት ነው ። ለበርካታ ዓመታት ጀርመን የኖሩትና የተማሩት የታሪክ ምሁር ዶክተር ልጅ አስፋወሰን አሥራተ ካሳ የሁለቱን አገሮች ጥላቻ ከመነሻው ይዘረዝራሉሁለተኛው የዓለም ጦርነት በናዚ ጀርመን ሽንፈት ከተደመደመ ከ 18 ዓመታት በኋላ ነበር የጀርመንና የፈረንሳይን ግንኙነት ታሪክ ለመቀየር የበቃው ስምምነት ላይ የተደረሰው ። እጎአ ሐምሌ 8 1962 ዓም ፓሬስ ፈረንሳይ ውስጥ የዚያን ጊዜው የጀርመን መራሄ መንግሥት ኮናርድ አደናወርና የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ሻርል ደጎል የኤሊዜ ውል የሚል ስያሜ የተሰጠውን ስምምነት ፈረሙ ። ለሁለቱ አገራት ግንኙነት ስምረት መሰረት የጣለው ይኽው ውል ሊፈረም የቻለው በመሪዎቹ ጥንካሬና እምነት መሆኑን ዶክተር ልጅ አስፋወሰን ያስረዳሉ ።
። ሁለቱ ባለራዕይ መሪዎች በፈረሙት ውል መሰረት የመንግሥታቱ ተወካዮች የውጭ ደህንነትን የወጣቶችንና የባህል ግንኙነቶችን በመሳሰሉ ጠቃሚ ጉዳዮች ላይ በየጊዜው ምክክሮች ማካሄድ ጀመሩ ። ኮናርድ አደናውርና ሻርል ደጎል በሁለቱ አገራት ወጣቶች መካከል መተማመን እንዲሰፍን የሰጡት ትኩረት ሁለቱ የቀደሞ ባጋራዎች በአውሮፓ ወሳኝ ሚና ያላቸው ወዳጆች የሆኑበትን መንገድ ጠረገ በሂደትም ታሬካዊው የኤሊዜ ውል የመንግሥታቱንና ህዝቦችን ግንኙነት በእጅጉ ቀየረ ። ከ40 ዓመታት በላይ ጀርመን የኖሩት ዶክተር ልጅ አስፋወሰን ወሉ ያስከተለውን ለውጥ የታዘቡ የዓይን ምስክር ናቸው ። ከትናንት በሰተያ እሁድ 50 ዓመት የደፈነው የኤሊዜ ውል ከምንም በላይ ለአውሮፓ አንድንት መጠናከር ያደረገው አስተዋፅኦ የጎላ መሆኑ ይወሳል ። የ2ቱ አገሮች ወዳጅነት የህብረቱ መሰረት ሲሆን በዚህ ሂደትም የአሁኖቹም ሆኑ የቀደሙት መሪዎች ሚና ትልቅ ድርሻ አለው እንደ ዶክተር ልጅ አስፋወሰን
የጠላትነትን ጠባሳ ሽሮ ጥብቅ ወዳጅነትን ያሰፈነው የጀርመንና የፈረንሳይ የእርቅ ውል ለ ሌሎች የአውሮፓ ሃገራት በአርያነት ሊወሰድ የሚችል እንደሆነ ይታመናል ።
የጀርመንና የፈረንሳይ የእርቅ ውል 50 ኛ ዓመት ሲታሰብ ከዚያ አስቀድሞ ኢትዮጵያ ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ በታሪክ ቀዳሚዋ ሃገር መሆኗ ሊዘነጋ አይገባም ይላሉ ዶክተር አስፋወሰን አሥራተ ካሳ ።
የጦርነት ጠባሳ ሽሮ ወዳጅነት እንዲሰፍን መሰረት የጣለው የጀርመንና የፈረንሳይ ውል 50ኛ ዓመት በአንደኛው የዓለም ጦርነት በጀርመን የቦምብ ድብደባ ከባድ ጉዳት በደረሰበት ራይም በተባለው የፈረንሳይ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ካቴድራል ባለፈው እሁድ በደመቀ ስነ ስርዓት ታስቧል ። በዋዜማው ደግሞ እዚያው ከተማ ውስጥ በ1ኛው የዓለም ጦርነት የተገደሉ የጀርመን ወታደሮች መካነ መቃብር መደፈሩ ጥላቻው እስካሁን ሙሉ በሙሉ መሻሩን አጠያያቂ ሊደርገው ይችላል ። እንደ ዶክተር አስፋ ወሰን ግን በአሁኑ ሰዓት ይህን መሰሉ አስተሳሰብ ያላቸው ዜጎች ጥቂት ናቸው ።
የጀርመንና የፈረንሳይና ግንኙነት የለወጠው የኤሊዜ ውል ላይ ያተኮረው የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን በዚሁ አበቅቷል ። በዝግጅቱ ማብራሪያ በመስጠት የተባበሩኝን ዶክተር ልጅ አስፋወስን አሥራተ ካሳን እያመሰገንኩ በዚሁ የምለያችሁ ሂሩት መለሰ ነኝ ።
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