1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስራኤል ሀማስ ጦርነትና የአውሮጳውያን አቋም

ማክሰኞ፣ መስከረም 29 2016

የአውሮጳ ኅብረት ትናንት የአሸባሪውን የሀማስ ጥቃት በጥድፊያ አውግዞ ለፍልስጤም ሊሰጥ ያቀደውን ከ700 ሚሊየን ዶላር በላይ የልማት እርዳታ መያዙን አሳውቆ ነበር ። ሆኖም ማምሻውን ውሳኔውን ሽሯል። የጀርመንን ጨምሮ የአውሮጳ ሀገራት ፖለቲከኞች ለፍልስጤም የሚሰጡት እርዳታ እንደገና ይታይ እያሉ ነው።

https://p.dw.com/p/4XN0N
Gazastreifen |  israelische Vergeltungsluftangriffe
ምስል Mahmud Hams/AFP/Getty Images

የእስራኤል ሀማስ ጦርነትና የአውሮጳውያን አቋም

የእስራኤልና የአሸባሪው ሀማስ ጦርነት ተባብሷል። እስራኤል በጋዛ የምታካሂደውን የአየር ጥቃት አጠናክራ ስትቀጥል ፍልስጤማውያን ተዋጊዎችም ወደ ቴላቪቭና ወደ ማዕከላዊ እስራኤል ሮኬቶችን ሲተኩሱ አምሽተዋል። አሸባሪ የተባለው ሀማስ ባለፈው ቅዳሜ እስራኤል ላይ ባደረሰው ድንገተኛ ጥቃት በርካታ እስራኤላውያን ከተገደሉ በኋላ እስራኤል በጋዛ የጀመረችውን መጠነ ሰፊ የአጸፋ እርምጃ አጠናክራ ቀጥላለች። በእስራኤል ታሪክ ከባድ በተባለው በዚህ ጥቃት ቁጥራቸው 900 የሚጠጋ ሰዎች ተገድለዋል። ከመካከላቸው በኔጌቬ በረሀ በመካሄድ ላይ በነበረው የሙዚቃ ድግስ ላይ ሀማስ በከፈተው ጥቃት የሞቱት 260 ሰዎች ይገኙበታል። በእስራኤል አጸፋ ጥቃትም ከፍልስጤም በኩል 687 ሰዎች መገደላቸውን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር  አስታውቋል።ማሕደረ ዜና፣ የእስራኤልና ሐማስ ጦርነት

ማምሻውን የጀርመንን ጨምሮ የአውሮጳ ሀገራት ፖለቲከኞች ለፍልስጤም የሚሰጡት እርዳታ እንደገና ይታይ እያሉ ነው። 
ዶክተር ለማ እንደሚሉት ግን በሀማስ ከፍተኛ ጥቃት የደረሰባት እስራኤል እንደቀድሞው በዚህ ትስማማለች ብለው አያምኑም። የአውሮጳ ኅብረት ትናንት የአሸባሪውን የሀማስ ጥቃት በጥድፊያ አውግዞ ለፍልስጤም ሊሰጥ ያቀደውን ከ700 ሚሊየን ዶላር በላይ የልማት እርዳታ መያዙን አሳውቆ ነበር ። ምስል Abed Rahim Khatib/dpa/picture alliance

