የአውሮፓ የስደተኞች ቀውስ
ረቡዕ፣ የካቲት 25 2012ማስታወቂያ
ቱርክ የአውሮፓ ድንበሯን ከከፈተች በኋላ ሶማሊያውያንን ጨምሮ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ወደ ግሪክ ለማቆረጥ መንገድ በማፈላለግ ላይ ናቸው። ስደተኞቹ በቱርክ ድንበር የሚፈሰውን የኢቭሮስ ወንዝ በእግር ለማቋረጥ ሙከራ እያደረጉ መሆኑን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።
የኢቭሮስ ረግረጋማ ሥፍራን ለማቋረጥ የሞከሩ 1,000 ገደማ ስደተኞች ማገዳቸውን የግሪክ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ወደ አውሮፓ ለመሻገር ከሚሞክሩት መካከል የአፍጋኒስታን፣ ፓኪስታን፣ ሞሮኮ፣ ባንግላዴሽ፣ ሶማሊያ እና ማሊ ዜጎች ይገኙበታል።
በኢድሊብ ከሶርያ ኃይሎች ግብግብ የገጠመችው ቱርክ በአውሮፓ ላይ ጫና ለማሳደር ድንበሯን በግዛቷ ላስጠለለቻቸው ስደተኞች እንደምትከፍት አስታውቃለች። ከ3.5 ሚሊዮን በላይ የሶርያ ስደተኞች ያስጠለለችው የቱርክ ፕሬዝዳንት ረቺብ ጣይብ ኤርዶኻን ከአውሮፓ ከፍ ያለ ድጋፍ ጠይቀዋል።
ገበያው ንጉሴ
ሸዋዬ ለገሠ