የአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝደንት ቃል ኪዳኖች እና ተግዳሮቶች
ቅዳሜ፣ ግንቦት 13 2014ማስታወቂያ
ሐሳን ሼይክ ሞሐሙድ ለሁለተኛ ጊዜ የተመረጡ የመጀመሪያው የሶማሊያ ፕሬዝደንት ናቸው። ከዚህ ቀደም ከጎርጎሮሳዊው 2012 እስከ 2017 አገሪቱን በፕሬዝደንትነት መርተዋል።
በሶማሊያ ፖለቲካ ኃይለኛ የሚባለው የሐውያ ጎሳ አባል የሆኑት ሐሳን ሼይክ ሞሐሙድ እግራቸው ወደ ፖለቲካ ያመራው በጎርጎሮሳዊው 2011 አንድነት ለሰላም እና ልማት የተባለውን ፓርቲ አቋቁመው ነው። ፓርቲው በተመሠረተ በአመቱ ፕሬዝደንት ሆነው ሲመረጡ በአክራሪዎች ጥቃት የተተራመሰችውን አገር ወደ መረጋጋት ይመራሉ ተብሎ ተስፋ ተጥሎባቸው ነበር።
ከዚህ ቀደም በምርጫ ያነሸነፏቸውን ፕሬዝደንት መሐመድ አብዱላሒ ሞሐመድን ተክተው ወደ ሥልጣን ሲመለሱ "ከራሷ እና ከዓለም የተስማማች ሶማሊያ ለመገንባት" ቃል ገብተዋል። ይሁንና
በርካታ ፈተናዎች ይጠብቋቸዋል። አል-ሸባብ አሁንም በርካታ የሶማሊያ አካባቢዎችን ተቆጣጥሮ ደም አፋሳሽ ጥቃቶች ከመፈጸም አልተገታም። በአፍሪካ ቀንድ በበረታው ድርቅ ሳቢያ 40 በመቶ የሚሆነው የሶማሊያ ሕዝብ ተርቧል። በሶማሊያ ፌድራል መንግሥት እና በግዛቶቿ መካከል ያለው የፖለቲካ ሽኩቻም ኹነኛ መፍትሔ ይፈልጋል።
ገበያው ንጉሴ
እሸቴ በቀለ