1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተመራጩ የፈረንሳይ ፕሬዚደንትና ቀጣዩ የአዉሮጳ ፖለቲካ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 19 2014

በፈረንሳይ በተካሂደው ፕሪዝዳንታዊ ምርጫ አገሪቱን ላለፉት አምስት ዓመታት የመሩት የአርባ አራት ዓመቱ ጎልማሳ ኤማኑኤል ማክሮ በድጋሜ አሸናፊ ሁነዋል። ፕሬዝዳንት ማክሮ  ለሁለተኛ ግዜ ያሽነፉት ለሁለተኛ ግዜ እክስመጨረሻው የተፎካክሯቸውን  ብሔረተኛዋን ወይዘሮ ማሪ ሌፒንን በሰፊ ልዩነት በልጠው ነው።

https://p.dw.com/p/4ASrz
Frankreich Präsidentschaftswahl Wahlkampf Emmanuel Macron
ምስል Thierry Breton/PanoramiC/imago images

ለፕሬዝዳንቱ ፈጥነው የደስታ መልክት አስተላለፈዋል

ሚያዝያ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ዕሁድ በፈረንሳይ በተካሂደው ፕሪዝዳንታዊ ምርጫ አገሪቱን ላለፉት አምስት ዓመታት የመሩት የአርባ አራት ዓመቱ ጎልማሳ ኤማኑኤል ማክሮ በድጋሜ አሸናፊ ሁነዋል። ፕሬዝዳንት ማክሮ  ለሁለተኛ ግዜ ያሽነፉት ለሁለተኛ ግዜ እክስመጨረሻው የተፎካክሯቸውን  ብሔረተኛዋን ወይዘሮ ማሪ ሌፒንን በሰፊ ልዩነት በልጠው ነው። ሚስተር ማክሮ በፈረንሳይ ከሀያ ዓመታት ወዲህ በተከታታይ ያሸነፉ በቸኛ ፕሬዝዳንት በመሆንም እየተጠቀሱ ነው። ፕሪዝዳንቱ  አሸናፊ  ለሆኑበት የዚህ ሁለተኛ ዙር ውድድር የበቁት፤ ከሁለት ሳምንትት በፊት በተካሂደውና በርካታ ተወዳዳሪዎች በተሳተፉበት ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሚስተር ማክሮን፤ በ28 ከመቶ ወይዘሮ ለፔን ደግሞ በ23 ከመቶ ውጤት  ከፍተኛውን ድምፅ ያገኙ ተወዳዳሪዎች ስለነበሩ ነው። ሁለቱም ባለፉት  ሁለት ስምንታት ከፍተኛ የምርጫ ዘመቻዎችን ሲያካሂዱ ቆይተው፤ ባለፈው ዕሁድ በተደረገው የመለያ ምርጫ ሚስተር ማክሮን የመራጩን ህዝብ 41.5 ከመቶ ያገኘቱን ተፎካካሪያቸውን ወይዘሮ ሌፔንን 58.5 ከመቶ በማግኘት በሰፊ ልዩነት አሸንፍዋቸዋል። ዛሬ አፕሪል 24 2022 ዓ.ም አብዛኛዎቻችሁ አገሪቱን ለሌላ አምስት ዓመት እንድመራ መተማመኛ ስታችሁኛል`ሲሉም ምሽት ላይ በመሀል ፓሪስ ለተሰበሰቡት ደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግር አሸናፊነታቸውን አብስረዋል። 

Präsidentschaftswahl in Frankreich, Stichwahl, Marine Le Pen
ምስል Francois Mori/AP Photo/picture alliance

