Eshete Bekeleረቡዕ፣ ነሐሴ 8 2016ሶማሌላንድ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን የምታሸማግለው ቱርክ ገለልተኛ አይደለችም ስትል ከሰሰች። የሶማሌላንድ ክስ የተደመጠው በአንካራ ለሁለተኛ ጊዜ የተካሔደው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ውይይት ያለ ውጤት ከተበተነ በኋላ ነው። የሱዳንን ጦርነት ለማብቃት ያለመ ድርድር የብሔራዊው ጦር አዛዥ ጄነራል አብደል ፋታኅ አል-ቡርኻን በሌሉበት ተጀመረ። ግብጽ እና ሶማሊያ የወታደራዊ ትብብር ፕሮቶኮል ሥምምነት ተፈራረሙ። በጋዛ ውጊያ የገጠሙ ኃይሎች ተኩስ እንዲያቆሙ ለማድረግ ያቀደ ድርድር በቃጣር ሊካሔድ ነው። ጀርመን የኖርድ ስትሪም የጋዝ ማስተላለፊያን በማፈንዳት የጠረጠረችውን ግለሰብ ለመያዝ የእስር ማዘዣ አወጣች።