1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም.

ዓርብ፣ ጥር 26 2015

«ከ50% በታች ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲዎች የመቀበል አቅምን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የተሻለ ውጤት ያመጡት ተመርጠው ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡና ደካማ ውጤት ያስመዘገቡባቸውን የትምህርት ዓይነቶች ለ1ዓመት በዩኒቨርስቲዎች እንዲማሩ ተደርጎ የሚሰጣቸውን የመመዘኛ ፈተና የሚያልፉ ከሆነ የ1ኛ ዓመት የዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን ይጀምራሉ»ት/ሚኒስቴር

https://p.dw.com/p/4N5PZ
Gipfeltreffen der Frontstaaten Somalias in Mogadischu
ምስል Ethiopian PM Office

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት፥ ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም.

«ኢትዮጵያና ሶማሊያ አንድ ቤተሰብ ናቸው ሰላም ለማውረድ የሚከናወነው ስራ ጥሩ ነው።» የሚልነው።  ኑረዲን ሁልጫፎ  «በምስራቅ አፍሪካ አዲስ የ ጂኦ ፖለቲካ አብዮት ያስፈልጋል::ኢትዮጵያ ደግሞ ይህን በበላይነት መምራት ይኖርባታል የሚል አስተያየት አለኝ»ብለዋል። ኢቫንጀሊስት ቴዎድሮስ በሚል የፌስቡክ ስም የሰፈረ አስተያየት መተባበሩ ጥቅም እንዳለው ያጎላል።«ምሥራቅ አፍሪቃ አንድ እየሆነችው ነው። አንድ ከሆን እንቆማለን ከተከፋፈልን ግን እንወድቃለን።»ይላል። ጥሩ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን የጀመሩት ኤፍሬም ከበደ በፌስቡክ ምክንያቱም በማለት ይቀጥላሉ «ምክንያቱም የጎረቤት ሰላም ማጣት ለራስም አሳሳቢ ስለሆነ!» ካሉ በኋላ «ነገር ግን  ሀገራችን አሁን ምን ላይ ነች? ኢትዮጲያ ሀገራችን ዜጎች የሚፈናቀሉበት፣ቀን በቀን ሰው የሚገደልበት ፣ዜጎች ላባቸውን ጠብ አድርገው የአፈሩት ሀብት በደቂቃ የሚወድምበት ሀገር ላይ ሆነን፣ቀሪው ዜጋ ደግሞ በፍርሀት የሚኖርባት ሀገር ሆናለች!ስለዚህ ቅድምያ ለውስጥ ችግራችን ፖለቲካዊ መፍትሄ መስጠት ያስፈልገናል ሲሉ ሃሳባቸውን ደምድመዋል። የአይናለም ሺበሺ «የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች ይላል። ጊዜ ንኩሉ በሚል የፌስስ ቡክ ስም «ኤርትራ የት አለች?  (ፕሬዝዳንት) ኢሳያስን ረስተዋል የሚል ጥያቄ አለ። ወልደ ማርያም መዝገቦም በፌስቡክ እሱ (ኢሳያስ)የት ቀረ ለማስታወስ ብዬ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ የኬንያ የጅቡቲና የሶማሊያው መሪዎች በመቀድሾው ጉባኤያቸው የተስማሙበት የጋራ ዘመቻው ደቡብ እና ማዕከላዊ ሶማሊያ የሚገኙ የአሸባብ ጠንካራ ይዞታዎች ላይ እንደሚያነጣጥር በጋራ መግለጫቸው አሳውቀዋል። 
