1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቱሪዝም አቅምና የጸጥታው ፈተና

ረቡዕ፣ ጥር 1 2016

በኦሮሚያ ክልል ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የቱሪዝምን ዘርፍ ትልቁ የኢኮኖሚ ደጋፊ አቅም ለማድረግ ሰፋፊ እንቅስቃሴዎች ስለመከወናቸው ይነገራል፡፡ በዚህም አሁን ላይ የክልሉን ቱሪዝም የአገሪቱ የቱሪስት ካርታ ላይ ማስገባት ስለመቻሉ ነው የሚወሳው፡፡

https://p.dw.com/p/4b5FS
Äthiopien Oromia Region Tourismus-Seiten
የባቱ ሐይቅ ዳርቻ የቱሪዝም መዳረሻ ምስል Seyoum Getu/DW

የኦሮሚያ ቱሪዝም በጸጥታ ስጋት ውስጥም ዉጤታማ መሆኑ ተገለጸ

የቱሪዝም አቅምና የጸጥታው ፈተና

በኦሮሚያ ክልል ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የቱሪዝምን ዘርፍ ትልቁ የኢኮኖሚ ደጋፊ አቅም ለማድረግ ሰፋፊ እንቅስቃሴዎች ስለመከወናቸው ይነገራል፡፡

በዚህም አሁን ላይ የክልሉን ቱሪዝም የአገሪቱ የቱሪስት ካርታ ላይ ማስገባት ስለመቻሉ ነው የሚወሳው፡፡

ክልሉ በአስቸጋሪ የጸጥታ ሁኔታ በሚፈተንበት ባሁን ወቅት የክልሉ የቱሪዝም ገቢ አመንጪነት ከምን ጊዜውም በላይ የላቀ ነው በሚል በክልሉ ቱሪዝም ኮሚሽን ተነግሯል፡፡

 

የቱሪዝም እምቅ አቅምና የመዳረሻዎች ልማት

ገና፣ ጥምቀትና ሌሎችም ሰዎችን የሚያሰባስብ የአደባባይ በዓላት ከሚዘወተርባቸው ወቅቶች አንደኛው በሆነው በዚህ የበጋ ወቅት ኢትዮጵያ ከፍተኛውን የጎብኚዎች ቁጥር ተቀብላ የምታስተናግድበት ወቅት ተብሎ ይታመናል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትም በተለያዩ ጊዜያት እንደሚገልጸው የቱሪዝም ዘርፍን ኢኮኖሚውን እንዲደግፍ ዋነኛ ትኩረት ከተሰጣቸው አንዱ በሚል ይጠቁሟል፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ በዚህ ዘርፍ ላይ በስፋት እየሰራ መሆኑን የሚገልጸው የኦሮሚያ ክልል በተለይም በመዳረሻዎች ልማት ላይ አተኩሮ እንደሚሰራ ያወሳል፡፡ በተለይም ደግሞ በኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን በኩል ክልሉ ያለውን የቱሪዝም ሃብት በስፋት እንደሚተዋወቁም ይገለጻል፡፡ አቶ ኢፋባስ አብዱልዋሃድ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ናቸው፡፡

አቶ ኢፋባስ አብዱልዋሃድ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ናቸው፡፡
ገና፣ ጥምቀትና ሌሎችም ሰዎችን የሚያሰባስብ የአደባባይ በዓላት ከሚዘወተርባቸው ወቅቶች አንደኛው በሆነው በዚህ የበጋ ወቅት ኢትዮጵያ ከፍተኛውን የጎብኚዎች ቁጥር ተቀብላ የምታስተናግድበት ወቅት ተብሎ ይታመናል፡፡ምስል Seyoum Getu/DW

እንደሳቸው ገለጻ ክልሉ ባሁን ወቅት ባሉት የቱሪስት መዳረሻዎች ላይ አበክሮ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህን ወቅት ልዩ የጎብኚዎች ትኩረት በሚስበው የዝዋይ ሃይቅ ላይ የጥምቀት በኣልን በልዩ ድባብ ማክበርን ጨምሮ በዓለም ቱሪዝም ድርጅት ምርጥ የቱሪዝም መዳረሻ በሚል እውቅና የተሰጠው የወንጪ ኃይቅ ላይ የተሰራውን የመዳረሻ ልማትን እንዲሁም እንደ ጅማ ያሉትን አከባቢዎች የጎብኚዎች መዳረሻ ለማድረግ ሰፊ የማስተዋወቅ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም በቅርቡ እንኳ በርካታ የውጪ አገራት ጎብኚዎችን ወደ ጂማ ማቅናታቸውን በማሳያነት አቅርበው ክልሉ የጎብኚዎችን ትኩረት መሳቡን አስረድተዋል፡፡

