የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ጋዜጣዊ መግለጫ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 11 2015ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት አመቱ 75 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ገቢ ያገኘበትን እና 101 ከመቶ የገቢ እቅዱን አሳክቼበታለሁ ሲል ያስታውቀበትን አመት ያሸበረቀ ውጤት የተመዘገበበት የበጀት አመት አፈፃፀም ሲሉ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገልፅዋል ። ኢትዮ ቲሌኮም በያዝነው አመት ያስመዘገበው ውጤት ፤ ከባለፈው የበጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ23.5 በመቶ ብልጫ እንዳለው አስረድተዋል።እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ ከሚያስገኙ ገቢዎች 164 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ጨምረው ገልጸዋል። በበጀት ዓመቱ የኢትዮ ቴሌኮም ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር 72 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፤ ይህ የተያዘው ዕቅድ አንፃርም ሲትይ 98 በመቶ ውጢት መመዝገቡን ተነግሯል። ከመደበኛ አገልግሎት በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ 203 ምርትና አገልግሎት ለደንበኞች የቀረበ ሲሆን ከዚህም መካከል 116ቱ አዲስ ምርትና አገልግሎቶች መሆናቸውም ተነግርዋል ።የተቀሩት ማሻሻያ ተደረገባቸው ለደንበኞቹ ቀርቧል ተብሏል ። ምንም እንኳን አመቱ የተሳካ ቢሆንም የተለያዪ ተግዳሮቶች እንደነበሩበት እና ይህንንም በተገቢው ሁኔታ እንደተወጣው አስታውቀዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በተለያዪ የሀገራችን ከፍሎች ከሚከሰተው ግጭት ጋር በተይያዘ በተቋሙላይ የደረሰውን ጉዳት የዋጋ ተመን እንዲያሳውቁ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቂ ሲመልሱ በጉዳዪላይ በርካታ ባለድርሻ አካላት ስላሉበት አሁን መረጃውን መስጠት አሳሳች ይሆናል ሲሉ ገልፅዋል።ከተገኘው ገቢ መካከል 43.7 በመቶ የሚሆነው የሚሸፍነው የድምጽ አገልግሎት ሲሆን 26.6 በመቶ የሚሆነውን ደግሞ የኢንተርኔት ጥቅል ነውም ተብሏል ። ኢትዮ ቴሌኮም 20 በመቶ የነበረውን የተጠቃሚዎች ቁጥርም ወደ 33 በመቶ ማድረስ መቻሉ ሲገለጽ 164 ከተሞች 4ጂ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋልተብሏል ።በ300 ከተሞች 4ጂ እና አድቫንስድ 4ጂ አገልግሎቶች መስጠት መጀመሩንም አስታውቋል ። በበጀት ዓመቱ ገቢን ለማሳደግ ትርፋማነቱን ለማጠናከር ባቀደው መሰረት ያልተጣራ ትርፍ 51.2 በመቶ ማስመዝገቡ ይህም ከዓምናው ጋር ሲነጻጸር 24 በመቶ እድገት ማሳየቱም ሰምቷል። ዋና ስራስፈፃሚዋ ከተለያዪ የቲክኖሎጂ ተቋማት ጋር እየሰሩ እንደሆነም ተናግረዋል
ሀና ደምሴ
ኂሩት መለሰ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር