የሽታይንማየር የአፍሪቃ ህብረት ጉብኝት
ረቡዕ፣ ጥር 22 2011ማስታወቂያ
የጀርመን ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር በኢትዮጵያ ያደረጉትን የ3 ቀናት ጉብኝታቸውን ዛሬ አጠናቀው ወደ ጀርመን እየተመለሱ ነው። ፕሬዝዳንቱ ዛሬ እኩለ ቀን ላይ ከአዲስ አበባ ለመነሳት ቢያቅዱም አውሮፕላናቸው ባጋጠው የቴክኒክ ችግር ምክንያት ጉዞአቸው እንዲዘገይ መደረጉ ተዘግቧል።ሽታይንማየር ዛሬ ጠዋት በአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽን በመገኘት ከህብረቱ ባለሥልጣናት እና ሠራተኞች ጋር የሀሳብ ልውውጥ አድርገዋል። የህብረቱ ቃል አቀባይ ለDW እንደተናገሩት ሽታይንማየር የጀርመንን እና የአፍሪቃ ህብረትን ትብብር የማሳደግ ፍላጎት አላቸው። የጀርመን መንግሥት በአፍሪቃ ህብረት አማካይነት የአባል ሀገራት ልማትን ሊያፋጥኑ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ እየሰራ መሆኑንም ቃል አቀባይዋ ተናግረዋል። ያነጋገራቸው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