ሰሞኑን በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ብዙ አስተያየቶች ከተንሸራሸሩባቸው ጉዳዮች መካከል የኢትዮጵያ  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ስለተፈጠረው ቀውስ የሰጡት ማብራሪያና የቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ፣ዐቢይ የሰጡትን ማብራሪያ በመቃወም የሰጠው ባለ ስድስት ነጥብ መግለጫ ይገኙበታል። ዐቢይ በዚህ ሳምንት ለካቢኔ አባሎቻቸው በሰጡት ማብራሪያ «የተፈጠረው ችግር ቀላል እና በንግግር የሚፈታ ነው በማለት ለማግባባት የተደረጉ ሙከራዎች እንደነበሩ ተናግረው ነበር። ይሁንና ቅዱስ ሲኖዶሱ  ይህንን በቤተ ክርስቲያኗ “አስተምህሮ ውስጥ ጣልቃ እንደመግባት እና የምታስተላልፋቸውን ሃይማኖታዊ እና ቀኖናዊ ውሳኔዎች ያላቸውን ውጤት ወደ ጎን የተወ ነው” በማለት እንደተራ ግጭት እና የግለሰቦች አለመግባባት አድርገው ማቅረባቸው ተገቢ አለመሆኑን ገልጿል።  አብዛኛዎቹ ጽንፍ የያዙ፣ ዘለፋ ያመዘነባቸውና ጥላቻዎችን የሚነዙ ናቸው።  ከዚህ ከጸዱት በጣት ከሚቆጠሩት አስተያየቶች የሚከተሉትን ሃሳቦች አግኝተናል። ጥቁር ሰው በፌስቡክ  « የጎሳ ፖለቲካችን ፍሬ መስጠት ጀምሯል የዘር ፖለቲካችን በዚህ ከቀጠለ ሀገርና ሀይማኖትም ሊያሳጣን ይችላል። የሀይማኖት አባቶች ከዚህ የመበላላት ፖለቲካ ራሳቸውን አርቀው ህዝቡን ይመልሳሉ ብለን ስንጠብቅ እነሱም በ10 ጣታቸው ተዘፈቁበት።»ሲሉ አብደታ አራርሳ «በሀይማኖትም ሆነ በፖለቲካ የሕዝብ ጥያቄ ከታፈነ ይዋል ይደር እንጂ አፈናውን ፈንቅሎ መፈንዳቱ አይቀሬ ነው። መራራ እውነት ።» በማለት  በጭሩ ሃሳባቸውን አስቀምጠዋል። »ስዩም ስለሺ ደግሞ ማሰሰቢያ አላቸው። «በእምነት ጉዳይ ባትገቡ ይበጃል ውዝግብ ቢቀስቀስ መከላከያ የሚያቆመው ጉዳይ አይደለም፣ ሕዝባችን ለሃይማኖቱ ቀናኢ መሆኑን አትዘንጉ»ይላል።
 ወርቁ በዳዳ ዋቅቶላ ዘለግ ያለ አስተያየት ሰጥተዋል። ሃሳባቸው አጠር ብሎ ሲቀርብ «እኔ ስለ ሹመቱ ሀሳብ መስጠት አልፈልግም። የቤተክርስቲያኗ የውስጥ ጉዳይ ስለሆነ ቤተክርስቲያኗ ራሷ መፍታት አለባት ብዬ አምናለሁ። ነገር ግን መብት መጠየቅና አልፈፀም ካለ በሕጉና በደንቡ መብትን ማስከበር ወንጀል ሆኖ መታየት የለበትም። ግብዝ ግለሰቦች የተፈጠረውን ቀዳዳ እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው የፖለቲካ ፍላጎታቸውን በሀይማኖት ጥላ ስር እያራመዱ ይገኛል።በመሆኑም ቆም ተብሎ በእርጋታ መፍትሄ ካልተቀመጠለት ኋላ ለመፍታት እጅጉን ሊያስቸግር ይችላል። ሚዲያዎችም ገለልተኛና ሚዛናዊ መሆን አልቻሉም። ይህም ሌላ ፈተና ነው! በአጠቃላይ ይህ ጉዳይ "በዘመቻ፣በውግዝት፣በግዞትና በእልህ" እንደማይፈታ ግን አስረግጬ መናገር እፈልጋለሁ ፣ሲሉ ሀሳባቸውን አጠቃለዋል። 
ከጥቂት ቀናት ወዲህ በሰፊው መነጋገሪያ የነበረው ሌላው ሰሞነኛ ጉዳይ ያለፈው ዓመት የአስራ ሁለተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ነው። የ2014 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎች መካከል ከግማሽ በላይ ውጤት ያስመዘገቡት ሦስት ነጥብ ሦስት ብቻ መሆናቸው ሲያነጋግር ከርሟል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፈተናውን መውሰድ ከቻሉት 896 ሺህ 520 ተማሪዎች ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡት 29,909 ብቻ መሆናቸውን ተናግረዋል።  ፈተናው የተሰጠው በዩኒቨርስቲዎች ነው የተሰጠው ። ዓላማውም ፈተናን ከስርቆትና ኩረጃ መከላከል መሆኑ በወቅቱ ተነግሯል። ሚኒስትሩ ራሳቸው አስደንጋጭ ባሉት ውጤት ላይ በማኅበራዊ መገኛ ዘዴዎች የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል።  