1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት አቋም

ዓርብ፣ መስከረም 6 2015

የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚደንት ወይዘሮ ኡርዝላ ቮን ደርላየን በስትራቡርግ የአውሮጳ ፓርላማ ጉባኤ ባሰሙት ዓመታዊ ንግግራቸው፤ ህብረቱ በዓመቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የፖለቲካ፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አጀንዳዎችን ግልጽ አድርገዋል፤ የሚወሰዱ የማሻሻያ እርምጃዎችንም አስታውቀዋል።

https://p.dw.com/p/4GvoK
Frankreich | Ursula von der Leyen im Straßburger Europaparlament
ምስል Jean-Francois Badias/AP Photo/picture alliance

የአውሮፓ ኮሚሺን ፕረዝደንት ንግግር

የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚደንት ወይዘሮ ኡርዝላ ቮን ደርላየን ትናንት በስትራቡርግ የአውሮጳ ፓርላማ ጉባኤ ባሰሙት  ዓመታዊ ንግግራቸው፤ ህብረቱ በዓመቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የፖለቲካ፤ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አጀንዳዎችን ግልጽ አድርገዋል፤ የሚወሰዱ የማሻሻያ  እርምጃዎችንም አስታውቀዋል። የዩክሬን ጦርነትና ህብረቱ በጦርነቱ ምክንያት ያጋጠመው የኃይል አቅርቦት እጥረትና ቀውስ ዋናዎቹ የፕሬዝዳንቷ ንግግር ትኩረቶች ነበሩ።  

ወይዘሮ ቮን ዴር ላይን የዩክሬኑ ፕሬዝድናት ቮሌድሜር ዜሌንስኪ ባለቤት ወይዘሮ ኦሌና ዜሌንስኪ በክብር እንግዳነት በተገኙበት ባሰሙት ንግግራቸው፤ ዩክሬን በሩሲያ አንጻር እፈጸመች ያለውን ተጋድሎ አድንቀው፤ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችው ጦርነት በሁሉም ላይ የተስነዘረ ጥቃት እንደሆነ  አስታውቀዋል። “ይህ ሩሲያ በይክሬን ላይ ብቻ የከፈተችው ጦርነት አይደለም። ጦርነቱ በኃይል አቅርቦት ላይ፤ በኢኮኖሚያችን ላይ፤ በዕሴቶቻችንና ተስፋችን ላይ፤ በአጠቃላይም በዴሞክራሲያችን ላይ የተክፈተ ጦርነት ነው። ስለሆነም ዛሬ እዚህ የቆምኩት በሁላችን ትግልና ትብብር ፑቲን ይወድቃል፤ አውሮጳና ዩክሬይን ያሸንፋል በሚል እምነት ነው። ከዚሁ ጋር በማያይዝ ቮንዴር ላይን  የዩክሪኖችን ተጋሎና ጀግንነትም በዚህ ሁኔታ ገልጸውታል። “ብርቱነት ስም አለው ስሙም ዩክሬን ነው። ብርቱነት መልክ አለው መልኩም የዩክሬን ወንዶችና ሴቶች ፊት ነው በማለት በአሁኑ ወቅት ልዩ የሆነ ጽረ ሩሲያ ጦርነት እያካሄዱ መሆኑን አውስተዋል። 

Frankreich | Ursula von der Leyen im Straßburger Europaparlament
ምስል Jean-Francois Badias/AP Photo/picture alliance

