1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮ-ኤርትራ ግንኙነት እና ተግዳሮቶቹ

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 7 2010

ኢትዮጵያ ሲገቡ ዛሬ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ «የኤርትራና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ከእንግዲህ ሁለት ሕዝቦች ናቸው ብለው የሚገልፁ ካሉ ሀቁን የማያውቁ ናቸው” ብለዋል።

https://p.dw.com/p/31Si6
Äthiopien - Ankunft des Präsidenten Isayas Afewerki aus Eritrea
ምስል Y. G. Egziabher

የኢትዮ ኤርትራ ግንኙነት ተግዳሮቶች

ኢትዮጵያ ሲገቡ ዛሬ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ «የኤርትራና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ከእንግዲህ ሁለት ሕዝቦች ናቸው ብለው የሚገልፁ ካሉ ሀቁን የማያውቁ ናቸው” ብለዋል። ይኽ ንግግራቸው ምናልባትም ሁለቱን ሀገራት ይበልጥ አቀራርቦ ወደ አንድ የሚያመጣ ሊኾን እንደሚችል ተንታኞች ተናግረዋል። የአፍሪቃ ቀንድ የፖለቲካ ተንታን እና ደራሲ አቶ ዩሱፍ ያሲን «ንግግሩ ቆም ተብሎ ታስቦበት ከኾነ በጣም ደስ ይላል» ብለዋል።

ሙሉ ቃለ መጠይቁ ከድምጽ ማጫወቻው ይገኛል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሰ