Eshete Bekeleሐሙስ፣ ታኅሣሥ 18 2016የተ.መ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን በኢትዮጵያ ሐቀኛ የሽግግር ፍትኅ ተግባራዊ እንዲሆን ጥሪ አቀረበ። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “መንግሥት በፌዴራልም ሆነ በክልል ደረጃ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነቱን በማያሻማ መልኩ እንዲያሳይ” ጥሪ አስተላልፏል። በኦሮሚያ ክልል ሖሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በተፈጸመ የአየር ጥቃት ስምንት ሰዎች ሲገደሉ አምስት መቁሰላቸውን ሁለት እማኞች ተናገሩ። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል አዛዥ ብርጋዴር ጀነራል መሐመድ ሓምዳን ዳጋሎ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተገናኙ። የሶማሊያ እና የሶማሌላንድ መሪዎች ለሚወዛገቡባቸው ጉዳዮች መፍትሔ ለማበጀት በጅቡቲ ንግግር ጀመሩ