የአውሮጳ ህብረትና አባል አገራቱ የዩክሬን ጦርነት ክተጀመረ ጀምሮ የገንዘብና የጦር መሳሪያ እርዳታ በገፍ እያቀረቡ መሆኑ የሚታወቅ ነው። በአንጻሩ በሩሲያ ላይ፤ ልዩ ልዩ የማዕቀብ ውሳኔዎችን በማሳለፍ አገሪቱ እንድተገለልና የኢኮኖሚ አቅሟ ጦርነትን መሸከም እዳይችል ለማድረግ ብዙ ጥረት ተደርጓል። ፕሬዚዳንቷ በዓመታዊ ንግግራቸው የተወሰዱትን እርምጃዎችና ተገኝቷል ያሏቸውን ውጤቶችም ዘርዝረዋል። “የሩሲያ የፋይናንስ ዘርፍ እስትንፋስ መቆሚያው ላይ ደርሷል። ሦስት አራተኛዎቹን የሩሲያ ባንኮች ከዓለማቀፉ ገበያ  ውጭ አድርገናቸዋል። አንድ ሺ የሚሆኑ ኩባንያዎች አገሪቱን ለቀው ወጥተዋል በማለት ሩሲያ በዩክሬን ላይ በክፍተችው ጦርነት ምክንያትና አውሮጳ ህብረት በጣለባት ማዕቀብ ምክኒያት የገባችበትን ቀወስ ገልጸዋል ።  

ይሁን እንጂ ህብረቱና  ሌሎች መእራባውያን አገሮች በሩሲያ ላይ የጣሉት ማዕቀብ የተፈለገውን ያህል የሩሲያን ኢክኖሚ እንዳላደክመውና ይልቁንም በተለይ በአውሮጳ ላይ የኃይል አቅርቦት እጥረት እንዳስክተለና በዚህም አውሮጳ በከፍተኛ  የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት እንደተመታ እይተገለጸ ነው።  

ከዚህ አንጻር ህብረቱ ችግሩን ለመቋቋም  የሚያስችሉ ልዩ ልዩ እርምጃዎችን እንደሚወስድና አባል አገሮችም ልክ እንደስካሁኑ በአንድነት በመቆም ይህን ችግር እንዲወጡ ወይዘሮ ቮንዴር ሌየን በንግግራቸው አሳስብውዋል። ሆኖም ግን አውሮፓ በዩክሬን ጦርነት ምክኒያት እየከፈለ ያለው ዋጋና የገባበት ቀውስ ህዝቦችን ለከፍተኛ ችግር ዳርጓል የሚሉ የተቃውሞ ድምጾች እየተሰሙ ነው። በተለያዩ ከተሞች ለምሳሌ በቅርቡ በፕራግ፤ ዜጎች አደባባይ ወተው ተቃውሟቸውን የገለጹ ሲሆን፤ በአንዳንድ አባል አገሮች ህብረቱ በዩክሬን ጦርነት ላይ በሚከተለው ፖሊሲና በተለይም በሩሲያ ላይ በተወሰዱት የማዕቀብ እርምጅዎች  ላይ ልዩነትና ተቃውሞ ያላቸው የፖለቲክ ፓርቲዎች ወደ መንግስት ስልጣን እየቀረቡ እንደሆነ እየተነገረ ነው። ወይዘሮ ቮንዴር ላይን ትናንት በፓርላማው ዓመታዊ ንግግራቸውን እያሰሙ በነበረበት እለትም፤ በስዊድን አፍቃሪ የአውሮጳ ህብረት የንበረው ፓርቲ ተሸንፎ በምትኩ በህብረቱ ፖሊሲዎች ላይ ቅሬታና ተቃውሞም ያሏቸው ቀኝ ዘመም ፕርቲዎች ወደ ስልጣን እንደመጡ ታውቁል። ስዊድን ከመጭው ጥር ወር ጀምሮ የህብረቱን የፕሬዚዳንት ስልጣን የምትይዝ ሲሆን፤ ይህም በወይዝሮ ቮን ዴር ላይን እቅዶች ተግባራዊነት ላይ የራሱ የሆነ ተጽኖ ሊያሳድር ይችላል እየተባለ ነው። ወይዘሮ ቮን ደር ላይን ግን ዛሬም በኪይቭ ተገኝተው ህብረቱ ለዩክሬን በቀጣይ ስለሚሰጠው ርዳታና የህብረቱ እጩ አባል እንድትሆን በተወሰነው መሰረትም ከወዲሁ በነጻ ገበያው ተጠቃሚ ስለምትሆነበት ከፕሬዝዳንት ዘለነስኪ ጋር መክረዋል። 

ገበያው ንጉሴ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ኂሩት መለሰ