1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ ህብረት በመራዊ ከተማ የተፈጸመው ግድያ እንዲጣራ ጠየቀ

ረቡዕ፣ የካቲት 6 2016

የአውሮፓ ህብረት በቅርቡ በኢትዮጵያ በአማራ ክልል በመራዊ ከተማ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ አውግዞ መግለጫ አውቷል። ህብረቱ በቃል አቀባዩ በኩል ትናንት ባወጣው መግለጫ፤ ግድያው በነጻና ገለልተኛ ቡድን ተጣርቶ የወንጀሉ ፈጻሚዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቋል።

https://p.dw.com/p/4cOY2
Symbolbild: EU Kommission | Brüssel, Belgien
ምስል Cornelius Poppe/NTB/picture alliance

የአውሮፓ ህብረት በመራዊ ከተማ የተፈጸመው ግድያ እንዲጣራ ጠየቀ

የአውሮፓ ህብረት በቅርቡ በኢትዮጵያ በአማራ ክልል በመራዊ ከተማ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ አውግዞ መግለጫ አውቷል። ህብረቱ በቃል አቀባዩ በኩል ትናንት ባወጣው መግለጫ፤ ግድያው በነጻና ገለልተኛ ቡድን ተጣርቶ የወንጀሉ ፈጻሚዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቋል። ዲደብሊው የህብረቱን ቃል አቀባይ ወይዘሪት ናቢላ ማስራሊንን ስለዚህ፤ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ህብረቱ ለመጀመሪያ ግዜ በኢትዮጵያ ላይ ስላወጣው መግለጫ ማብራሪያ ጠይቆ ነበር፤ “ የአውሮፓ ህብረት በመራዊ ከተማ  የተገደሉት ሰላማዊ ሰዎች ጉዳይ በጣም አሳስቦታል” በማለት  ወንጀሉ በገለልተኛ አጣሪ  ቡድን እንዲጣራ የጠየቀ መሆኑን አስታውቀዋል።በክልሉ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ እዲራዘም መደረጉም የህዝቡን የሰብዊ መብቶች እንደሚገድብና ይህም ህብረቱን እንደሚያሳስበውም ቃል ዓቀባዩዋ አክለው ገልጸዋል።

የአውሮጳ ሕብረት ዋና መስሪያ ቤት
የአውሮፓ ህብረት በመራዊ ከተማ  የተገደሉት ሰላማዊ ሰዎች ጉዳይ በጣም አሳስቦታል” በማለት  ወንጀሉ በገለልተኛ አጣሪ  ቡድን እንዲጣራ የጠየቀ መሆኑን አስታውቀዋል።ምስል Monasse T/Andia/IMAGO

የፖለቲካ ልዩነቶች በውይይት እንዲፈቱ የቀረበ ጥሪ

 የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ልይነቶችና አለመግባባቶች በውይይትና ድርድር መፈታት እንዳለባቸው እንደሚያምንና ለዚህም ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግም ቃል አቀባዩዋ መግለጫውን ዋቢ አድረገው አስረድተዋል ።በመራዊው ግጭት ከ80 በላይ ሰዎች ተገድለዋል ፤ ኢሰመጉ “ የአውሮፓ ህብረት አሁንም የፖለቲካ ልዩነትን በውይይትና እርቅ ለመፍታት የሚደረግ ሂደትን ይደግፋል፤ ያግዛልም”፤ በማለት  ሁሉም ኢትዮጳያውያን ይህንን መንገድ እንዲከተሉ ህብረቱ ጥሪ ያቀረበ መሆኑን አስታውቀዋል። 

ኢትዮጵያውያን የችግር መፍቻው ውይይትና ድርድር መሆኑን ሊረዱት ይገባል ያሉት ቃል አቀባይ ናቢላ፤ በህብረቱ በኩል የዘላቂ ሰላም መምጫው ድርድርና ውይይት ብቻ መሆኑ የሚታመንበት እንደሆነ አጽኖኦት ሰተው ተናግረዋል፤ “ አሁንም በኛ እመንት  በአገሪቱ ውስጥ ያለው ግጭት በዘላቂነት ሊወገድ የሚችለው በሰላማዊ መንገድ ብቻ ነው” በማለት ኢትዮጵያውያን ይህንን  በአውርፓ ህብረት በኩል በቸኛ ነው የተባለውን  የለላም መንገድ እንዲከተሉ አሳስበዋል።

ምዕራብ ጎጃም ውስጥ የሚገኝ ገጠራማ ስፍራ
ኢትዮጵያውያን የችግር መፍቻው ውይይትና ድርድር መሆኑን ሊረዱት ይገባል ያሉት ቃል አቀባይ ናቢላ፤ በህብረቱ በኩል የዘላቂ ሰላም መምጫው ድርድርና ውይይት ብቻ መሆኑ የሚታመንበት እንደሆነ አጽኖኦት ሰተው ተናግረዋል፤ ምስል Seyoum Getu/DW

በመራዊ ስለተፈጸመው ግድያ የወጡ ተጨማሪ መግለጭዎች

ክወራትት በፊት በመንግስትና የፍኖ ታጣቂዎች መካከል  ግጭት ከተጀመረ ወዲህ፤ ይህ በመራዊ  ከተማ ተፈጸመ የተባለው የስለማዊ ሰዎች ግድያ፤ ከፍተኛውና አሰቃቂው እንደሆነ በሰፊው እየተነገረ ነው።የአማራ ክልል የጸጥታ ሁኔታ የኢትዮጵያ ሰባዊ መብት ኮሚሺን ጥር 20 ቀን ማለዳ በመንግስት ወታደሮችና የፋኖ ታጣቂዎች መካከል የነበረውን ውጊያ ተክትሎ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸሙን  ባወጣው መገልጫ አስታውቋል። ኮሚሽኑ በመግለጫው የ45 የየተገደሉ ስለማዊ ሰዎችን ስም ዝርዝርም አካቷል። የመራዊው የሰላማዊ ሰዎች ግድያ  በሌሎች ዓለማቀፍ ሜዲያዎችም ሰፊ ሽፋን ተስቶታል።

ገበያው ንጉሴ

ታምራት ዲንሳ

እሸቴ በቀለ