1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ አካሄድ

ረቡዕ፣ መስከረም 21 2012

መንግሥት በሚከተለው የልማታዊ  መንግሥት መርህ የሃገሪቱ ኢኮኖሚ ሁለት መልክ ያለው እንደነበር ይናገራል። አንዱ ተከታታይ እድገት የተመዘገበበት ተብሎ ሲጠራ በሌላ በኩል ደግሞ የፍትሃዊ ተጠቃሚነት እጦት ተንሰራፍቶ ሀገሪቱን ለማክሮ ኢኮኖሚ መዛባትና ዘርፉን ከባድ ቅርቃር ውስጥ ማስገባቱን ራሱ መንግሥት አምኖ መፍትሄዎችንም እያፈላለገ ይገኛል።

https://p.dw.com/p/3Qex8
Äthiopien Addis Ababa | Getachew Assefa - Äthiopischer Wirtschaftswissenschaftler
ምስል DW/S. Mushie

የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ አካሄድ

የማክሮ ኢኮኖሚው ሚዛን መዛባት መገለጫዎችም ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ እጥረት ፣ እያሻቀበ ያለው አገራዊ የእዳ ክምችት ፣ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትና መንግስት ለግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ በቂ የመንቀሳቀሻ ገንዘብ ማቅረብ አለመቻል ሆነው ተቀምጠዋል። ሀገሪቱ በመጀመርያው የእድገትና የመለወጥ የ አምስት አመት እቅድ እንዲህ ያለው የኢኮኖሚ መዛባት ችግር ይገጥመኛል የሚል ትንተናና ትንበያ አልነበራትም።
ይልቁንም በ 2020  ዝቅተኛ መካከለኛ ገቢ ገቢ ያላቸው ሃገራት ተርታ እንሰለፋለን ነበግ ውጥኗ። ይህ እልሆን ብሎ ጊዜው በአምስት አመት ተገፋ ። ያም የማያዋጣ ሲሆን የውጥኑ የስኬት ጊዜ 2030 ነው ተብሏል። ከዚህ ባለፈ ደረጃም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያን በሚቀጥሉት ከ አምስት እስከ 10 አመታት ውስጥ ከ አምስቱ የአፍሪካ የዳበረ የኢኮኖሚ አቅም የገነቡ ሃገራት ውስጥ እናሰልፋለን ማለታቸውንና አሁን ይተገበራል እየተባለ ያለው የአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እቅድ ያልበሰለና በትክክለኛ ባለሚያዎች ተተንትኖ ያለመቅረቡ አመላካች ንግግር ነው በማለት ብሄራዊ ኢኮኖሚስቱ አቶ ጌታቸው አሰፋ ይሞግታሉ። ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ
ሰለሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