የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ
ሰኞ፣ ነሐሴ 15 2015የአማራ ክልል ከአንዳንድ አካባቢዎች በቀር እየተረጋጋ መሆኑ ተገለፀ። በባህር ዳር የትራንስ ፖርት አገልግሎት ካለፉት ቀናት የተሻለ እንቅስቃሴ እንደሚታይ ባህርዳር የሚገኘዉ ወኪላችን ገልጿል። ይሁንና አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች የፀጥታ መደፍረስ መኖሩን የፋኖ ታጣቂዎች እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ወኪላችን ከተለያዩ አካባቢዎች የደረሰዉን መረጃ ገልጿል። በሌላ በኩል የመንግሥት አካላት በአማራ ክልል ጥያቄዎችን በተመለከተ ከህዝብ ጋር ዉይይት መጀመራቸዉ ተገልጿል።
የቀድሞው የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ኃላፊ ኮሎኔል አለበል አማረ በአለፈው ሐሙስ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቤተሰቦቻቸው አመልክተዋል። የኮሎኔሉ ታናሽ ወንድም እንደሆኑ የገለፁልን ገበየሁ አማረ፣ ወንድማቸው ባለፈው ሐሙስ ከሰዓት በፊት ባሕር ዳር ከተማ ውስጥ ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት በፀጥታ ኃይሎች ተወስደዋል፣ የት እንዳሉ እንደማያውቁም ተናግረዋል።
ሌላ የቅርብ ቤተሰብ አባል በበኩላቸው ኮሎኔል አለበል ባለፈው ሐሙስ ከሁለት አጃቢዎቻቸው ጋር በመንግስት ኃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አረጋግጠዋል። ኮሎኔሉ በተለምዶ "መኮድ " እየተባለ ከሚጠራው የባሕር ዳር አካባቢ እንደሚገኙ ቢሰሙም በዓይን ያያቸው ሰው ማግኘት እንዳልተቻለ ተናግረዋል።
ኮሎኔል አለበል ከ 2011 ዱ የአማራ ክልል አመራሮች ግድያ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ታስረው የነበረ ሲሆን መጨረሻ ላይ ነፃ መለቀቃቸው ይታወሳል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከፍተኛ ውጊያ የነበረባቸው በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬና ደንበጫ ከተሞች እየተረጋጉ አእንደሆነ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የመከላከያ ሰራዊት አባላትም በየከተሞቹ እንደሚታዩ አብራርተዋል። የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትም ቀስ በቀስ ወደስራ እየገቡ መሆናቸውንና የባጃጅ ተሽከርካሪዎችም በየከተሞቹ ይታያሉ ነው ያሉት። በአንዳንድ የክልሉ ወረዳ ከተሞች ደግሞ አሁንም የፋኖ ታጣቂዎች አእየተንቀሳቀሱ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። መራሮች ግድያ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ታስረው የነበረ ሲሆን መጨረሻ ላይ ነፃ መለቀቃቸው ይታወሳል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከፍተኛ ውጊያ የነበረባቸው በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬና ደንበጫ ከተሞች እየተረጋጉ አእንደሆነ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የመከላከያ ሰራዊት አባላትም በየከተሞቹ እንደሚታዩ አብራርተዋል። የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትም ቀስ በቀስ ወደስራ እየገቡ መሆናቸውንና የባጃጅ ተሽከርካሪዎችም በየከተሞቹ ይታያሉ ነው ያሉት። በአንዳንድ የክልሉ ወረዳ ከተሞች ደግሞ አሁንም የፋኖ ታጣቂዎች እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ።
ዓለምነዉ መኮንን
አዜብ ታደሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