የሀማስን ጥቃት ተሽቀዳድመው ያወገዙት ምዕራባውያን መንግሥታት ከእስራኤል ጎን እንደሚቆሙና ድግፍ እንደሚያደርጉላትም አስታውቀዋል። ጀርመን፣ፈረንሳይ ፣ዩናይትድ ስቴትስ ብሪታንያና ጣሊያን ዛሬ ባወጡት የጋራ መግለጫ ከእስራኤል ጎን እንደሚቆሙ ተናግረዋል። አምስቱ ኃያላን መንግሥታት የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል እንዳለው በመግለጫቸው ሀማስን ሳይጨምር ለፍልስጤማውያን ሕጋዊ ፍላጎቶች እውቅና ድጋፍ እንሰጣለንም ብለዋል።  እስራኤል በጋዛ ትጠቀማለች የሚባለው ያልተመጣጠነ ኅይል ጉዳይ ደግሞ ከምዕራባውያን አጋሮቿ በኩል ሲነሳ አለመነሳቱ ማስተዛዘቡ አልቀረም። ከዚሁ ጋር ይልማ እንደሚለው አሸባሪ በተባለው ሀማስና በእስራኤል የሚካሄደው ጦርነት ወደ አካባቢው አገራት የመሻገሩ ስጋት ከየአቅጣጫው ጎልቶ ይሰማል።ጀርመንን ጨምሮ ምዕራባውያን መንግሥታት በእስራኤል ሀማስ ጦርነት ላይ ስለያዙት አቋም ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ሳይንስ ምሁርና የሕግ ባለሞያ ዶክተር ለማም ስጋቱን ይጋራሉ።
ዶክተር ለማ እንደሚሉት  እስራኤል በጋዛ ላይ ስለምትፈጽመው ያልተመጣጣነ የሚባል ጥቃት አጋሮቿ አሁን አስተያየት ይሰጣሉ ብለው አይጠብቁም ። የእስራኤል መንግሥት ምስረታ 75ኛ ዓመትበሌላ በኩል እስራኤል የአጸፋ እርምጃዋን ካጠናከረች በኋላ ሀማስ በፍልስጤም ግዛት በእስራኤል ድብደባ በሚወድም እያንዳንዱ ቤት፣ጠልፎ የወሰዳቸውን ሰዎች እንደሚገድል በማዛት ላይ ነው። እስራኤል የታያዙ አባላቱም በለውጥ እንዲሰጡት እየጠየቀ ነው። ዶክተር ለማ እንደሚሉት ግን በሀማስ ከፍተኛ ጥቃት የደረሰባት እስራኤል እንደቀድሞው በዚህ ትስማማለች ብለው አያምኑም። 
የአውሮጳ ኅብረት ትናንት የአሸባሪውን የሀማስ ጥቃት በጥድፊያ አውግዞ ለፍልስጤም ሊሰጥ ያቀደውን ከ700 ሚሊየን ዶላር በላይ የልማት እርዳታ መያዙን አሳውቆ ነበር ። ሆኖም ማምሻውን ውሳኔውን ሽሯል። የጀርመንን ጨምሮ የአውሮጳ ሀገራት ፖለቲከኞች ለፍልስጤም የሚሰጡት እርዳታ እንደገና ይታይ እያሉ ነው። እስራኤልና የሀማስን ጦርነት የሚቃወሙ እና የሚደግፉ ሰላማዊ ሰልፎችም በርሊንን ጨምሮ በተለያዩ የዓለማችን ከተሞች ተካሂደዋል።  በተለይ ጀርመን በተካሄዱ ሰላማዊ ሰልፎች ላይ ሀማስን በመደገፍ የወጡ ሰዎች ላይ ክትትል እንደሚያደርግና እርምጃ እንደሚወስድም መንግሥት አስታውቋል።
ኂሩት መለሰ

አሸባሪ የተባለው ሀማስ ባለፈው ቅዳሜ እስራኤል ላይ ባደረሰው ድንገተኛ ጥቃት በርካታ እስራኤላውያን ከተገደሉ በኋላ እስራኤል በጋዛ የጀመረችውን መጠነ ሰፊ የአጸፋ እርምጃ አጠናክራ ቀጥላለች።
የእስራኤልና የአሸባሪው ሀማስ ጦርነት ተባብሷል። እስራኤል በጋዛ የምታካሂደውን የአየር ጥቃት አጠናክራ ስትቀጥል ፍልስጤማውያን ተዋጊዎችም ወደ ቴላቪቭና ወደ ማዕከላዊ እስራኤል ሮኬቶችን ሲተኩሱ አምሽተዋል። አሸባሪ የተባለው ሀማስ ባለፈው ቅዳሜ እስራኤል ላይ ባደረሰው ድንገተኛ ጥቃት በርካታ እስራኤላውያን ከተገደሉ በኋላ እስራኤል በጋዛ የጀመረችውን መጠነ ሰፊ የአጸፋ እርምጃ አጠናክራ ቀጥላለች። ምስል Markus Schreiber/AP/picture alliance

እሸቴ በቀለ