ቱሪዝምና የጸጥታ ፈተናው

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በኦሮሚያ በተለያዩ አከባቢዎች በሚስተዋለው የከፋው የጸጥታ ስጋት ዘርፉ እንደሚፈተን የአደባባይ ሃቅ ነው፡፡ በተለይም በቅርቡ በክልሉ በተለያዩ አቅጣጫዎች መንገደኞች ላይ የተጋረጡ ጥቃቶች እና በተሸከርካሪዎች ላይ የተፈጸመው የቃጠሎ አደጋዎች ዘርፉን ካስደነገጡ ይባልላቸዋል፡፡ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ አቶ ኢፋባስም የዚህም አደጋ ተጽእኖ አይሸሽጉም፡፡

 “ቱሪዝም ከነትርጉሙም ጉዞን የሚያካትት ነው፡፡ ሰዎች ለ24 ሰኣታት እና ከዚ በላይ ከሚኖሩበት አከባቢ ተንቀሳቅሰው ሌላ ቦታ ተጉዘው ቆይታ ማድረግ ነው ቱሪዝም፡፡ ከዚህ አንጻር ሰላም ቁልፍ ሚና አለው፡፡ ጎብኚዎች በሚሄዱበት ስፍራ ደህንነት ካልተሰማቸው እንኳን የሚቆዩበትን ጊዜ ማራዘም እንቅስቃሴም አያደርጉም፡፡ በመሆኑም ደህንነት ለጎብኚዎች ዋናው ነትብ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ በዚህ አራት ዓመት ውስጥ ህ በአገራችን ፈታኝ ነው፡፡ አንዱ ሲል ሌላ እየተባለ ዘርፉን ፈትኖታል፡፡ ግን ደግሞ እነዚ ፈተናዎች አሉ ብለን እኛ መስራቱን አናቆምም” ብለዋል፡፡

ወንጪ ሐይቅ የቱሪዝም መዳረሻ
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በኦሮሚያ በተለያዩ አከባቢዎች በሚስተዋለው የከፋው የጸጥታ ስጋት ዘርፉ እንደሚፈተን የአደባባይ ሃቅ ነው፡፡ በተለይም በቅርቡ በክልሉ በተለያዩ አቅጣጫዎች መንገደኞች ላይ የተጋረጡ ጥቃቶች እና በተሸከርካሪዎች ላይ የተፈጸመው የቃጠሎ አደጋዎች ዘርፉን ካስደነገጡ ይባልላቸዋል፡፡ምስል Seyoum Getu/DW

ቱሪዝም በኦሮሚያ በገቢ እምርታን ስለማሳየቱ

አቶ ኢፋባስ እንደሚሉት እንዲያም ሆኖ በቅርቡ ከቱሪዝም በተለይም በኦሮሚያ ክልል የሚገኘው ገቢ ከየትኛውም ጊዜ የላቀ ነው ይላሉ፡፡ “ባለፈው የበጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልል ከቱሪዝም የተገኘው ገቢ ወደ 9.6 ቢሊየን ብር ነው፡፡ ይሄ ገቢ ከዚህ በፊት ተገኝቶ አያውቅም፡፡ ክልሉ ፓርኮችና ኢኮቱሪዝም ሳቶች ላይ አበክሮ እየሰራ ነው፡፡ በክልሉ 24 አዳዲስ ብሔራዊ ፓርኮችና 18 የኢኮቱሪዝም አሁን ላይ በኢስ መልክ ተከልለዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር አሁን ኦሮሚን የቱሪዝም ካርታ ላይ በማስገባት ሰፊ ትኩረት ለዘርፉ ተሰጥቶ በርካታ ስራዎች ተሰረቷል” በማለትም አስተያየታቸውን አጋርተውናል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበው የቱሪዝም ጥሪ

በቅርቡ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ደ/ር) የቱሪዝም መዳረሻን በሚያስመርቁበት ወቅት በሶስት ዙር ብለው ባቀረቡት ጥሪ ኢትዮጵያውያን አገራቸውን እንዲጎበኙ መጠየቃቸው ይታወቃል፡፡ በጥሪው መሰረት ምን ያህል ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መጥተው እየጎበኙ ነው ለሚለው ጥያቄ ዶቼ ቬለ በተለይም ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጄንሲ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ግን ለጊዜው ባለመሳካቱ ጥረቱ አልሰመረም፡፡

የወንጪ ሐይቅ የቱሪዝም መዳረሻ
በቅርቡ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ደ/ር) የቱሪዝም መዳረሻን በሚያስመርቁበት ወቅት በሶስት ዙር ብለው ባቀረቡት ጥሪ ኢትዮጵያውያን አገራቸውን እንዲጎበኙ መጠየቃቸው ይታወቃል፡፡ ምስል Seyoum Getu/DW

ምንም እንኳ ወደ አገራቸው የመጡትን ኢትዮጵያውያን ቁጥር ባይገልጹትም የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ አቶ ኢፋባስ ግን ባርካታ ያሉት ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ክልል መጥተው እየጎበኙ ነው፡፡ “ካለፈው ገና በዓል ጀምሮ ኢትዮጵያውን መጥተው አገራቸውን እንዲጎበኙ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቀረቡት ጥሪ መሰረት በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እየገቡ ነው” በማለት አስረድተዋል፡፡

ስዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

ማንተጋፍቶት ስለሺ