ሳንኩራ ኤ ገበየሁ በፌስቡክ «አድሱ የፈተና ስርዓት ትክክለኛ አካሄድ ነው። በማለት ለፈተናው አሰጣጥ ድጋፋቸውን ሲሰጡ ኪሩቤል የማነህም « የፈተና አሰጣጡ ጥሩ ነው ምክንያቱም በሁለት እግሩ የሚራመድ ትውልድ ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል። በረከተአብ ኤም መኔቦም « ግፉበት የተሸለ ትውልድን ለመፍጣር የተሸለ አእምሮ ያስፈልጋል ትክክለኛ ሙያ መቼም ቢሆን ያስከብረል ሀገርን ያነጸል!!!! ብለዋል ። «በጣም ደስ ይላል ሰው የልፋቱን ማጨድ መጀመሩ ታሪካው ነው»ያሉት ደግሞ ወግደረስ በዛ ናቸው
«አሁን ገና ለትምህርት ጥራት ጥሩ እየተሰራ ነው,።ዲግሪ ከረሜላ አይደለም ዝምብሎ የሚሰጠው አሪፍ  ነው ሚኒስትራችን ተመቸኝ ሁሉም እንደስራው ያገኛል። ብለዋል ጌች ኪንግ በፌስቡክ ። ሳዳ ጀማል «ችግሩ ተማሪ አይደለም ያለ መፍትሄ የተማሩ ተማሪዎች አሉ  ደጋግሞ ቢጠየቁ መፍትሄ ያላገኙት እነዚህ ተማሪዎች ለምን ወደቁ ይባላል? ችግሩ የተማሪ አይደለም።እስኪ ገጠር ውስጥ ያሉ ትምህርት ቤቶችን ፈትሹ ሲሉ ሃሳባቸውን አጠቃለዋል።
በላይነህ ሰደቦ  ።«የትምህርት ጥራትን ለመረጋገጥ ፈተና ማክበድ ሰይሆን ለተማሪ መጽሐፍ ማሟለት፣ ለአስተማሪ በቂ ዝግጅት እንድያደርግ ድጋፍ መድረግ አለበት፤ ይህ ሰይሆን የትምህርት ጥረትን ማረጋገጥ ከባድ ነው። ሲሉ ጉድለቶችን ጠቁመዋል
ዘማን እሱባለው ንጉሴ ደግሞ ውጤቱን ያዩበት መንገድ ሌላ ነው። «ሠውየው ከየት መጀመር እንዳለበት ያወቀ አይመስለኝም የጀመረው ከአናቱ ነው ስርነቀል ለወጥ እንዲመጣ ካስፈለገ እውነትም ከልቡ ሰለትምህርት ጥራት ከተጨነቀ መጀመር የነበረበት ከመነሻው ነው በዚህ የተነሳም ለወጡም እንደለውጥ ላይመዘገብለት ይችላል ከ890 በላይ ተማሪ  አስፈትኖ 30,000 ብቻ ካለፈ ለወደቀው እጅግ በርካታ ለሆነውም መፍትሔ አብረህ መፈለግ አለብህ ምክንያቱ ትልቅ እቀውት የሚጠይቀው እዚጋ ነው ሲሉ የበኩላቸውን አስተያየት አቅርበዋል
 ሚኒስትሩ ፣ከ50 በመቶ በታች ያመጡ ተማሪዎች የአገሪቱን ዩኒቨርሲቲዎች የመቀበል አቅምን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት “የተሻለ ውጤት ያመጡት ተመርጠው ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገቡና ደካማ ውጤት ያስመዘገቡባቸውን የትምህርት ዓይነቶች ለአንድ ዓመት በዩኒቨርስቲዎች ውስጥ እንዲማሩ ተደርጎ፤ የሚሰጣቸውን የመመዘኛ ፈተና የሚያልፉ ከሆነ የአንደኛ ዓመት የዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን ይጀምራሉ ብለዋል 

Äthiopien Das äthiopische Bildungsministerium hat angekündigt, dass die Schulprüfungen auf Bundesebene stattfinden werden
የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋምስል Shewangizaw Wegyayehu/DW
Äthiopien General der äthiopisch-orthodoxen Kirche
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብጹእ አቡነ ማትያስ እና የቤተክርስቲያኗ ሲኖዶስ ዋና ጸሀፊ አቡነ ጴጥሮስ መግለጫ ምስል Solomon Muchie/DW
Gipfeltreffen der Frontstaaten Somalias in Mogadischu
የኢትዮጵያ፣የኬንያ፣የጅቡቲና የሶማሊያ መሪዎችምስል Ethiopian PM Office

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