ሚስተር ማክሮንና ወይዘሮ ሌፔን በፈረንሳይ ፕሬዝዳንታዊ ውድድር በሁለተኛ ዙር የመለያ ውድድር ሲፎካከሩ ይህ የመጀመሪያ ግዚያቸው አይደለም። እንደ ጎርጎረሳዉያን አቆጣጠር በ2017 ዓ.ም ሚስተር ማክሮን ከመሀል ቀኝ ፓርቲያቸው ወጥተው የራሳቸውን ፓርቲ በመመስረት ልክ እንዳሁኑ ከወይዘሮ ሌፒን ጋር በሁለተኛ ዙር ውድድር ተፎካክረው፤ የመራጩን ህዝብ 66 ከመቶ በማግኘት ወይዘሮ ሌፒንን እጅግ በስፋ ልዩነት አሸንፈዋቸው ነበር። ወይዘሮ ሌፔን የፈረንሳይ አክራሪ ብሄረተኛ ፓርቲ መሪ ሲሆኑ፤ በጸረ ስደተኛና ፍላስያን  እንዲሁም ሙስሊም ሴቶች የሚለብሱትን ቡርቃ በመቃወም ይታወቃሉ። ፈረንሳይ ሉላኢዊንቷን ለአውሮፓ ህብረት  አሳልፋ ሰታለች በማለትም የአውሮፓ ህብረት  የአባል አገሮቹን ልኡላዊ መብት ባከበረና በጠበቀ ሁኒታ መሻሻል አለበት በማለት ይከራከራሉ። አሸንፈው ስልጣን ቢይዙ፤ ፈረንሳይን ከስሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ እንድሚያስወጡም ሲናገሩ ቆይተዋል። በዘንድሮው የምርጫ ዘመቻም እነዚህ መሰረታዊ የፓቲያቸው እምነቶችና ፖሊሶዎች እንዳሉ ሁኔው፤ የኑሮ ውድነት  ጉዳይ ዋና የቅስቀሳ አጀንዳ ሁኖ ተነስቷል።  ሚስተር ማክሮን ከሰፈው ህዝብ የራቁና የህዝቡን ችግር የማይረዱ ናቸው ሲሉም ወንጅለዋቸዋል።

ሚስተር ማክሮን በበኩላቸው ወይዘሮ ሌፔንና ፓርቲያቸው ለፈረንሳይ ህዝብና ለዘመኑ ዴሞክራሲ የማይመጥኑ የዘረኝነት ፖሊሲ የሚያራምዱ ናቸው በማለት ነበር ቅስቀሳቸውን ሲያክሂዱ የቆዩት።  በአውሮፓ ህብረት አፍቃሪነታቸው የሚታወቁት  ሚስተር ማክሮ፤ ፈረንሳይ የአውሮፓ ህብረትን  በማጠናከር አህጉራዊና አለማቀፋዊ ሚናዋን መጫወት ይገባታል በማለትም የወይዘሮ ሌፔን የብሂረተንነት ፖለቲካን ሲኮንኑና ሲያቀሉ ነው የከረሙት፤ በተለይ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ባክሂዷቸው የምርጫ ዘመቻዎች፤ በየከተሞቹ አደባባባዎች በመገኘትና ከህዝብ ጋር በመወያየት  የህዝብን ችግር የማይረዱና ከህዝቡ የራቁ ናቸው የሚለውን ትችት ለማስተባባበል ሞክረዋል። የህዝቡን ችግር ከራሳቸው አንደበት የሰሙና የተረዱ ማሆናቸውን በመግለጽም፤ በስልጣን ቆይታቸው ማሻሽዎችን እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል። ከሁሉም በላይ ግን የዘንድሮውን  የፈረንሳይን የምርጫ ልዩ ያደረገው በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ይለው የዩክሬን ጦርነትና እያስክተለ ያለው ችግር ነበር። ፈረንሳይ በአውሮፓ ህብረትና ኔቶ አባልነቷ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን ጦርነት በማውገዝ የጸረ ሩሲያ የምዕራባውያን ህብረት ዋና አጋር አገር ናት። ወይዘሮ ሌፒን ግን ምንም እንኳ አሁን ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን ጦርነት ቢይወግዙም፤ የፕሬዝድንት ፑቲን  ወዳጅ እንደሆኑ ነው የሚታወቀው። በዚህም ምክኒያት እሳቸው ቢያሸንፉ፤ የምራቡን አለም ጸረ ሩሲያ አቋም ሊያናጉና የአውርፓ ህብረተንም አንድነት ሊነቀንቁ ይችላሉ ተብለው ነበር የተፈሩት። እሳቸው ግን ዛሬም ያብዛኝዎቹን ፈረንሳዮች ይሁንታ ባለማግኘታቸው የፕሬዝደንትነት ህልማቸው ዕውን ሳይሆን ቀርቷል።

Infografik Präsidentschaftswahl Frankreich zweite Runde ES

ሆኖም ግን ወይዘሮ ሌፔን ምንም እንኳ ምርጫውን አሸንፈው የፕሬዝዳንትነት መንበሩን ባይጨብጡም ያገኙት ውጤት ግን ከመቺውም ግዜ ይበልጥ አሁን  በፈረንሳይ ፖለቲካ ትልቅ ሚና እንዲኖራቸው የሚያደርግ እንደሆነና ትግላቸውንም እንደሚቀጥሉ ነው ዕሁድ ምሺት ለደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ነግግር ያስታወቁት። “የምናራምዳቸው ህሳቦችና እምነቶቻችን በሁለተኛው ዙር ውድድር  43 ከመቶ ድምጽ በማግኘት የበለጠ ተቀባየነት  አግንተዋል። ይህ በራሱ ትልቅ ድል ሲሆን ይህም የፈረንሳዮችን መብት ለማስክበርና ለማስጠበቅ የምናደርገውን ትግል አጠናክረን እንድንቀጥል የሚያደርግ ነው” በማለት እሳቸውም ሆነ ፓርቲያቸው የፖቲካ ትግላቸውን አጠነክረው የሚቀጥሉ ማሆናቸውን ገልጸዋል።

የምርጫው ውጤት እንደተሰማ የአውሮፓ ህብረትና  የአባል አገሮች መንግስታት ለፕሬዝዳንት ማክሮን ፈጥነው የደስታ መልክት አስተላለፈዋል። የአውሮፓ ካውንስል ፕሬዝዳንት ሚስተር ሚሸል  በዚህ አስቸጋሪ ወቅት  ጠንካራ አውሮፓና ለአውሮፓ ህብረት መጠናከር ቁርጠኛ የሆነች ፈረንስይ ያስፈልጋሉ በማለት፤ እሳቸው በማሸንፋቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። የኮሚሽኑ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ኡርሱላ ቮንዴር ለየንም በውጤቱ በጣም እንደተደሰቱና ይህም በመልካም ሁኒታ ላይ ያለውን ትብብራቸውን ለማስቀጥል እንደሚረዳ ያላቸውን እምነት ገለጸዋል፡፤ የጀርመን፣ ጣሊያን ኔዘርላንድስና ሌሎች ያውሮፓ ህብረት አገሮች መሪዎችና የኔቶ አባል አገሮች መንግስታት፤ ለፕሬዝዳንት ማክሮን ያስተላለፏቸው መልክቶች የምርጫው ውጤት ለነሱም እፎይታ ያስገኘላቸው መሆኑን በመግለጽ ጭምር ነው። የቻይናና የሩሲያ መሪዎችም እንደዚሁ የደስታ መልክት ለፕሬዝዳንት  ማክሮ አስተላልፈዋል።

Präsidentschaftswahlen Frankreich | Emmanuel Macron und Marine Le Pen
ምስል Patrick Batard/abaca/picture alliance

የምዕራባውያን መንግስታት በተለይ ደግሞ የአውሮፓ ህብረት አገሮች የፈርንሳይን ምርጫ በተለየ ሁኒታ መከታተል ብቻ ሳይሆን አንዳንንዶች ለምሳሌ እንደ ፖርቱጋልና ስፔን የመሳሰሉት፤ ፈረንሳዮች ብሄረተኛዋን ሌፔንን እንዳይመርጡ ማሳሰቢያ ሲሰጡ እንድነበር ተገልጿል። ሚስተር ፒየር ሃስኪ የተባሉ ፈረንሳዊ የፖለቲካ ተንታኝ፤  የፈረንሳይ ምርጫ፤ የአውሮፓ ህብረትን በተለየ ሁኒታ  ያሳስበበት ምክኒያት፤ ወይዘሮ ለፔን ቢያሸንፉ ከፍተኛ ቀውስ ሊከተል ይችል ስለነበር ነው ያላሉ።፡ “በወይዝሮ ለፔን ማሸነፍ ምክኒያት ሊከተል የሚችልን ቀውስ አውሮፓ ሊሸከም አይችልም፡፤ ምክኒያቱም የሳቸው ፕሮግራም ጸረ የአውሮፓ ህብረት በመሆኑ ህብረቱን ሊከፋፍል ስለሚችል ነው” በማለት አሁን የተገኘው ውጤት ግን ህብረቱን ከሌላ ቀውስ ታድጎታል ብለዋል ።

በጦርነት እየታመሰች ያለችው ዩክሬንም የፈረንሳይን ምርጫ በንቃት ስትክታተል ነው የክረመችው። የሚስተር ፑቲን ደጋፊ ናቸው የሚባሉት ወይዘሮ ለፔን ቢያሸንፉ ፤ለዩክሬን መጥፎ ዜና ነበር የሚሆነው የሚለው የፍራንስ 24 የዩክሬን ዘጋቢ ሚስተር ጋሌሪ ክራክ ውጤቱ የንበረውን ስጋት የቀነሰ መሆኑን አስታውቋል። “የፈረንሳይን ምርጫ ዩክሬን በቅርብ ነበር የምትከታተለው  ምክኒይቱም ለፔን ካሸነፉ የምዕርባውያን ድጋፍ ይቀንሳል ወይም ይስተጓጎላል  የሚል ስጋት ስለነበር ነው በማለት  ውጤቱ ለኪየቭም እፎይታን ያስገኘ መሆኑን ገልጿል። 

ሚስተር ኤማኑኤል ማክሮ ይህን፤ የሁሉንም ትኩረት የሳባውን ምርጫ ቢያሸንፉም በርክታ ተግዳሮትችና ፈተናዎች ግን  ከፊታቸው እንደሚጠብቋቸው ነው የሚታወቀው። የምርጫው ውጤት ነባሮቹን ፓርቲዎች እንዳልነበሩ አድርጎ፤ የፈረንሳይን የፖለቲካ መድረክ፤ የማክሮን ሊበራል ፓርቲ፣ የግራዎቹና የወይዘሮ ለፔን ብሂረተኛ ፓርቲዎች መፎካከሪያ መድረክ ያደረገው ሲሆን፤ ሶስቱም በመጭው የስኔ ወር በሚድረገው የምክር ቤት ምርጫ የተሻለ ውጤት እናመጣለን ባይ ናቸው።  የሚስተር ማክሮን የወደፊት ስኬትም በስኔው የምክር ቤት ምርጫ በሚያገኙት ድምጽ ይወሰናል ነው የሚባለው። በዚህም ምክኒያት ማክሮን ለግራዎቹም ለወይዘሮ ለፔን ደጋፊዎችም እሳቸው ከእንግዲህ የሁሉም ፕሪዝዳንት እንጂ የአንድ ፓርቲ ዕጩ አለመሆናቸውን በመግለጽ የአንድነትና የትብብር ጥሪ አቅርበዋል። ማክሮን 28 ከመቶ ለሚሆኑትና ድምጸ ተአቅቦ ላደረጉ ፈርንሳዮችም መልክት አስተላለፈዋል። “ድምጽ ያልሰጡ ፈረንሳዮችንም አስባለሁ። አለመምረጥ በራሱ ተቃውሞ እንድሆነና ይህም መልስ የሚሻ መሆኑን እገነዘባለሁ በማለት እሳችውና መንግስታቸው በሚቀጥሉት ዓመታት የሁሉንም ዜጎች ጥያቄዎች እንደሚያስተናግዱ አስታውቀዋል ።

Präsidentschaftswahl in Frankreich
ምስል Francois Mori/AP/dpa/picture alliance

ፕሬዝድንቱ ያገኙትን  ድል በመጠቀም  በስደተኞችና ፈላስያን ጉዳይ የአውሮፓ ህብረት የጋራ ፖሊስ እንዲኖረውና አባል አገሮች እንዲተባበሩ ለማድረግ ጥረት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ። አገራቸው እስከ መጭው የስኔ ወር መጨረሻ ድረስ   የያዘችውን የህብረቱን የፕሪዝዳነሲ ስልጣን በመጠቀምም ህብረቱ እንደጉጉል ባሉ ትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ላይ ሊጥል ያሰበውን ቁጥጥር እንዲገፋበትና ተግባራዊ እንዲያደርግ የበኩላቸውን ያደርጋሉ ተብሎ ይታሰባልም።  

ከወዲሁ ግን ፕሬዝዳንት ማክሮን የመጀመሪይ የድል ማግስት የውጭ አገር ጉዟቸውን ወደ በርሊን በማድረግ  ክቻንስለር ኦላፍ ሹልዝ ጋር እንደሚመክሩ ነው የሚጠበቀው።

ገበያው ንጉሴ

አዜብ ታደሰ